Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?

Post by Guest1 » 25 May 2021, 15:49

የኢትዮ ህገ መንግስት ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ይላል። የኢትዮጵያ ህዝቦች አይልም።
እስከዛሬም ለምን ህዝቦች ተባለ ማነው ብሄር ማነው ብሄረሰብ ነበር ማነው ህዝብ ነበር ክርክሩ። ማነው ትልቅ ማነው ትንሽ? ነበር ፓለቲካው .... መዝሙሩም ብሄር ብሄረሰቦች የኢትዮጵያ ልጆች ነው የሚለው የኢትዮጵያ ህዝቦች አይልም። ወይ ጉድ!! ክክክክክክክክክክክክክ

የአሁኑ ክርክር የተነሳው ህዝብ እንጂ ህዝቦች አይደለንም ስለተባለ ነው። ህገ መንግስቱ የሚለው ብሄር ብሄረስብና ህዝቦች አገር እንጂ የኢትዮጵያ ህዝቦች አይደለም ይህ ቢሆንማ ብዙ አያጣላም ነበር። ከፍና ዝቅ ስላደረገ በ3 ደረጃ። እና? አሁን ሌላ ውዥንብር ወይም አጄንዳ ተከፈተ ክክክክክክክክክክክክ

የአማራ ህዝቦች ሳይሆን ለምን ህዝብ አልተባለም? ክክክክክ ለምን ህዝብ ይባላል? ለምን ብሄረ አማራ ብሄረ ትግሬ ወዘተ... እና የወላይታ ብሄረሰብ ... እና የኩናማ ህዝብ እንደተሰጣቸው መደብ አልተባሉም? ህገመንግስቱ የሚለው ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አሁን ደግሞ ህዝብና ህዝቦች ለምን? ፓለቲካ / የብሽሽቅ ፓለቲካም ስለሆነ!! የቃላት ጨዋታ አይደለም!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42672
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?

Post by Horus » 25 May 2021, 17:00

ገስት፣

ከላይ እንዳልኩት ነው። አንድ ቃል እንዴት ተፈጠረ? ሆን ተብሎ ነው ወይስ በዘልማድና በድንገት የሚሉት ሁሉም ትክክል ናቸው። በቋንቋ ቲኦሪ ወስጥ ብዙን ግዜ የአንድ ቃል ድምጽ፣ የፊደላት ድርደራ ቅደም ተከተል (እስፔሊንግ) እና የቃሉ ትርጉም ሆን ተብለው በቋንቋ ቀማሪዎች የሚሰሩ አሉ ። ከስር ጀምሮ፣ በፊደል ደረጃ ትግጉም ይዘው የመጡ አሉ። ብዙዎቹ በዚቮሉሽን ተናጋሪው ህዝብ እንደ ተመቸው የፈጠራችው እጅግ ብዙ አሉ ። ለዚህ ነው እያንዳንዱ ቃል ታሪክ አለው ያልኩኝ ። ግን ቋንቋ ብቸኛው ማሰቢያና ማወቂያ ብሎም መግባቢያ መንገድ ስለሆነ ለኮግ ኒቲቭ ሳይንስ፣ ለአርቲፊሻል ክህሎት፣ ለአርትና ማንኛውን የሰው አይምሮ የፈጠራቸው ነገሮች የሚመዘገቡትና ሚኖሩት በቋንቋ አማካይነት ሰለሆነ የዚያ መሰረት፣ ኳንተም ስለሆነ እንደ አርትም እንደ ሳይንስም መጠናት አለበት ፣ እያንዳንዱ ቃል ማለት ነው ። ግን ድንጋይን ለምን ድንጋይ አልነው? ቤትን ለምን ቤት አለነው የሚለው የራሱ ምርምር አለው ። በቲኦሪ ያንድ ቃል ድምጽ በዘፈቀደ የተሰጠ ነው የሚባለው ። ለዚህም ነው መኖሪያ ህንጻ አንዱ ቤት ሲለው ሌላው ሃውስ የሚለው ። ስም በመሰረቱ መታውቂያ ምልክ እንጂ ስለተሰያሚው ነገር ባህሪ አይነግረንም ። ዉሃ የሚለው ቃል ስለ ሃይድሮጂን ና ኦክሲጂ ምንም ስለማይነግረን ማለት ነው ።
Last edited by Horus on 26 May 2021, 13:33, edited 1 time in total.

