Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42464
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ቀንድ፣ አፍሪካ፣ ምዕራብ ኤሲያ፣ ምስራቅ ኤሲያ፣ አውሮፓና አሜሪካ

Post by Horus » 28 Jan 2021, 04:06

ይህን የምጽፈው ምንም ለማለት አይደለም ። ብቻ አንድ ነገር ለመናገር ነው።

አንድ፣ ወያኔን ፈጥረው ረድተው አዲስ አበባ እንዲገባ ያደረጉት ኤርትራዊያን አሁን መልሰው እያጠፉት ነው።

ሁለት፣ መለስን በቀይ ምንጣፍ ያሞናሞኑት እነ ሳይድ ባሬ ጠፍተዋል፣ የዚያኔ ዘመን ሱማሌ ጠፍታለች ።

ሶስት፣ የሻአቢያ ደጋፊው ሳዳም ሁሴን እና ሌላው አረብ አሁን የለም ።

አራት፣ ሱዳን ተከፋፍላለች፣ ገና ትከፋፈላለች ።

አምስት፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደ ገና በፍቅር ሽር ጉድ እያሉ ነው።

ስድስት፣ ኢትዮጵያን በዘር የከፋፈሉት ግብጽ፣ እንግሊዝና አሜሪካ ናቸው። ዛሬም ኢትዮጵያ አለች ።

ሰባት፣ አረቦች ኢትዮጵያን የርካሽ ሰው ጉልበት፣ የምግብና የዉሃ ምንጭ ለማድረግ እየተፎካከሩ ነው።

ስምንት፣ እስራኤል ኢትዮጵያን ካረቦች ጋር በምታደርገው ሽኩቻ እንደ ጠጠር ትጠቀምብናለች ።

ዘጠኝ፣ እንግሊዝና አውሮፓ የቅኝ ረዕዮታቸው እንዳይሻር ኢትዮጵያ የነሱ ተመጽዋች ዲፔንደንት ሆና እንድትቀር ይሰራሉ ። ሙሉ ትኩረታቸው ትግሬ ተራበ ሲባል መጮህ ነው።

አስር፣ አሜሪካ አንድም ቀን ኢትዮጵያ እንድታድግ፣ ታላቅ እንድትሆን ፈቅደው አያውቁም፣ ዎያኔን ረድተው ደግፈው በኛ ላይ የጫኑ አሜሪካኖች ናቸው።

አስራ አንድ፣ አሁን ቻይና ያፍሪካ የጅ አዙር ቅኝ ገዥ ስለሆች እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስለተቆጣጠረች አሜሪካኖች ግራ ተጋብተዋል ። በትግሬ ረሃብ ሰበብ አሁንም መሰሪ ጠላትነታቸውን ይቀጥላሉ።

አስራ ሁለት፣ ቻይና በቆሻሻ ሸቀጥና የሌብነት ብድራቸው ኢትዮጵያን ማድማታቸው ይቀጥላል።

አስራ ሶስት፣ ግን የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከ30 አመት በፊቱ እጅግ እግጅ የሚለያት 5 ሚሊዮን ዲያስፕራ ኢትዮጵያዊ በ180 አገሮች ተዘርቶ ባመት ከ6 እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር ሬሚታንስ ወደ ኢትዮጵያ ይልካል፤ ኢትዮጵያን ይጠብቃል ፣ አለ የተባለ እውቀትና ቴክኖሎጂ ወደ አገር ቤት ያስገባል ።

አስራ አራት፣ የዛሬቱ ኢትዮጵያ እንደ ድሮ ማንም ቅኝ ገዥ በዶላር የሚያስፈራራት አገር አይደለችም።

አስራ አምስት፣ ግን ግን ግን ኢትዮጵያ የዘር ፌዴሬዝን ካላፈረሰች ያረብና የቅኝ ገዦች መቀለጃ ሆና ትቀራለች!

አበቃሁ !

Last edited by Horus on 28 Jan 2021, 17:05, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42464
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ቀንድ፣ አፍሪካ፣ ምዕራብ ኤሲያ፣ ምስራቅ ኤሲያ፣ አውሮፓና አሜሪካ

Post by Horus » 28 Jan 2021, 16:54

ያሜሪካ ፖሊሲ ያው የረጀ ብላ ብላ ነው። ኢትዮጵያ ዎያኔ የሚባል የኢፔሪያሊስቶች ፍጡር አፈር ተድሜ አግብታ እንዳይነሳይ ቀብራለች። አሁን አሜሪካና አውሮፓ ለትግሬ ስንዴና አስፕሪን ማደል ከፈለጉ በኢትዮጵያ መንግስት ተቆጣጣሪነት ገብተው ያድሉ። ያው አገራችንን ለመሰለል ደሞ ለመሸረብ ነው። ይሞክሩት ። ስለሆነም አቢይ ቶሎቶል ዎያኔን ፊዚካሊ ሙሉ በሙሉ መደምሰስና ማጥፋት ነው ያለበት ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አንድ ሰው መቆም ብቻ መልሱ !! አድዋ በአል ደርሷልና ሰብሰብ ሰብሰብ እንበል !!!!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ቀንድ፣ አፍሪካ፣ ምዕራብ ኤሲያ፣ ምስራቅ ኤሲያ፣ አውሮፓና አሜሪካ

