Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12654
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ኢትዮጵያዊ ነን” በሚለው ብዙኃንና “ኢትዮጵያዊ አይደለንም” በሚሉ ኦነጋውያን መካከል የሚካሄደው “አገራዊ ምክክር ጉባዔ” ( በአቻምየለህ ታምሩ የተፃፈ)

Post by MINILIK SALSAWI » 15 Aug 2026, 23:35

ኢትዮጵያዊ ነን” በሚለው ብዙኃንና “ኢትዮጵያዊ አይደለንም” በሚሉ ኦነጋውያን መካከል የሚካሄደው “አገራዊ ምክክር ጉባዔ” በአቻምየለህ ታምሩ የተፃፈ

ቢቢሲ ስለ ምክክር ኮሚሽን ተብዮው መሰንበቻ ዛሬ ያወጣው ዘገባ፣ መድረኩን በየዋህነት “አገራዊ ምክክር” የሚደረግበት ገለልተኛ መድረክ ነው ብለው ለሚያምኑት ሁሉ፣ በውስጡ እየተፈጸመ ያለውን ዐቢይ አሕመድ መር ኦነጋዊ ሸፍጥ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
ዘገባው እንደሚያሳየው፣ ምክክር ተብዮው እየተደረገ ያለው “ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን፤ አዲስ አበባም የኢትዮጵያ ዋና ከተማና፣ በአስተዳደሯም ራሷን የቻለች የሁሉም ኢትዮጵያውያን የፌዴራል ከተማ ትሁን” በሚሉ ብዙኃን ኢትዮጵያውያን እና “አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሳትሆን የኦሮሞ ብቻ ናት፤ ስለሆነም የኦሮሚያ አካል መሆን አለባት” የሚል አቋም በያዙ፣ ኢትዮጵያዊ አይደለንም በሚሉ ኦነጋውያን መካከል ነው። በእነዚህ ሁለት አቋሞች መካከል ያለው ልዩነት ተራ የሐሳብ ልዩነት ሳይሆን፣ መሠረታዊ የሀገር ማንነት ጥያቄ ነው።
ከሁሉም ይበልጥ አስገራሚው ደግሞ፣ “አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሳትሆን የኦሮሞ ብቻ ናት፤ ስለሆነም የኦሮሚያ አካል መሆን አለባት” የሚል አቋም የሚያራምዱትን፣ ኢትዮጵያዊ አይደለንም የሚሉትን የኦነጋውያን ቡድን የሚመራው፣ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሰየመው ዐቢይ አሕመድ የሚባለው ጉድ መሆኑ ነው።
በሌላው ዓለም፣ የአንድ ሀገር መሪ ዋናው ተግባር የዚያችን ሀገር የጋራ መሠረት፣ የጋራ ዋና ከተማና የጋራ ማንነት ማጠናከር ነው። ዐቢይ አሕመድ የሚባለው ኦነጋዊ ጉድ ግን፣ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ተሰይሞ የሚገዘግዛትን አገር “አላውቅሽም” ብሎ፣ “ኢትዮጵያዊ አይደለንም፤ አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሳትሆን የኦሮሞ ብቻ ናት፤ ስለሆነም የኦሮሚያ አካል መሆን አለባት” የሚለውን ኦነጋዊ ቡድን ይመራል።
መስፍን አርአያ የሚባለው የዐቢይ አሕመድ ከዳም በተደጋጋሚ ኮሚሽኑ “ተመካካሪዎች የሚመካከሩበት መድረክ ነው” ሲል ይሰማል። ይህ ከሆነ ታዲያ፣ “አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ ከተማ መሆኗን ዕውቅና ይሰጣት” የሚለው ጉዳይ፣ ከታች ጀምሮ በተካሄደው ምክክር ተብዮው ያልተነሳ፣ ያልተወያዩበትና “ተመካካሪዎቹ” ያልጠየቁት ጉዳይ ሆኖ ሳለ፣ ድንገት “ከበላይ የመጣ ሐሳብ” ተብሎ በቃለ ጉባኤ ውስጥ እንዴት እንዲገባ ተደረገ?