Naga Tuma
Member+
Posts: 7362
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?

Post by Naga Tuma » 26 May 2021, 13:12

Horus wrote:
25 May 2021, 02:23
ቃል ብርሃን ነው፣ ቃል መብራት ነው!

እስቲ አንዳንድ በድንቁርና ላይ ቆመው ያሉ ቃላትና ጽንሰ ነገሮችን እናጣራ ።

የ'ሕዝብ' ስረቃል...

ቃሉ ሲጀመር የጥንታዊ ቀምጥ ወይም ቆጵት ነው። በዚያን ዘመን 'ከብ' ብሎ ይጀምራል ። 'ካ' በግብጽ ያንድ ነገር መንፈስ፣ ምስል፣ ወይም ዛሬ ጎስት፣ ኢሜጅ የምንለው ነበር። 'ባ' በግብጽ ህይወት፣ ህያው ማለት ሲሆን ዛሬ በላቲን 'ባዮ' የሚባለው ነው። በአነባበብ ደረጃ ግብጾች እንዴት እንዳሉት አሁን ተረስቷል። ስለሆነም አናባቢ የሌለው 'ከብ' አንድ ሰው ማለት ነበር።

'ከ' በድምጽ ሺፍት 'ሸ'፣ 'ሰ' ይሆናሉ ልክ ጠ፣ ጨ እንደ ሚሆነው ። ስለሆነም 'ሸብ፣ ሰብ' ዛሬም በሴምና በላቲን ውስጥ አሉ። ለምሳሌ ሆሞ ሴፒየን በሚለው የሰው ልጅ መጠሪያ ውስጥ ያለው ሴፒየን ሰብ ከሚለው የተወረሰ ነው ። ሰብ ማለት በኢትዮጵያ አብዛኛው ቋንቋዎች ሰው ማለት ነው።

በጉራጌኛ ሰው በቀጥታ ሰብ ይባላል። ቤተሰብ ስንል ቤተሰው ወይም የሰው ቤት ማለታችን ነው። ሰብ ወይም ሰው አንድ ግለሰብ ነው ።

በ ግዕዝና አረብኛ ሰብ ከሚለ ነጠላ ስም 'እስብ፣ ህዝብ' የብዝህ ስም ተቀዳ። በመሰረቱ ብዝህ፣ ብዙ ማለትም ከዚያ የተቀዳ ነው።

በአጭሩ ሕዝብ ማለት ሰብ ለሚለው ነጠላ ስም ፕሉራል ስም ነው ። ሕዝብ ማለት ብዙ ግለሰቦች ማለት ነው ። እንዲያውም በጉራጌ ቋንቋ ሕዝብ ማለት ሰቦች ነው የሚባለው። ብዙ ሰብ ሰቦች ይባልሉ። ብዙ ሰው ሕዝብ ይባላሉ ።

የድንቁርና ስህተቶች

ብሄረሰብ የሚለው ቃል ስህተት ነው ። ብሄረ ሰብ አንድ የብሄር ግለሰብ ማለት እንጂ ያንድ ብሄር ብዙ ሰቦች ወይም ሰዎች ማለት አይደለም ። ይታረም !

ሕዝቦች የሚለው ቃል ደደብ ነው ። ሕዝብ ብዙ ወይም ፕሩላር ስም ነው ። ስለዚህ ድጋሚ ብዝህ ቃል ነው ። ልክ መጻፍት ብዙ ነው ። መጻህፍቶች ደደብ ነው ።ድጋሚ ማብዛት ነው።

ስለዚህ ብሄረሰብ ማለት አንድ ሰው ብቻ ነው የሚጠራው።

ሕዝቦች የሚለው ቃል ፍጹም የድንቁርና አባባል ነው ። ሁለቱም ይታረሙ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚሉ ደንቆሮች ናቸው ። ያሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም የኢትዮጵያ ሰቦች ናቸው ።

ሕዝብ ብዙ ሰው፣ ብዙ ሰብ፣ ሰቦች፣ ሰዎች ማለት ነው !!


