Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
( ͡° ͜ʖ ͡°)
Member
Posts: 2312
Joined: 11 Jan 2020, 21:22

NEVER FORGET: "ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በትግርኛ እየተነጋገሩ ቀጠቀጡኝ።" -- አንዳርጋቸው ፅጌ

Post by ( ͡° ͜ʖ ͡°) » 14 Mar 2020, 16:26

አንዳርጋቸው ፅጌ ባንድ ወቅት ሚነሶታ ላይ ባደረገው ንግግር እንዲህ ብሎ ገልፆ ነበር።

"....... በ2005 ሰኔ ወር ላይ ትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ያሉበት የወያኔ አፋኝ ቡድን አጥር ዘሎ ወደ ግቢያችን ገባ። ግቢው ዉስጥ በሚኖሩ ሰዎችና በአባቴ ፊትም አንዱ በዱላ ጀርባየን መታኝ። ተዳባዳቢው ወጣት፥ "ለምን ትመታኛለህ? የጠየቃችሁኝን አላደርግም አላልኩም" ስል ጠየቅሁት። ወጣቱ 15 ሰዎች እየሰሙት፥ "ደብድቡት! የሚል ትእዛዝ ተሰጥቶናል" ሲል መለሰ።

ዱላው በዚህ አላበቃም። አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በትግርኛ እየተነጋገሩ ቀጠቀጡኝ። የራሳቸው ዘር እየቀጠቀጠ የመግዛት መብት እንዳለው፥ ለዚያ መብት ያበቃቸው የተለየ ጀግንነት የተላበሱ መሆናቸው በድንፋታ እየተናገሩ ነበር ዱላው የሚያዘንቡብኝ። በደህና ቀን የተማርኳት ትግርኛ ባለጌ ስድባቸውን ለመስማት አስቻለቺኝ። የሰማሁትን ከሰማሁ በሁዋላ ትግርኛ የማልሰማ ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር።

አማራ ብለው የሚጠሩት ዘር በተለይ፣ እጅግ አስፀያፊ፣ እዚህ ለመድገም የሚቀፍ ስድብ እየተሳደቡ ዱላና ርግጫ አወረዱብኝ። ግማሽ ፊቴን በሰደፍ አፍርሰው ኮማ ውስጥ ጨምረውኝ፥ ጭቃ መሬት ላይ ጥለዉኝ ሄዱ። በዘር ጥላቻ የተመሰረተ ብልግና የሞላው ድርጊታቸውን የፈጸሙት ከ 700 አስከ 800 የሚሆን እስረኛ ፊት ነው።

የደበደቡኝ የቅንጅት ደጋፊ በመሆኔና የኔን ቅስምም ለመስበር ነበር። በድብደባው የተነሳ ስንት ሰኣት ወይም ደቂቃ ኮማ ዉስጥ እንደቆየሁ አላውቅም። ከኮማ እንደወጣሁ ያገኘሁት ማንነቴ ግን በፊት ከነበረኝ ማንነቴ የተለየ ነበር። ከደብዳቢዎቹ ዘር ጋር ለተገናኘ ማንኛዉም ሰው ከፍተኛ ጥላቻና ምሬት ልቤን ሞልቶ አገኘሁት። ከሚደበድቡኝ ስድስት የመለስ ዜናዊ አሽከሮች በላይ የሚሻገር ከሰዎቹ ትግሬነት ጋር የተሳሰረ፣ ለዘራቸው በሙሉ መጥፎ ስሜት እንዲሰማኝ ያደረገ፣ ጥላቻ ስብእናዬን እንደ አሲድ ሲበላው አገኘሁት። በጣም የሚያስደነግጥ ስሜት ነበር።

..... ሌላው የኔ አይነት የህሊና ወቃሽ የሌለው ተመሳሳይ በደል ሲደርስበት ምን ሊያስብ እንደሚችል ገምቱት። በመለስ ዜናዊ ወታደሮች ቤቱ የተቃጠለው፣ ሚስቱንና ወጣት ልጁን የተደፈረው፣ የተዘረፈው፣ የተዋረደው፣ በጥቅሉ የዘር ማጥፋት እርምጃ የተወሰደበት መላው የሃገሪቱ ህዝብ ምን ይሰማዋል?....."

Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10117
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: NEVER FORGET: "ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በትግርኛ እየተነጋገሩ ቀጠቀጡኝ።" -- አንዳርጋቸው ፅጌ

Post by Digital Weyane » 14 Mar 2020, 16:43

አዎ ኡየሰደብን ደበደብነው፣ ታድያ ሙን ይጠበስ ? :roll:


Post Reply