በነገራችን ላይ ለኤርምያስ መፈታት የእኔም አስተዋትጽኦ ነበረበት:: መንግስት ያለምክንያት ያስራል: ፍታ ሲሉት ይፈታል:: እስክንድር ነጋን እንዲፈታ ወያኔን ስወተውት ነበር::
ህዝቡ ራሱ ችግር ያለበት ሕዝብ ነው: በመንጋ የሚነዳ ሌባ ነው እያሉ ቢያስችግሩት : ኤርምያስ እነዚህ ሰዎች ጤነኞች ናቸው ወይ ነው ያለው:: አዎ ሕዝብ ማመዛዘን መቻል አለበት :: እንድ እንስሳ መመራት የለበትም::
ወደ ዋናው ጉዳይ ስንገባ: ኤርምያስ አነጋጋሪ ሰው ነው:: ይህን ረጅም ሰዓት ሙሉውን ተከታትየዋለሁ:: ምናልባት ሁሉን እዚህ ልፅፎ ለመጨረስ ላይበቃ ይችላል: ግን ዋና ዋናውን እጠቃቅሳለሁ::