Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ጁንታው ያወደመው በ24 ሰዓት በስንት ርብርብ ስራ የምታስጀምር ጉደኛ ክልል¡¡ ይበለኝ የእጄን ነው ያገኘሁት ብሏል ዘፋኙ!! 11ዱ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀመሩ ETV

Post by sarcasm » 27 Dec 2021, 13:16

አሸባሪው ህወሓት ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 11ዱ ስራ ጀመሩ
******************
አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ከተማ ጉዳት ካደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 11ዱ ምርት ማምረት መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አሸባሪ ቡድኑ በደሴና ኮምቦልቻ ያወደማቸውንና ጉዳት ያደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች መልሶ ለማቋቋም ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቦታው ላይ ጊዜያዊ ቢሮ ከፍቶ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑ ይታወሳል።
ጊዜያዊ ቢሮው ከክልሉ መስተዳድር አካላት፣ ከባለድርሻዎች፣ ከባለሀብቶች፣ እንዲሁም ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ባደረገው ቅንጅታዊ ስራ 11 የጨርቃጨርቅ፣ የምግብና መጠጥ እንዲሁም የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ምርት የማምረት ስራ ጀምረዋል።
የጊዜያዊ ቢሮው ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደገለጹት በአካባቢው የሚገኙ ባንኮች፣ጉምሩክ፣ኢትዮ ቴሌኮም እና ኤሌክትሪክ ስራ መጀመራቸው ፋብሪካዎቹ ወደ ስራ እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረከቱ ሲሆን በቅርቡ ኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ሲለቀቅ ተጨማሪ ፋብሪካዎች ወደ ምርት ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።



https://www.facebook.com/EBCzena/posts/5158160657549102

https://www.facebook.com/stalinna/posts ... 3318469793


The tale of two textile factories


ወራሪ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የአማራ፣ የሶማልያ ሰራዊቶች በትግራይ በቆዩባቸው ወራት በትግራይ የነበሩ ፋብሪካዎችን ሙሉ ለሙሉ ነው ያወደሙት።
በተለይም ረሐብተኛው የኤርትራ ሰራዊት ከአልመዳ፣ አዲግራት መድሐኒት ፋብሪካ፣ ጎዳ የብርጭቆ ፋብሪካ፣ ሼባ ሌዘር፣ ሰማያታ እምነበረድ፣ ኢዛና የመአድን ፋብሪካ፣ ስፓ ውሐና ሌሎች ፋብሪካዎች ማሽነሪዎችን ነቃቆሎ ነው የወሰደው፤ መውሰድ ያልቻለውን ደግሞ በድማሚት አውድሞታል።

የአማራ የትምክሕትና የጄኖሳይድ ሐይልም እንዲሁ በምዕራብ ትግራይ የነበሩ የኢንዳስትሪ ተቋማት(የወልቃይት ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ) ሙሉ ለሙሉ ወደ አመድነት ቀይረዋቸዋል። የኢትዮጵያ ሰራዊትም እንዲሁ በንፅፅር ደረጃው አነስ ባለ መጠንም ቢሆን ተመሳሳዩን ፈፅሟል።

እነዚህ ፋብሪካዎች አሁን ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፤ እንደ አዲስ ካልተሰሩ በቀር ሊጠገኑ የሚችሉም አይደሉም፤ ሙሉ ለሙሉ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።
"አማራን አወደመ" የተባለው የትግራይ ሰራዊት ግን የኮምቦልቻ የኢንዳስትሪ መንደርን ሲጠብቅ ከረመ፤ እነሆ ከኢንዳስትሪው መንደር የተበላሸ ወይም የተዘረፈ አንድ ወሳኝ ማሽን ወይም ሌላ ወሳኝ ግብአት እንኳ ባለመኖሩ ይኸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ሊገባ ነው። ይህንን የኢትዮጵያ መንግስት ሚድያዎችም እያረጋገጡት ነው።
የትግራይ ሰራዊት ኮምቦልቻን የለቀቀ ቀን የከተማው ወጣቶች የኢንዳስትሪ መንደሩ ላይ የተወሰነ ዝርፍያ የፈፀሙ ቢሆንም የተወሰኑ የቢሮ እቃዎችና ጥሬ እቃዎች ነው የዘረፉት።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ይህንን ተራ የመንደር ዝርፍያ በትግራይ ሰራዊት የተፈፀመ የኢንዱስትሪ መንደሩንና ከውስጡ ያሉ ፋብሪካዎችን የማውደም ስራ" አስመስለው እያቀረቡት ነው፤ ገና ብዙ ብዙም ይላሉ። ፍፁም ሐሰት እንደሆነ ግን የኮምቦልቻ ህዝብ ያውቃል፤ ህሊና ያለው ሁሉ ሊያገናዝበው የሚችል ቀላል ሐቅም ነው።


በአጠቃላይ ከኢንዳስትሪ መንደሩ አንድ የተበላሸ የፋብሪካ ማሽን፣ አንድ የወለቀ ብሎን የለም፤ ፋብሪካዎቹም ሰሞኑን ወደ ስራ እንደሚገቡ እየተገለፀ ነው።
እናስ የትግራይ ሰራዊት የአማራ ጠላት ነውን?

የሚባለውን፣ የሚወራውን ሳይሆን አይናችን የሚያየውን ነው ማመን ያለብን። የትግራይ ሰራዊት ቢፈልግ የኢንዳስትሪ መንደሩንና ከውስጥ ያሉ በርካታ ፋብሪካዎችን ልክ የኤርትራ፣ የአማራና የኢትዮጵያ ሰራዊቶች እንዳደረጉት ወደ አመድ ክምርነት፣ ወደ ፍርስራሽነት መቀየር አይችልም ነበርን? እስቲ ያንን ለማድረግ ማን ከለከለው?





Please wait, video is loading...