Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4615
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

መብራት ኃይል : እዚህ አገር በጥባጭ ነው! ለምን አይፈርስም? ለምን አይሸጥም? ሕዝቡን እያማረረ እስከመቼ?

Post by Abaymado » 24 Mar 2021, 22:58

ህዝቡ ሁሉ የሚያወራው ስለዚህ የበሰበሰ መስሪያ ቤትን ጉድ ነው:: ከንፅህና ንፅህና የለው : ቅልጥፍና የላቸው : ግድየለሽ የሆኑ: ሂሳብ በስርዓቱ አስልተው መናገር የማችሉ : ስራን በግዜው የማያደርሱ ።።።።

የአንድ ሰው የተተመነለት ሂሳብ 1200 ብር ሆኖ እነሱ 10000 ብር የሚሉ ጉዶች ናቸው:: ያ ሰው ትክክል አይደለም ይጣራልኝ ብሎ ከሄደ መልስ የሚያገኘው ከአመት በህዋላ ነው::

አሁን ደሞ ያየሁት ጉድ:: የመብራት ኃይል ሰራተኛ ወደ አንዱ ቤት ሄዶ "በሰዓቱ አልከፈላችሁም" ብሎ መብራት ይቆርጥባቸዋል:: ሰዎቹ መብራት ኃይል ሄደው ያመለክታሉ:: መብራት ኃይል "150 ብር መቀጫ ትከፍላላችሁ" ሲሉዋቸው:
ሰዎቹ :"ለምን እንከፍላለን እኛ በሰዓቱ ነበር የምንከፍለው : ለምን ተቆረጠ?" ቢሉ
መብራት ኃይል: ደሞ "ለምን አትቁረጥ ብላችሁ ደረሰኝ አታሳዩም ነበር" ይላሉ::
ሰዎቹ :" ሰውየው ደረሰኝ ማየት አይፈልግም : መቁረጥ ነው የሚፈልገው" ብለው ቢነግሩም መብራት ኃይል ግን መፍትሄ አልሰጠም::

ከዛም ሰዎቹ መቀጫውን ከፍለው የሰውየውን ስልክ ቁጥር ተቀብለው "ደውሉለት" ይባላሉ::
ሰውየው ስልኩን ሳምንት ሙሉ ዘግቶ ጠፋ:: ሰዎቹ ሳምንት ሙሉ ጨለማ ውስጥ ከረሙ::

ከዛም መብራት ኃይል የሚሰራ ሰው ይህንን ሰው ፈልጎ ያገኘውና ጉቦ ሰጥቶ ለምኖ እንዲቀጥል ያረገዋል::

ይህ ነው መብራት ኃይል ማለት:::

በነገራችን ላይ መብራት ኃይል ይህንን ከተከታተለው: የልጁ ስልክ ቁጥር ይህ ነው
09433303439 (ታምራት ) ነው:: ይህን የሰው እና እሱን የመስሉ ሰዎች እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል::

Axumezana
Senior Member
Posts: 19086
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: መብራት ኃይል : እዚህ አገር በጥባጭ ነው! ለምን አይፈርስም? ለምን አይሸጥም? ሕዝቡን እያማረረ እስከመቼ?

Post by Axumezana » 25 Mar 2021, 00:34

I myself have similar experience. Lier Abiy is not interested in controlling corruption. Mebrat Hail , Levels and Gebiwoch are the most corrupted. After lier Abiy coming to power my experience is corruption has increased by ten fold( 1000%). How is lier Abiy dreaming to bring prosperity in highly corrupted society?

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: መብራት ኃይል : እዚህ አገር በጥባጭ ነው! ለምን አይፈርስም? ለምን አይሸጥም? ሕዝቡን እያማረረ እስከመቼ?

Post by Ethoash » 25 Mar 2021, 07:42

ወንድሞቼ

ጉቦን የምታጠፉት ለስራተኛው ትክክለኛውን ደሞዝ ስትከፍሉት ነው።

ደሞዝ ብቻ አይበቃም ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት አለበት ለምስሌ ሕክምና በነፃ ። ኢንሽራንስ የሞትና የደህንነት ኢንሹራንስ መብራት ሀይል ለሁሉም ስራተኞች መግባት አለበት። ሌላው ደግሞ የቤት ክራይ ድጎማ ቤት ክራይ የቤት ባለቤት ለመሆን በሚል ፕሮግራም ለስራተኞቹ ቤት ስርቶ መስጠት አለበት።

