https://m.facebook.com/story.php?story_ ... 9403920568
ስድስቱ የፓርላማው ውሳኔዎች

በግፍ ለተጨፈጨፉ ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት
እንዲደረግ፣

በአገራችን በየትኛውም ክልልና አካባቢ በሲቪል ዜጎች
ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ያስከተሉ እና ንብረት ያወደሙ
ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ እንዲደረግ፣

. በየደረጃው ያለው አመራር አካል የፀጥታ አካል እና
የፍትህ ተቋም የሕዝቡን ደህንነትና ሠላም በጥብቅ
እንዲያስከብር፤ አጥፊዎች ለሕግ ተጠያቂነት
እንዲቀርቡ እንዲደረግ፣

ከመንደራቸው እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ
የማቋቋም ሥራ በአስቸኳይ እንዲሰራ፣

የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከየትኛውም
ጊዜ በላይ በወንድማማችነት፣ በአብሮነት እና በአንድነት
እንዲቆሙ፣

በምክር ቤቱ የበላይ አመራር የሚሰየሙ ስብጥሩ ሁሉንም ብዝሀነቶች ታሳቢ ያደረገ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን በማጣራት ምክር ቤቱ እና ለሕዝቡ በቂ መረጃ እንዲኖረው ለማስቻል፥ እንዲሁም ለቀጣይ እርምጃዎች የሚረዳ ምክረ-ሀሳብ እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች፡፡