ሆረስ፥

የሳባ ፊደሉ ሠ እና የሮማን ቁጥር III መመሳሰል ደንቆኝ ሳያበቃ ሳፕያን የሚለዉ ቃል መሰረት ሰብ ነዉ የሚል ሌላ ድንቅ ኣመጣህ? ተመስገን። ሰብ/ሰበ/ሻብያ/ሳባ የሚሉት ቃላት ላይ ኣይኖቼ ካረፉ ሰንብተዋል። ሳፕያን ከሰብ መመሳሰሉን ከኣሁን በፊት ገምቼ ኣላዉቅም።

ኣዉሮፓ ዩሮፕ የተባለችን ሰዉ ስም ሲጠቀም የእኛዉ እዉቅ ንግስት ሳባ በላትን ሳፕያን ከተባለዉ ቀድማ ስሙን ኣገኘች?

ሌሎች የታሪክ እዉነታዎች ቢቀሩ እነዚህ ሁለቱ ብቻ ግራንድ ኢትዮጵያን ሬነይሳንስ ከሚለዉ ግራንድ ሬነይሳንስ የሚለዉን መጠቀም የበለጠ ኣርቆ ኣስተዋይነት ያደርጋሉ።

እኔ እንደገባኝ ከሆነ ሰብ ኣንድ ሰዉን ሳይሆን ለብዙ ሰዎች ነዉ። ሰበ፣ ሰብ፣ እና ሶሳይቲ ተመሳሳይ ይርጉም ያላቸዉ ይመስለኛል። ግለሰብ፣ ኣንድ ሰዉ፤ ቤተስብ፣ በኣንድ ቤት የሚኖሩ ብዙሃን ሰዎች፤ መህበረስብ፣ ያበሩ ወይም የተባበሩ ብዙሃን ሰዎች፤ ብሄር በእግዛብሄር ስር የሚኖሩ ሰዎች ይመስለኝ ነበር፣ ታሪካዊ አመጣጡ።

ይህን የትርጉም ልዩነት የበለጠ ጥናት የምያስተካክለዉ ይሆናል።

Horus
Senior Member+
Posts: 42672
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?

Post by Horus » 26 May 2021, 14:18

ናጋ ቱማ፣

እንደ ምን ሰነበትክ? አባይን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል ይባላል። ገና ምን አይተህ! አንድ እጅግ ጠቃሚ መረጃ ልስጥህ፣ በቋንቋ ላይ ያለህ ኪዩሮሲቲ ስለሚመቸኝ ።

በ1510 ዓም እንደ አውሮፓ ቀመር ኢየሩሳሌም ውስጥ ለመስቀል ጦርነት ወዶ ዘማች ሆነው የመጡ ሮማዊያን የሃይማኖት ሰዎች ነበሩ ። እንዚህ ሮማዊያን ካቶሊኮች መሆን አለባቸው ። በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም እና አካባቢው ከአንድ በላይ ቤተክርስቲያና (ገዳማት) ነበሯት ። የኦቶማን አምፓየር የወሰዳቸን ጨምሮ።

እነዚህ ሮማዊያን እነዚያ ገዳሞች ውስጥ ኢትዮጵያዊ መነኩሴዎች ያገኛሉ ። መነኩሴዎች የሚጠብቋቸው ለ1000 አመት የተደረሱ ግዙፍ የብራና መጻህፍቶችን ሲያዩ ፈረንጆቹ ፍጹም ለያምኑ አልቻሉም ። የአለም እውቀት (ዊዝደም) ያዘሉ ድጓዎች መሆን አለባቸው በሚል እምነት ባልሳሳት 2 ወይም 3 የኢትዮጵያ ቄሶችን እስከ መጻህፍቶቻቸው ጋር ሮማ ወሰዷቸው። ስምምነቱ ምን እንደ ነበር አላውቅም፣ ማለትም ጉብኝት፣ ለትምህርት፣ በግዴታ ግልጽ አይደለሁም።

