Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Ethiopian Court Cleared Fmr Head of METEC Gen Kinfe Dagnew - Tigrayans Are finally getting vindicated

Post by sarcasm » 04 Mar 2022, 18:52



ሜ/ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በሜቴክ ዙሪያ ለዶ/ር አብይ አህመድ ትችት ምላሽ ሰጡ (3.5 years ago)


temari
Member
Posts: 3941
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Re: Ethiopian Court Cleared Fmr Head of METEC Gen Kinfe Dagnew - Tigrayans Are finally getting vindicated

Post by temari » 04 Mar 2022, 18:59

ZHabesha claims that the general is cleared only from 1 charge out of 4 and still has 3 charges open against him.


sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Ethiopian Court Cleared Fmr Head of METEC Gen Kinfe Dagnew - Tigrayans Are finally getting vindicated

Post by sarcasm » 04 Mar 2022, 21:20

የሜቴክ አከራካሪ ሁለት መርከቦች ግዥ ዙሪያ ሜ/ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሰጡት ምላሽ - NAHOO TV


sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Ethiopian Court Cleared Fmr Head of METEC Gen Kinfe Dagnew - Tigrayans Are finally getting vindicated

Post by sarcasm » 05 Mar 2022, 19:00

ኢህአዴግ እንደ ሜቴክ ..

Finfinne Times



የተለያዩ አውፕላኖችና የሰባት መርከቦች ባለቤት የሆኑት ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በነፃ እንዲፈቱ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስኗል። ብልፅግና ህወሓትን ለመምታት ከተጠቀመባቸው የፕሮፓጋንዳ ስልቶች መካከል የሜቴክ ምዝበራ ወንጀል ክስ ስኬታማ ነበር።

ምንም እንኳን ሜቴክ የመንግስት የልማት ድርጅት ቢሆንም ከነበረው ተፅዕኖና አቅም በላይ ተለጥጦ የኢህአዴግ የስልጣን ዘመን አሉታዊ ታሪክ ሂሳብ ማወራረጃ በመሆን መስዕዋትነት እንዲከፍል ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት ፣ የስኳር ኮርፖሬሽን ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር ፣ ከሜቴክ ጋር ሲሰሩ የነበሩ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ኮርፖሬሽኖችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ መጠየቅ የነበረባቸውን የፕሮጀክቶች ምዝበራና መንጎተቶችን ለሜቴክ በማሸከም ብልጣ ብልጦቹ ከደሙ ነፃ እንደሆኑና የለውጡ መሪ በማስመሰል ሾልከው ወጥተዋል።

ከአውሮፕላን እስከ ግዙፍ የንግድ መርከቦች ብሎም ሀገሪቱ ለሜቴክ መድባ የማታውቀውን ቢሊየን ብሮች በመጨማመር ጥሩ የፖለቲካ ትርፍ ሸምተውበት ነበር። ይህንን ሀጢያት በሙሉ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ በማሸከም በፕሮፖጋንዳ ለውሰው ህዝቡን አጋቱት።

ጀነራሉ በማንነታቸው ተጋሩ በመሆናቸው ደግሞ የህዝቡና የፕሮፓጋንዳው ማነጣጠሪያ ተጋሩዎች ላይና በ27 አመታት የስልጣን ዘመናቸው ለጥሩውም ለክፉውም አብረው በአንድ ግንባር ላይ ሲሰሩ በነበረችው ህወሃት ላይ ተላከከ።

እራሱን የለውጡ መሪ በማለት ከኢህአዴግ ላይ እራሱን ወደ ብልፅግና የቀየረው ቲም ምንም ሀጢያት ላይ እንደሌለበትና አዲስ እንዲመስል አርቴፊሻል ማንነት ያገኘበት ቅፅበት ልንለው እንችላለን። ህዝቡም ሾርቴ በመሆኑ የተነገረውን ተቀብሎ አጀንዳውን አቀጣጠለው።

የሆነ ሰአትማ ከኢትዮጵያ የተዘረፈውን 64 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጠ/ሚ አብይ አህመድ ያስመልሳሉ በማለት ለተለያዩ የውጭ ባንኮች ደብዳቤ እስከመፃፍ ተደርሶ ነበር። አንዳንዱማ ከሀገሪቱ የተዘረፈው ኢትዮጵያን ወደ አውሮፓ እድገት ይቀይር ነበር ያሉም አሉ።

ሜቴክ የኢህአዴግ ሀጢያት ማወራረጃ ሆነ። ሁሉም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና ግለሰቦች መጠየቅ ሲገባቸው አንዱ አንዱ ላይ በማላከክ የተገኘውን የፖለቲካ ትርፍ አጠቃላይ ሀገሪቱን ለመቆጣጠር ተጠቀሙበት። በእርግጥ ሜቴክ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያሳካቸውም ፕሮጀክቶች እንዳሉ ሁሉ ተጠያቂ የሚሆንበትም ፕሮጀክቶች አሉ።

ነገር ግን የኢህአዴግ የፕሮጀክት የአፈፃፀም ችግር ፣ የልማታዊ መንግስት ፖሊሲ ስህተቶች የፈጠሩት ተቃርኖዎች.. በፓርቲው ክፍተት የተፈጠሩ ብልሹነት ፣ የተለያዩ የአሰራር እንከኖች ፣ በአጠቃላይ እንደ ፓርቲና እንደ መንግስት የተፈጠረው ችግርን ለአንድ የመንግስት የልማት ድርጅት ሜቴክ በመስጠት እግረ መንገድም ህወሓትን ነጥሎ በመምታት ተሳክቶላቸዋል።

በነገራችን ላይ ሜጀር ጀነራል ክንፈን አሳልፎ ለፌደራሉ መንግስት የሰጠው የትግራይ ክልል ነው። የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ጀነራሉ ከተያዙ በኃላ የአጀንዳውና የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳውን አቅጣጫ ከተገነዘቡ በኃላ ..

"እኛ ጀነራል ክንፈን አሳልፈን የሰጠነው ሁሉም ያጠፉ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሆኑ ባለስልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑና የለውጡ ሂደትን ለማሳለጥ ግለሰቦች በህግ አግባብ እንዲዳኙ ካለን ልባዊ ፍላጎት እንጂ ለፖለቲካ ትርፍ እንዲውል አልነበረም" .. ብለው ነበር።


የሆነው ሆኖ በፕሮፖጋንዳ የተፈጠረው ግርግር .. እራሱን የለውጡ አመራር ብሎ ለሚጠራው ቲም መንገድ ማሳለጫ ተደርጎ የተሽሞነሞነውና የፖለቲካ ትርፍ የታሰበበት የሙስና ክስ ..የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎት ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በነፃ እንዲሰናበቱ ወስኗል።

ነገር ግን አሁን ላይ ጀነራሉ ነፃ ቢባሉም የብልጽግና ብልጣ ብልጦቹ ጥሩ የፖለቲካ ትርፍ ያጋበሱበት ወቅታዊ አጀንዳ ነበር።

Finfinne Times
Please wait, video is loading...


Post Reply