በእውነቱ ይህ ብቻ የምክክር ተብዮውን ኦነጋዊ ማጭበርበሪያ መሆኑን ለማሳየት ከበቂ በላይ ነው። ከታች ያልተነሳን ጉዳይ ዐቢይ አሕመድ ከላይ ስላወረደው ብቻ፣ ተመካካሪዎቹ ተብዮዎች ያልጠየቁትን እንደጠየቁ አስመስሎ፣ ያልተወያዩበትን እንደተወያዩበት አድርጎ በቃለ ጉባኤ ማስፈር ምክክር አይደለም። ይህ አብነት የሚያሳየው ምክክር ኮሚሽን ተብዮው ምድረካ ኦነጋዊ የማይጠረቃ ፍላጎትን በሕዝብ ስም ለማስፈጸም የተዘረጋ ኦነጋዊ ማጭበርበሪያ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ የተናገርነውን የሚያረጋግጥ ብቻ ነው።
የነ ዐቢይ አሕመድ ኦነጋዊ ቲያትር በዚህ ብቻ አያበቃም። አብዛኞቹ “ተመካካሪዎች” አዲስ አበባ ራሷን የቻለች የፌዴራል ከተማ ትሁን ሲሉ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ የኦሮሚያ ትሁን ማለታቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል። ይህ እውነታ “አብዛኞቹ እንዲህ አሉ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ እንዲህ አሉ” ተብሎ በቃለ ጉባኤ እንዲሰፍር ሲባል ግን፣ “አብዛኞቹ” እና “የተወሰኑ” የሚሉት ቃላት እንዲጠፉና ሁለቱም “አማራጭ አንድ፣ አማራጭ ሁለት” ተብለው እንዲመዘገቡ ተደርጓል።
ይህ ተራ የቃላት ምርጫ አይደለም። ይህ ብዙኃኑን ከቃለ ጉባኤ ላይ የማጥፋት፣ ጥቂቶችን ወደ ብዙኃን ደረጃ የማሳደግ፣ እውነተኛውን የድምፅ ሚዛን ደብቆ የጥቂቶቹን ፍላጎት ሕዝባዊ አማራጭ አስመስሎ የማቅረብ ኦነጋዊ አሻጥር ነው።
ቁጥርን አጥፍቶ፣ የብዙኃኑንና የጥቂቶቹን ልዩነት ደብቆ፣ ሁለቱንም እኩል “አማራጭ” ብሎ መመዝገብ እውነታን መዝግቦ ማስቀመጥ አይደለም፤ እውነታን ቀይሮ ለተፈለገው ፖለቲካዊ ውጤት ማመቻቸት ነው። መስፍን አርአያ “ሁሉም ነገር በቃለ ጉባኤ ተይዟል” የሚለን ሆዳም ስለኾነ እንጂ ቁጥር እየተደበቀ፣ የብዙኃኑና የጥቂቶቹ ልዩነት እየተፋቀ፣ ሁለቱ እኩል አማራጭ እየተደረጉ ከተጻፈ፣ የእውነታ መዝገብ ሳይሆን እውነታ የተጣመመበት ድሪቶ መሆኑ ጠፍቶት አይደለም።
ከዚህ በተጨማሪ፣ ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ መሠረት፣ “አጠናቃሪዎች” የተባሉት ሰዎች ራሳቸው እንደ ተመካካሪ ሆነው ኦነጋዊ ሐሳብ እንደሚሰጡ፣ “ይህ መሆን አለበት” ብለው እንደሚከራከሩ መስፍን አርአያ ራሱ አምኗል። ኦነጋዊ ፍላጎታቸውን በተመካካሪው ላይ እንዲጭኑ የተሰማሩ ኦነጋውያንን መስፍን አርአያ የሚባለው ጉድ ግን እንደ ባለሙያ ነው የሚቆጥራቸው።
የኦሮሞ ባለሥልጣናት በአካልና በስልክ ጭምር ጫና ለመፍጠርና ጣልቃ ለመግባት ሞክረዋል የሚል አቤቱታ በተሳታፊው ሁሉ ቀርቧል። ከታች ያልተነሳ አጀንዳ “ከበላይ” እየወረደ፣ አጠናቃሪዎች ከአጠናቃሪነት ወጥተው ተከራካሪ እየሆኑ፣ በባለሙያነት ስም ኦነጋዊ ፍላጎትን እየጫኑ፣ ባለሥልጣናትም ጫና ያደርጋሉ የሚል ቅሬታ እየቀረበበት ያለው የመስፍን አርአያ ኮሚሽን አሁን መጠየቅ ያለበት “ሂደቱ ችግር አለበት ወይ?” የሚል ሳይሆን፣ “ከዚህ ውስጥ ምክክር ሊባል የሚችል የቀረው ምንድን ነው?” የሚል ነው።
ይህ ሁሉ አንድ ላይ ሲታይ፣ ምክክር ኮሚሽን ተብዮው የሕዝብን ፍላጎት በገለልተኝነት የሚመዘግብ መድረክ ሳይሆን፣ ቀድሞ የተያዘን ኦነጋዊ አጀንዳ በ“ሕዝባዊ ምክክር” ማኅተም ለማጽደቅ የተዘጋጀ መሣሪያ መሆኑን ነው። ከታች ያልመጣን ከላይ አውርዶ፣ ያልተባለን እንደተባለ ጽፎ፣ የብዙኃኑን ድምፅ አጥፍቶ፣ የጥቂቶቹን ፍላጎት ከብዙኃኑ ጋር እኩል አማራጭ አድርጎ ማቅረብ ከሆነ፣ ይህንን “ምክክር” ማለት ለቃሉ ራሱ ስድብ ነው።