ኢትዮጵያዊያኖቹ ቫቲካን ውስጥ የላቲን ቋንቋ እንዲማሩ ተደረገና ያመጧቸውን የግዕዝ መጻህፍት (ወይም መጽሃፍ) ወደ ላቲን ተረጎሙ። እነዚያ የግዕዝ ቃላት ሁሉ የላቲን ቋንቋ አካል ሆኑ ። በዚህ ምክንያት ዛሬ እስከ 30% ያክል የፕሮቶ ኢንዶ ኢሮፒያን ስረው (ስረ) ቃላት ከግዕዝ የተገኙ ናቸው ።

አሁን አንድ ቃል ብቻ መርቄልህና ላብቃ!

ፌኖሜና የሚባለው ትልቅ ቃል ነው እንደ ምታቀው! እኛ ወደ መሃይምነት ወርደን ረሳነው እንጂ ቃሉ ግዕዝ ነው ። ፌኖ ማለት ፋና ወይም ብርሃን፣ የሚታይ፣ የበራ ማለት ነው ። ፋፋ፣ ፏ አለ፣ ፈፋ፣ የምንለው ማለት ነው። ሜና የሚለው ሁለተኛው ቃል እኛ መና፣ ባዶ፣ ምንም የሌለው፣ የሚለው ነው ። ደመና፣ ሀብስተ መና እንደምንለው ማለት ነው።

ስለዚህ ፌኖሜና ማለት ባዶ ብርሃን፣ በአይምሮ ወስጥ የሚታይ ፈረንጆች እንደ ሚሉት the appearance of an image or picture of something in the mind ነው ። ፋና መና (መና ፋና) ባዶ ብርሃን፣ ባዶ ፍኖት ማለት ነው። ግ ዕ ዙ ህብስተ መና እንጂ መና ህብስት አይልም ። ስለዚህ በ ግዕዝ ፋናመና ወይም ፍኖተመና ነው የሚለው ልክ እንደ እንግሊዝኛው ማለት ነው ።

ስለዚህ ፌኖሜኖሎጂ ማለት በግዕዝ ስነ ፍኖተመና ይባላል።
ኬር

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?

Post by Guest1 » 26 May 2021, 14:45

etymology ሰረ ቃል መፈለግ ማን ይከለክላል? ማንም። ታሪካዊ አመጣጥ።
ነጥቡ
ቤተሰብ ምንድነው? ስው የሚኖርበት? ወይ ጉድ!! አንድ ሚስትና አንድ ባል? one family ሁለት ሚስትና ልጆቿቸው? ሁለት family? ከአያት ጋር። extended family? ከጊዜና ቦታ ጋር የተለያየ ትርጉም አለው። እንደየአገሩ የኢኮኖሚ እድገት ስለዝህም የፓለቲካ እድገት።
people? በአንድ አካባቢ የሚኖር ህዝብ ተመሳሳይ ወይም አንድ ቋንቋ የሚናገሩ
ብሄርስ? ብሄረሰብ? ሁሉም ህዝብ ናቸው። ግን ደረጃቸው የለያያል። እንደ የኢኮኖሚውና እንደየአገሩ ፓለቲካ የተለያየ ትርጉም አለው።

ስላለፈው በእርግጥ መናገር የሚቻለው። በቡድን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ስማቸው ጎሳ ክ ላን ትራይብ የሚባሉት ከሌላው ጋር ያልተቀላቀሉ ስም ነበራቸው ክላን ትራይፕ ይባላሉ። ስምም አላቸው እራሳቸው ያወጡት ወይም ሌላው ያወጣላቸው ስም አላቸው። ከሌላው ጋር ሲቀላቀሉ ህዝብ ይሆናሉ። የዚያ አገር ሰው ይባላሉ። ህዝብ የሚሆኑት ህዝብ ነን ማለት ሲጅምሩ ወይም የሌላ አገር ሰው የዚያ አገር ህዝብ ስላቸው ነው። people በእንግሊዝኛ ሊፈልግ ነው!! ተናድጃለሁ!! ክክክክ
ዋናው ነጥብ
እዝህ ህዝብ ሳይሆን ህዝቦች ሲባል የፓለቲካ ክርክር ነው የቃል አመጣጥ ወይም ህዝብ ህዝቦች ክርክር አይደለምምምምም! ወይ ጉድ!

