በስቃያቸው ተሳልቀናል። ጁንታውን ለመደምሰስ በሚባል ስም ለወንበር በተደረገ ጦርነት ድጋፋችንን ሰጥተን ነበር። ያተረፍነው ግን የትግራይን ህዝብ ስቃይና ሰቆቃ ብቻ ነው።
እዚህም እዚያም በህውሀት ሲሳበቡ የነበሩ ችግሮች አሁንም እንደቀጠሉ ነው። ህውሀት ከተደመሰሰ በየቦታው ስታቀናብራቸው ነበር የተባሉት ችግሮች መቀረፍ ነበረባቸው።
ከጦርነቱ ምንም አላተረፍንም። እንደ ሀገር ሉዝ አድርገናል። አሁንም በትግራይ ክልል በየቀኑ በረሀብ ምክንያት ከመቶ ሰው በላይ ይሞታል። ወጣቶች በየመንገዱ ይገደላሉ። ንብረታቸውን ተዘርፈዋል። ሴቶቻቸው ተደፍረዋል። ህፃናቶቻቸው እናቶቻቸው ለረሀብና ለስደት ተጋልጠዋል። እነዚህ ህዝቦች ቂም ቢይዙብን አትናደዱባቸው። ብሎክ አታድርጓቸው። ከኛ ብዙ ስለሚጠብቁ ነው የሚሰድቡን። አሁንም እንደ ሀገር አብረን እንድንቀጥል ከተፈለገ ለትግራይ ህዝብ ፍቅር ማሳየት ነው ያለብን። ንዴታቸውን ይወጡብን። ይስደቡን ። ትክክል ናቸው።
እኛ አደባባይ ላይ ወጥተን ለተፈፀመባቸው ግፍ ይቅርታ መጠየቅ አለብን። ይሄንን መንግስት መቃወም አለብን። በቃን ማለት አለብን።
የሆነው ሆኖ ትግራይ will prevail ❤
Please wait, video is loading...