Post by Abe Abraham » 28 Jan 2021, 18:01

Horus wrote:
28 Jan 2021, 04:06
ይህን የምጽፈው ምንም ለማለት አይደለም ። ብቻ አንድ ነገር ለመናገር ነው።

አንድ፣ ወያኔን ፈጥረው ረድተው አዲስ አበባ እንዲገባ ያደረጉት ኤርትራዊያን አሁን መልሰው እያጠፉት ነው።

ሁለት፣ መለስን በቀይ ምንጣፍ ያሞናሞኑት እነ ሳይድ ባሬ ጠፍተዋል፣ የዚያኔ ዘመን ሱማሌ ጠፍታለች ።

ሶስት፣ የሻአቢያ ደጋፊው ሳዳም ሁሴን እና ሌላው አረብ አሁን የለም ።

አራት፣ ሱዳን ተከፋፍላለች፣ ገና ትከፋፈላለች ።

አምስት፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደ ገና በፍቅር ሽር ጉድ እያሉ ነው።

ስድስት፣ ኢትዮጵያን በዘር የከፋፈሉት ግብጽ፣ እንግሊዝና አሜሪካ ናቸው። ዛሬም ኢትዮጵያ አለች ።

ሰባት፣ አረቦች ኢትዮጵያን የርካሽ ሰው ጉልበት፣ የምግብና የዉሃ ምንጭ ለማድረግ እየተፎካከሩ ነው።

ስምንት፣ እስራኤል ኢትዮጵያን ካረቦች ጋር በምታደርገው ሽኩቻ እንደ ጠጠር ትጠቀምብናለች ።

ዘጠኝ፣ እንግሊዝና አውሮፓ የቅኝ ረዕዮታቸው እንዳይሻር ኢትዮጵያ የነሱ ተመጽዋች ዲፔንደንት ሆና እንድትቀር ይሰራሉ ። ሙሉ ትኩረታቸው ትግሬ ተራበ ሲባል መጮህ ነው።

አስር፣ አሜሪካ አንድም ቀን ኢትዮጵያ እንድታድግ፣ ታላቅ እንድትሆን ፈቅደው አያውቁም፣ ዎያኔን ረድተው ደግፈው በኛ ላይ የጫኑ አሜሪካኖች ናቸው።

አስራ አንድ፣ አሁን ቻይና ያፍሪካ የጅ አዙር ቅኝ ገዥ ስለሆች እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስለተቆጣጠረች አሜሪካኖች ግራ ተጋብተዋል ። በትግሬ ረሃብ ሰበብ አሁንም መሰሪ ጠላትነታቸውን ይቀጥላሉ።

አስራ ሁለት፣ ቻይና በቆሻሻ ሸቀጥና የሌብነት ብድራቸው ኢትዮጵያን ማድማታቸው ይቀጥላል።

አስራ ሶስት፣ ግን የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከ30 አመት በፊቱ እጅግ እግጅ የሚለያት 5 ሚሊዮን ዲያስፕራ ኢትዮጵያዊ በ180 አገሮች ተዘርቶ ባመት ከ6 እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር ሬሚታንስ ወደ ኢትዮጵያ ይልካል፤ ኢትዮጵያን ይጠብቃል ፣ አለ የተባለ እውቀትና ቴክኖሎጂ ወደ አገር ቤት ያስገባል ።

አስራ አራት፣ የዛሬቱ ኢትዮጵያ እንደ ድሮ ማንም ቅኝ ገዥ በዶላር የሚያስፈራራት አገር አይደለችም።

አስራ አምስት፣ ግን ግን ግን ኢትዮጵያ የዘር ፌዴሬዝን ካላፈረሰች ያረብና የቅኝ ገዦች መቀለጃ ሆና ትቀራለች!

አበቃሁ !

ወንድሜ ሆረሰ

እኔ ሻብያ ቤተ-ሰብየ ስለ ሆነ በደንብ ነው የማውቀው ። ጀብሃ በሃይማኖትና በኣረባዊነት ትነግድ ስለ ነበረች ትናንሽ እርዳታዎች - የማያጠግብና ለረሃብ የማያጋልጥ - ከኣረብ ኣገሮች ታገኝ ነበር ። ሻብያ ግን ሶሻሊስትና ክርስትያን ነው እየተባለ ከኣረብ ኣገሮች ምንም እርዳታ ኣያገኝም ነበር ብቻ ሳይሆን ብዙ ተጻብኦም ይገጥመው ነበር ።

ኣንድ ግዜ ሳዑዲያ ህዝባዊ ግንባር ኤርትራን ነጻ ለማውጣት ተቃርቦዋል የሚል ስጋት ስለነበራት በቀይ-ባሕር ከነሙሉ መሳርያዎችና ጥይቶች ( በየኤርትራ ህዝብ ገንዘብ የተገዛ ) ጭና ትጓዝ የነበረች መርከባችን ሕግና ስርዓት በሌለበት ኣገባብ ወደ ጅዳ ( ሳዑዲያ) እንድትጓዝ ኣድርገው ንብረታችን ዘረፉት ። ሻዕብያ ( ህዝባዊ ግንባር ) ከማን እርዳታ ታገኝ እንደነበረች ለማወቅ የሚከተለውን የጓድ መንግስቱ ሃይለ-ማርያም ንግግር ልትመለከት በትህትና እጋብዝሃለሁ ፥

Post Reply