ለምሳሌ የቤት ዋጋ አንድ ሚሊዬን ብር ቢሆን ። ቤቱን ስርቶ ለስራተኛው በወር አስር ሺህ ብር ክፈል የለዋል ። ደሞዜ አምስት ሺህ ነው ። እንዴት ነው አስር ሺህ በር ለቤት ሞርጌጅ የምከፈለው ይላል። ታድያ ይህ ነው የደሞዝ ጭማሪ የሚያስፈልገው። ጭማሪው ስራተኛው ኪስ ሳይገባ ተመልሶ ወድ መብራት ሀይል ኪስ ይገባል አስር ሺህ ብር የቤት ክራይ ሲከፍል። እንግዲህ ለስላሳ አመት ይህንን ክራይ ወይም ሞርጌጅ ከፍሎ ከጨረስ ቤቱ የስራተኛው ነው። እንዲህ እንዲህ አርገህ በጥቅማጥቅም ካስርከው ስራተኛው ጉበኛ አይሆንንም።

ሌላው ደግሞ ሼር ስራተኛውን መብራት ሀይል ማስገባት ነው። ይህ ከሆን መብራት ሀይል ሲያደግ ስራተኛው ተጠቃሚ ስለሚሆን ጉቦ ሳይፈልግ ይስራል።

እንግዲህ እዚህ ላይ ነው የቡዳ ሕዝብ ልኩ የሚታየው የመብራት ሀይል ስራተኞች ይህንን ሁሉ ጥቅም ሲያገኙ አይናቸው ቀይ የሚለብስው ። ስራተኞቹ በድህነት እንዲኖሩ የሚፈልጉት። ለምሳሌ ይህ ኮተቴያም የሚስኪኑን ስራተኛ ቴሌፎን በሕዝብ መድረክ ላይ አወጣው። ይህ ራሱ ወንጅል መሆኑን አያውቅም ወይ ። ስራተኛው ቢገደል ከስራ ቢባረር ተጠያቂው ማነው እራሱ ስልኩን ለጣፊ ።

ምነው ተረሳ እንዴ አንድ ስው ንፁ ነው ። በፍርድቤት ወንጅለኛ እስካልተባለ ድረስ። ነገ አንዱ የአንተን ቤተስቦች ቴሌፎኖች እዚህ ፎረም ላይ ቢለጥፍ ምን ይስማሀል። ብቻ እንዲህ አርገውኛ ብሎ ሁሉም ቢለጥፍስ ትንሽ ስነስርዓት የለም ። አንተ አንዲ ሺህ የማይሞላ ግቦ ከፍለህ ይሆናል ወይ በመቶ ብር ትገላገል የነበረውን ይህ ሁሉ ጣጣ ።

እንደውም መብራት ሀይል በሁሉም ኢትዬዽያዊ ላይ መቶ ብር በመጨመር ስራተኞቹን በሙሉ መካስ አለበት ያለ ስራተኞቹ መብራት ሀይል መብራት ሀይል አይሆንም ። እነዚህ ስራትች እድሉን አግኝተው ወጭ ቢወጡ እኮ ከመቶ ሺህ ዶላር በላይ ይከፈላቸዋል ። በዚህ በ፫ሺህ ደሞዛቸው ምነው ትቀናለህ ።

አንተ አሜሪካ መጥተህ ታክሲ ትነዳለህ ። እሱ ግን መብራት ሀይል ይስራል ። አንተ እንዴት እንደሚቀጠል ብታውቅ ኖሮ እኮ ትቀጥለው ነበር። መብራት ሀይል ስንት ገንዘብ ያፈስ ስበትን ስራተኛ ። ስልክ አስደውለህ ልታሽማቅቅ አትችልም።

ሁሉም ቴሌፎኖች እዚህ ልጅ ጋ የተደወሉት መሀቀብ መጣል አለባት ። ሁለተኛ ኢትየዽያ ውስጥ እንዳይደውሉ። መብራት ሀይል ይሄን ልጅ መከላከል አለበት።

ጉቦ የምታጠፋው መብራት ሀይልን አፍርስ አይደልም። እርግጠኛ ነኝ ለግቦ መፍት ሄ ምንም የለህም ዝም ብለው በደከመ ደሞዛችው ይኑር ከማለት በስተቀር ወይም እኔን ወይኔ ከማለት በስተቀር ። ከታክሲ ነጂ ምንም አልጠብቅምና ግድ የለም መልስ ባይኖርህም ።

ስልክ መደወል ከጀመርን ደግሞ መንግስት ሚሊዬን ስራተኞች አሉት ለሚሊዬኖቹም መደውል ይጠበቅብናል ማለት ነው። ለምን ሁሉም ጉቦኛ ነውና ። እንዳልኩህ ጉቦን የምታጠፋው አብይን በመቀየር አይደለም ሌላ አብይ ቢመጣ ጉቦ አይጠፋም ። ግን ደሞዛቸውን በማስተካከል ጉቦ ይቀንሳል።

አዋ ቡዳ አማራ ከሆንክ አይ ሀገሪቱ አቅም የላትም ትለኛለች ። አቅም ስሌሌላት ነው እኮ በደንብ ስራተኞቹን ከፍለን በደንብ አገልግሎት እናግኝ የምልህ ። ደህ ስለሆንን ግቦ አንችልምና ደሞዛቸው ከፍ ይበል።

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: መብራት ኃይል : እዚህ አገር በጥባጭ ነው! ለምን አይፈርስም? ለምን አይሸጥም? ሕዝቡን እያማረረ እስከመቼ?