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12654
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ከብሔራዊ ምክክሩ ጀርባ በኦሮሚያ ብልጽግና ካድሬዎችና በብሔራዊ ደህንነት ቢሮ አባላት እየተፈጸሙ ያሉ ደባዎች፤ ከደረሱኛና አፈትልከው ከወጡ ቁልፍ መረጃዎች በጥቂቱ፤ ( ያሬድ ሃይለማርያም )

Post by MINILIK SALSAWI » 15 Aug 2026, 23:52

ከብሔራዊ ምክክሩ ጀርባ በኦሮሚያ ብልጽግና ካድሬዎችና በብሔራዊ ደህንነት ቢሮ አባላት እየተፈጸሙ ያሉ ደባዎች፤ ከደረሱኛና አፈትልከው ከወጡ ቁልፍ መረጃዎች በጥቂቱ፤ ( ያሬድ ሃይለማርያም )
++++++
የቆዩና ታሪካዊ የሆኑ ስብራቶችን፣ ፖለቲካዊ ቁርሾዎችን፣ የተፈጸሙ በደሎችን፣ ግፎችንና የመብት ጥሰቶችን፣ በማህበረሰቡ መካከል የተፈጠሩ ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ነገሮችን ለማከምና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በሚል ለአራት አመት የተደከመበት የብሔራዊ ምክክር አዳዲስ ቁርሾዎችንና የፖለቲካ ሽኩቻዎችን መፍጠሪያ መድረክ ሆኗል።
ከሁለት ቀን በፊት እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ ተሳታፊ የሆኑ አምስት ሰዎችን በተናጠል ሰፋ ያለ ጊዜ ወስጄ ማውራት ችዬ ነበር። ከአምስቱ ሁለቱ የቆዩ የብልጽግና አባላት ሲሆኑ በመንግስት ሽፋን የኦሮሚያ ብልጽግና አባላት በምክክሩ ላይ እየፈጸሙት ባለው ፍጹም ሕገወጥ፣ መረን የለቀቀና አይን ያወጣ የአጀንዳ ነጠቃ ሥራ አንጀታቸው ያረሩ ካድሬዎች ሲሆኑ አንዱ ለብልጽግና ካለው ስስ ልብና ጭፍን ድጋፍ የተነሳ ዲያስፖራውን ወክለዋል በሚል ከውጭ ከገቡት ሰዎች ነው።
ለማንኛውም በነበረኝ ሰፊ ውይይት ከዚህ የሚከተሉት መረጃዎች ደርሰውኛል።
1ኛ/ በዚህ ምክክር ላይ ሁሉም የብልጽግና አባላት ለብቻቸው ተጠርተው በመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና በተለይም በደህንነት ሰዎች በተሰጣቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ብልጽግና ከሚፈልጋቸው አጀንዳዎች ውጪ የመንግስትን ገጽታ የሚጎዱ ምንም አይነት አጀንዳዎች እንዳይጸድቁ እንዲረባረቡ፣
2ኛ/ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ የብልጽግና አባላት ደግሞ ለብቻቸው በየቀኑ ከምክክሩ በኋላ በየአጀንዳው ላይ ከደህንነትና ከክልሉ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩና ትዕዛዝ እየተቀበሉ ሌሎች ተሳታፊዎችን (ኦሮሞ ያልሆኑ የብልጽግና አባላትን ጨምሮ) በተናጠል እንዲያስፈራሩና በስብሰባዎቹም ላይ ቁጣቸውን እንዲገልጹ፣ አጀንዳ እንዲያስቀይሩ፣
