Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40229
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኤትኖክራሲ፣ የጎሳ አገዛዝ ስርዓት በጭለማ ውስጥ ያሉ እንሰሶች ሚባክኑበት ተረት ነው

Post by Horus » 17 Jun 2020, 03:32


ያገራችህን ፖለቲከኞች ከተራ ጠንቋይ አይሻሉም።

በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የለም ።

ፌዴራል መንግስት የለም ።

የጎሳ ጽንሰ ሃሳብ ለፖለቲካ ስርዓት ማደራጃ ሊውል አይችልም፣ በፍጹም ።

ያለው ተቀያያሪ ተረኛ የጎሳ አምባ ገነንነት ነው።

ትላንት ትግሬ ነበር ።

ዛሬ ኦሮሞ ነው።

ቀጥሎ አማራ ይተካል።

በየኢትዮጵያ የሃይል ሚዛን የሚባል ነገር የለም ።

ያለው የቀውስ ትርምስ እና የቀውስ መሸጋሸግ ነው።

ፖለቲካውን የሚሰሩት አካላት የፖለቲካ ፍጥረቶች አይደሉም ። ዘር የፖለቲካ ፍጥረት አይደለም ።

ለሚቀጥለው ሺ አመት ሲገለባበጡ ይኖራሉ እንጂ በኢትዮጵያ ሚዛን ያለው ፣ የሚሰራ ፣ ዘመናዊ
ፋይዳዊ የፖለቲካ ሰርዓት እንኳንስ አቢይ እግዚአብሄርም ሊያመጣ አይችልም። ፖለቲካ በዘር
ስለማይደራጅ !!

ስለዚህ የኢትዮጵያ ፖለቲከኛ መደብ በእውነት በጭለማ ውስጥ ያለ አሳዛኝ ተምሮ የእውቀት ብርሃን
የተነፈገ ትራጂክ፣ ትራጂች ቡድን ነው። ይህ አብይንም ጨምሮ ነው።

እነዚህ አየሩን የሚያጣብቡት ንቃተ እውቀት የሌላቸው ለፋፊና ሰባኪዎች ሁሉ ምንም ነገር ማየት እንደ
ማይችሉ፣ እንዳልቻሉ ማሰብ የተሳናቸው የራሳቸውን ቅዠት የሚያምኑ ጠንቋዮች ናቸው።

ኢትዮጵጵያ ምትገፋው፣ የምትባክነው በጎሳ ቀውስ ትርምስ ነው። መንግስት የለም ። የፖለቲካ ሰርዓት የለም ።

ወደፊትም አይኖርም ። ጎሳዎች በጎሳ ተደራጅተው ፋይዳዊ ፣ የጸና ሰርዓት አቁመው አያቁም ።

ዛሬ ባለ ተራው ኦሮሞ ስለሆነ ወይ አቢይ የሚባል አፈ ጮሌ ስለመጣ የሳይንስ ሕግ፣ የተፈጥሮ ሕግ ራሱን
አይለውጥም ።

የዛሬ ተረኛ የዘር ባለስልጣኖች ታምሰው ታምሰው ልክ እንደ ዎያኔ መድረኩን ይለቃሉ ።

በኢትዮጵያ እውነተኛ የፖለቲካ ሳይንቲስት ገና አልተወለደም ።

ኤትኖክራሲ፣ ማለትም የዘር አገዛዝ ስርዓት ሺ ግዜ ፓርቲና የፖለቲካ መሃይም መንጋ ቢዘፍንለት
ሊዘምን በፍጹም አይችልም ። ኤትኖክራሲ ፍጻሜው ስርዓት ሳይሆን እልቂት ስለሆነ ።

ያ እውነተኛ ፖለቲከኛ ሲወለድ አለ ምንም መሽኮርመም እውነቱን ለሕዝቡ ይነግራል ፤ የጎሳ ሴራ አገር
ስለማያቆም እንዲፈርስ ሕዝቡን ያስነሳል ።

ያ ነው ገና የሚወለደው የኢትዮጵያ እውነተኛ ዘመናዊ ሳይንሳዊ መሪ !!

የቀረው ሁሉ የዘር ፖለቲካ ስልጣን ነጋዴ ነው ።

ይህ አቢይንም ተቃዋሚ ተብዬ ሺ እልፍ ፋይዳቢስ ፓርቲዎችንም ያካትታል ።

Last edited by Horus on 17 Jun 2020, 14:26, edited 2 times in total.