Post by Sam Ebalalehu » 25 Mar 2021, 08:50

Ethoash, where does the money come from ? You keep saying pay them good and corruption will no longer. I do not think it is that simple. The corruption culture that I have heard when I was in Addis years ago was pretty much depressing. With the corruption culture prevailing now, it is highly unlikely to make economic progress. Something has to be done about it.

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: መብራት ኃይል : እዚህ አገር በጥባጭ ነው! ለምን አይፈርስም? ለምን አይሸጥም? ሕዝቡን እያማረረ እስከመቼ?

Post by Ethoash » 27 Mar 2021, 06:53

Sam Ebalalehu wrote:
25 Mar 2021, 08:50
Ethoash, where does the money come from ? You keep saying pay them good and corruption will no longer. I do not think it is that simple. The corruption culture that I have heard when I was in Addis years ago was pretty much depressing. With the corruption culture prevailing now, it is highly unlikely to make economic progress. Something has to be done about it.
አቶ ሳም፣

እኔ ለኤርትራኖች ምንም አልመልስም ብዬ ነበር። ለምን ምንም በውስጣዊ ጉዳያችን ስለማያገባቹህ። ግን አንተ ብቻ ስለሆንክ መልስ የስጠኽኝ ብቻ ነው የምመልስልህ መልስ።

አንደኛ በደንብ ካነበብከው ለጉቦ መፍትሄ ብዬ ያቀረብኩትን ። አንድ ቡዳ አማራ ወይም ቀይ ደም ዓይን ኤርትራዊ ይህንን አንተ ያልከውን መልስ ይስጣል ብዬ ነበር ። አንተም እንደፈራሁት ገንዘብ የለንም ። ታድያ ገንዘብ የለንም ብለህ ባርያ ታስተዳደራለህ እንዴ።

ስው ገንዘብ አለው ጉቦ ለመስጠት ግን ገንዘብ የለውም ለዋጋ ጭማሪ።

እንግዲህ ለማስረዳት ያህል የኢትዬዽያ መብራት ሀይል መቶ ሺህ ስራተኞች አሉት እንበል

ክመቶ ሚሊዬን ሕዝባችን ፷ ሚሊዬን የመብራት ሀይል ደንበኛ ነው እንበል ። እንግዲህ በነዚህ ደበኖች ላይ የአንድ ብር ። እየህ የአንድ ብር የዋጋ ጭማሪ ብናረግ ። ለመብራት ሀይሌች የ፷ የስድስት መቶ ብር የደሞዝ ጭማሪ ማረግ እንችላለን ማለት ነው። አሁን ደግሞ አስር ብር ብቻ የዋጋ ጭማሪ ብናረግ ለመብራት ሀይሌት ስራተኞች ፮ሺህ ብር የደሞዝ ጭማሪ ማረግ እንችላለን ማለት ነው። ፫ሺህ ብር ደሞዝተኛ ፱ ሺህ ብር የደሞዝ እድገት አገኘ ማለት ነው ። የኢትዬዽያን ሕዝብ ብዙም ሳንጎዳ ።

ስለዚህ የመብራት ሀይል ደምበኞች በግቦ ምክን ያት ምንም አይነት የተቆራረጠ አገልግሎት አያገኙም። ስራተኛውም ይህንን የደሞዝ ጭማሪ የትም ቢሄድ ስለማያገኘው። ከስራ እንዳይባረር ብርትቶ ይስራል ።

ይህ የደሞዝ ጭማሪ ፺ ዘጠና ከመቶ የነበረውን ጉቦ ወድ ፵ እርባ ከመቶ ያወርደዋል ። ከዚያ መብራት ሀይል ቤት ስርቶ በባለቤትነት በረዝም ግዜ ክፍያ የሚኖሩበትን ቤት ሲስጣቸው አንድ ሚሊዬን ብር ስጣቸው ማለት ነው። ስለዚህ ከመብራት ሀይል ከተባረሩ የቤት ክራያቸውን ወይም ሞርጌጃቸውን መክፈል ስለማይችሉ ጎመን በጤና ብለው ይስራሉ።