3ኛ/ በተወሰኑና እጅግ አወዛጋቢ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ፤ በተለይም የአዲስ አበባና የድሬደዋ ከተሞች እጣፈንታ፣ በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች፣ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ስለሚደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት፣ በኦሮሚያ ክልል ስለሚገደሉ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በተነሱ የድንበር ይገባኛል ጥያቄዎች፣ ውዝግቦችና ሌሎች ከኦሮሚያ ክልል ጥቅም ጋር ተያይዘው በተነሱ ጉዳዬች ላይ በተደረጉ ውይይቶች ላይ ጠንካራ አቋም ይዘው እውነቱንና ትክክለኛ ያሉትን ነገር የተናገሩ፣ የተከራከሩና አጀንዳ ያስያዙ ሰዎች በስም ተለይተው በተናጠል በደህንነት አባላትና በካድሬዎቹ በኩል ክትትል እንዲደረግባቸውና ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ የደረሰባቸው መሆኑን።
4ኛ/ ካናገርኳቸው የብልጽግና አባላት አንደኛው በሦስት የኦሮሚያ ብልጽግና አባላት እዛው ስብሰባው ላይ 'አርፈህ ተቀመጥ፣ በመንግስት ደህንነቶች አይን ውስጥ ገብተሃል፣ እያንዳንዱ ንግግርህ ተቀርጿል፣ እንደ በጥባጭ ነው የተቆጠርከው፣ ትላንት ማታ የኦሮሚያ ብልጽግና አባላት ከደህንነት ሰዎች ጋር በነበረን ውይይት ያንተም ስም ከበርካታ ሌሎች ተቀናቃኝ ሰዎች ጋር ተካቶ ስምህ ሲነሳ ነበር፣ እርምጃ ሊወሰድብህ ይችላል፣ አርፈህ ልጆችህን አሳድግ' የሚሉ ምክር የመሰሉ ማስጠንቀቂያዎችና ማስፈራሪያዎች ከኦሮሚያ ክልል በመጡ ተሳታፊዎች የተሰጠው መሆኑን ገልጾልኛል።
5ኛ/ ሁሉም የምክክሩ ውይይቶች በቪዲዬ የሚቀዱ ሲሆን ኮሚሽኑ ለታሪካዊ ሰነድነት የሚቀመጥ ነው ቢልም ውይይቶቹ በሚካሄዱባቸው ሰዓት እዛው በሕንጻው ውስጥ የተለየ ክፍል ተዘጋጅቶላቸው ወሩን ሙሉ የእያንዳንዱን ስብሰባ ሂደት በእስክሪን እንዲከታተሉ የተመደቡ የብሔራዊ ደህንነት አባላት በምን አጀንዳ ላይ ማን ምን ተናገረ የሚለውን እየመረመሩ ግለሰቦቹ ላይ ክትትል እንደሚያደርጉና አስፈላጊም ሲሆን ግለሰቡ የያዘውን አቋም እንዲቀይር ውስጥ ባሉ የኦሮሞ ተሳታፊዎች መልዕክት እንደሚላክበት፣ ግለሰቡ አቋሜን አልቀይርም ካለም ደህንነቶቹ በቀጥታ እንደሚያናግሩትና እንደሚያስፈራረት በደሉ የደረሰበት ተሳታፊ አጫውቶኛል።