አንድ የማህበረሰብ ወይም የህብረተሰብ ፓለቲካዊ ቃል ነው። የዛን ህብረተስብ አኗኗርና የፓለቲካ ስርኣት ይነግራል ነው።
ቤት እራሱ ፓለቲካ ነው። ጎጆ ከሆነ ማን እንደሚኖርበት እናውቃለን።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?

Post by Guest1 » 26 May 2021, 15:02

people
c. 1300, peple, "humans, persons in general, men and women," from Anglo-French peple, people, Old French pople, peupel
"people, population, crowd; mankind, humanity,"
from Latin populus "a people, nation; body of citizens; a multitude, crowd, throng," a word of unknown origin. Based on Italic cognates and derivatives such as populari "to lay waste, ravage, plunder, pillage," Populonia, a surname of Juno, literally "she who protects against devastation," the Proto-Italic root is said to mean "army" [de Vaan]. An Etruscan origin also has been proposed. The Latin word also is the source of Spanish pueblo, Italian popolo.
In English, it displaced native folk.
Sense of "Some unspecified persons" is from c. 1300.
Meaning "body of persons comprising a community"
is by mid-14c. (late 13c. in Anglo-French);
the meaning "common people, masses"
(as distinguished from the nobility) is from late 13c.
The meaning "members of one's family, tribe, or clan" is from late 14c.
The word was adopted after c. 1920 by Communist totalitarian states, according to their opponents to give a spurious sense of populism to their governments.
It is based on the political sense of the word,
"the whole body of enfranchised citizens (considered as the sovereign source of government power," attested from 1640s.
This also is the sense in the legal phrase The People vs.,
.S. in US cases of prosecution under certain laws (1801)
.

መጨረሻ ላይ ያምታታሉ። እውነቱ ለመደበቅ ስለሚፈለግ እነሱ የፈጠሩት ሆኖ ሳለና ቶታሊቴሪያን ማለት ስላለባቸው።

ለማንኛውም ቶፒኩ ሃሪፍ ነበር። ሆረስ እናመሰግናለን።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7362
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?

Post by Naga Tuma » 27 May 2021, 02:18

ሆረስ፥

ለጨመርክልን ቃል እና ታሪክ ኣሁንም ተመስገን።

እንደቫቲካኑ የእኛም ገዳማት በቂ ላይብረሪ ቢኖራቸዉ የስደስታል።

ቫቲካን ዉስጥ ስላሉት ላይቤሽን ጉድጓዶች በባህል ካየሁኣቸዉ ጋር የሚመሳሰሉ ዳ ቪንቺ ኮድ መጽሃፍ ዉስጥ ሳነብ በጣም ደንቆኝ ነበር።

የታሪክ ኣባዩን የቻልኩትን ያህል መጋት በደስታ ነዉ።

ገስት፩፥

ነጥቦችህን በተለያየ ዘመናት/ጀበነ ወይም በረ/ኢራ ብትካፋፍል የበለጠ ገልጽ ይሆናሉ። መጻፍ ሳይጀመር በፊት መናገር ብቻ የነበረበት ጥንት ዘመን፣ መጻፍ የተጀመረበት እና ሽግግሩ ያመጣዉ ኣስተዋጽኦ፣ መሬትን እንደርስት በማየት ሶቨርኒቲ የሚል ጽንሰሃሳብ እውቅና ካገኘበት ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ። የቃላት መሰረታቂ ትርጉሞች ቅዝምዝም ሳይሆኑ ዘመን ተሻጋሪዎች ናቸዉ። ስምምነቶች ያዉ ስምምነቶች ናችዉ።

Post Reply