ይህ ደግሞ መብራት ሀይል ቤቱን በመቶ ሺህ ብር ሊስራው ይችላል። በብዛት ስለሚስራ ፣ እና መንግስት ቀረጥ ስለማይጥልበት ቤቱ በጥራት ግን በቅናሽ መስራት ይችላል ። ግን ገበያ ላይ ቤቶቹ ሚሊዬን ብር ስለሚያወጡ ስራተኛውን አደብ ማስያዝ ይቻላል። ሌላው ደግሞ ስራተኛው ከፈለግ ቤቱን ከአስር አመት በኋላ መሽጥ ይችላል ካልከው ቤቱን ለመክፈል ፴ አመት ቢፈጀበት ገንዘብ ማግኘት ከፈለገ በግዜ መሽጥ ይችላል። ከአስር አመት በኋላ ቤቱ ሁለት ሚሊዬን ብር ከደረስ ስራተኛው ሚሊዬነር ሆነ ማለት ነው አንድ ሚሊዬንን ለባንክ አንድ ሚሊዬኑን ለኪሱ አርጎ በጡረታ ወይ በስራ ቅየራ ሌላ ቦታ ከሄደ ቤቱን ሽጦ መሄድ ይችላል ። ከአምስት አመት በኋላ ምክን ያት ካለው።

ይህ የስራተኞች ጥቅማ ጥቅም አንተ ከምት ስጠው የመቶ ብር ጉቦ በጣም የላቀ ስለሆነ በተዓምርም ስራውን ማጣት ስለማይፈልግ ። ስራውን አክብሮ የስራል ማለት ነው። አሁን ግን ብታባርረው በነጋታው ስራ ያገኛል። ቤት የሚገነቡ ግለስቦች ኤሌትሪሻን ስለሚፈልጉ እንዚህን ስራተኞች አይናቸው ሳያሹ ደሞዝ ጨምረው ይቀጥሩዋቸዋል ። ስለዚህ አሁን ባለበት የመብራት ሀይል ስራተኛ ምንም አይስጉም ቢባረሩም ባይባረሩም የስራ መልቀቅያቸውን ተቀብለው ወድ ግሉ መስራቤት ይቀላቀላሉ።

ይህ ቤት ስርቶ ማከራየት ብቻ ፵ አርባ ከመቶ የነበረውን ጉቦ ወድ ፳ ሃያ ከመቶ ያወርደዋል ። የህክምና የህይወት ዋስትና በሞት ስራተኛው ቢለይ ቤቱን በነፃ ለሚስቱና ለልጆቹ የመስጠት ፖሊሲ የመሳስሉት ካሉ ጉቦውን ወድ ከ፳ በመቶ ወድ ፫ በመቶ ያወርደዋል ። ማለት ነው።

ይህ ብቻ አይደለም ስራተኞቹን ብዙ ብዙ ደሞዝ ጭማሪ ማረግ ይቻላል ። በኔ ግምት መቶ ሺህ ስራተኛ መብራት ሀይል አያስፈልገውም እምሳ ሺህ ስራተኛ ይበቀዋል ። ይህ ማለት ትንሽ ቴክኖለጂ ከተጠቀሙ በብዛት ስራተኛ መቀነስ ይችላሉ።

ለምሳሌ የመብራት ሀይልን ፖል ለመትከል ሙሉ በሙሉ የስው ሀይል ነው የሚጠቀሙት ነገር ግን ትንሽ ቴክኖለጂ ። የሚልዬን ብር መኪና ይግዙ አይደለም ትንሽ ቴክኖለጂ ቢጠቀሙ የመብራት ሀይሉን ፖል በቀላሉ መትከል ይችላሉ በፍጥነትም መትከል ይችላሉ ይህ ትንሽ ቴክኖለጂ የምልህ መኪና በማይገባበት ቦታ በተራራማ ቦታ ሄደህ ለመትከል የሚረዳህ መሳሪያ ነው። የመስራቤቱን ስራ በሙሉ በድጅታል ቢቀየር የመቶ ስራተኛ ስራ በጥቂት ስራተኞች ይስራል ይህ ግን እኔ የማልደግፈው ነው ። ለቀሩት ስራተኞች ሌላ ተቀያሪ ስራ እስካልተገኘላቸው ደረስ ይህንም ችግር ለመቅረፍ መብራት ሀይል ብዙ ዜዴ መጠቀም ይችላል ይህ በሌላ ግዜ ይህንን ረጅም መልስ እንኩዋን በአግባቡ አንብበህ የምተረዳው ስላልመስለኝ በዚህ ላቁም። ምህራፍ ሁለት በሌላ ግዜ

Post Reply