Horus
Senior Member+
Posts: 40229
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኤትኖክራሲ፣ የጎሳ አገዛዝ ስርዓት በጭለማ ውስጥ ያሉ እንሰሶች ሚባክኑበት ተረት ነው

Post by Horus » 17 Jun 2020, 14:04

ያቤሎ፣

አንተን ማስተማሪያ ግዜ የለኝም። አንተ በካልቸር ድርጅት፣ በፖልቲካ ድርጅት፣ በሶሺያ ድርጅት፣ በኢኮኖሚ ድርጅቶች መሃል ያሉትን ልዩነቶች ሊገባህ የሚያስችል አንጎል የተሰጠህ ሰው ሳላልኮንክ፤ አንተ በመሬትና በካርታው፣ በሪያሊቲና በሲምቦሉ፣ በስዕልና በፋክት፣ በድራማና በእውነታ መሃል ያሉትን ልዩነቶች ለማወቅ የሚያስችል አይምሮ የተሰጠህ ሰው ሳላልኮንክ ከኔ ጋር ግዜህን አታባክን ።

ይህ ሃረግ ላንተ መሰል ደናቁርት የተጻፈ ሳይሆን የፖለቲካ ሳይንስ ምን እንደሆነ ለሚገነዘቡት ነው። ያንተ እውቀት ካለበት፣ ያንተ ግንዛቤ ከተመደበበት ተራ ወይም ካታጎሪ አትውጣ ። እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃላት መፍለጥ አልወድም !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 40229
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኤትኖክራሲ፣ የጎሳ አገዛዝ ስርዓት በጭለማ ውስጥ ያሉ እንሰሶች ሚባክኑበት ተረት ነው

Post by Horus » 17 Jun 2020, 14:48

ኦሮሙማ፤ ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ ለማድረግ የተሰራ አጀንዳ፤


Horus
Senior Member+
Posts: 40229
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኤትኖክራሲ፣ የጎሳ አገዛዝ ስርዓት በጭለማ ውስጥ ያሉ እንሰሶች ሚባክኑበት ተረት ነው

Post by Horus » 18 Jun 2020, 01:01

እኔ ሆረስ እባላለሁ፣ ቃላት መሰንጠቅ አይመቸኝም።

የኦሮሞ ተስፋፊነት እና ሄጂሞኒ ምኞት በሉት ቅዠት እንደ 16ኝው ዘመን ይሳካል ብለው ሚያልሙት ወደ 21ኛው ዘመን ይግቡ ። አይሆንምና ።

እንዲያውም ይህ የተዝረከረከ የኦሮሞ ክልል ጂኦግራፊ በአራት ራስ ገዝ ክፍለ አገር መመደብ ግድ ይላል። እነሱም ሰሜን ኦሮሞ፣ ምስራቅ ኦሮሞ ፣ ደቡብ እና መ ዕራብ ኦሮሞ ናቸው።

ከዚያ ባለፈ፤
በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ፣ ኢትዮጵያ እንደ አገር መኖሯን የሚሹ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ ጎሳዎች፣ ብሄረሰቦች ከየትም ክልል ሆኑ አሁን አንድ አገር አቀፍ ትብብር እና መናበብ መጀመር አለባቸው ፣ ባስችሀኳይ ።

ለነገሩ፣
ፖለቲካ ልክ እንደ ካራምቦላ (ቢሊያርድ) የጠረጴዛ ጨዋታ ነው። በተለይ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ አንድ ጎሳ አንድ ነገር ሲያደርግ፣ አንድ ጎሳ አንድ ነገር ሲሆን የቅሩት ጎሳዎች ሁሉም ይነቃነቃሉ፣ ይናጋሉ፣ ይታመሳሉ ። ይህ ሕግ ነው ።

ለምሳሌ ዎያኔን እንመልከት ። እነመልስ ልክ ስልጣን ላይ እንደ ወጡ ለመስፋፋት የነበራቸውን ህልም ስራ ላይ ማዋል ጀመሩ፣ በወልቃይት፣ በሰሜን ወሎ ወዘተ።

ዛሬ በዚያ ጦስ ከአማራ ጋር ጦርነት አፋፍ ደርሰዋል ።

ኦሮሞች ከ30 ጎሳዎች ጋር ይዋሰናሉ ። በአሁን ወዊቅት ቢያንስ ካ10 ብሄረ ሰቦች ጋር ጠብ ውስጥ ናቸው። የወደ ፊቱን አስከፊ ጦርነቶች ለመገመት ይቻላል።

በዚህኛው የኦሮሞ መፋፋት የሚሆነው የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች ነው የሚሆነው ።

ኤትኖክራሲ መድረሻ ፍጻሜው ጦርነትና እልቂት ነው ። ይህ ሳይንስ ነው፣ የሚሆነውም ይህ ነው !!


Post Reply