6ኛ/ እጅግ አሳፋሪ የሆነው ጉዳይ ደግሞ ከላይ በጠቀስኳቸው የኦሮሚያ ክልልን የሚመለከቱ ጉዳዬች ላይ ውይይት ተደርጎ በአብላጫው ድምጽ የጸደቁና በቃለ ጉባኤ የሰፈሩ የውይይት ሃሳቦች ለፊርማ ተዘጋጅተው ሲመጡ በደህንነትና በኦሮሚያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውሳኔ ተቀይረውና ከስምምነቱ ውጪ ተዘጋጅተው ለፊርማ እንደሚቀርቡ፣ አንፈርምም ባሉ ሰዎች ላይም ክትትል፣ ወከባ፣ የግድያ ዛቻ፣ ማስፈራሪያና እንደሁኔታው መደለያዎችም እንደሚቀርቡ፤
7ኛ/ ውይይት ተደርጎባቸው በተሰብሳቢው የጸደቁ ነገር ግን የኦሮሚያ ክልልን የሚመለከቱ ጉዳዬች ሁነው የክልሉን ካድሬዎች የማያስደስቱ ጉዳዮች ውይይቱ ካለቀም በኋላ ከሰነዶቹ ላይ ተለይተው እንዳይካተቱ መደረጉን እና ይሄንንም የተቃወሙ ግለሰቦች ላይ ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተሰነዘረ መሆኑን፣
8ኛ/ በእያንዳንዱ ውይይት በሚካሄድበት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለውይይት ከተመደቡት ሰዎች ውጭ አስተባባሪ፣ አስተናባሪ መስለው እያንዳንዱን ተወያይ የሚቆጣጠሩ ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሰዎች መኖራቸውና በተወያዬቹ መካከል እርስ በርስ የሚደረጉ ምክክሮችን ጭምሮ ለመስማትና ለመቆጣጠር የሚጥሩ መሆኑን።
በአጠቃላይ ይህ የምክክር ሂደት ከምክክር ኮሚሽኑ እጅና ቁጥጥር ሙሉ በሙሉ መውጣቱንና ምክክሩን ከጀርባ ሆኑ አቅጣጫ እያሲያዘ ያለው የኦሮሚያ ብልጽግና ካድሬዎችና የብሔራዊ ደህንነት ቢሮ መሆናቸውን ያነጋገርኳቸው የብልጽግና አባላት ብዙ ማሳያዎችን እያቀረቡ አረጋግጠውልኛል።


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12654
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ምክክር ኮምሽኑ አያስፈልግም ያለችው የክምሽኑ ባለስልጣን ነች!

Post by MINILIK SALSAWI » 21 Aug 2026, 01:22

ድንቃንድ ዜና!
ምክክር ኮምሽኑ አያስፈልግም ያለችው የክምሽኑ ባለስልጣን ነች!
ዛሬ ኦህዴድ ከምክክር ኮምሽኑ አሰራር ውጭ ይወሰንልኝ ከማለቱ በፊት የኮምሽኑ ምክትል ኮምሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ኦዳ ነች ምክክሩን በአፍ ጢሙ የደፋችው!
ትናንት ጠዋት አጀንዳዎችን ቅርፅ አስይዘው ለ500 ቡድኖች ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ነበሩ። አጀንዳዎችን ለእነዚህ ቡድኖች የሚያቀርቡት ያልጨረሱት ጉዳይ ስለነበር ተወያዮቹ አዳራሽ ገብተው ቁጭ ባሉበት ሂሩት ገብረስላሴ ኦዳ ገብታ አንድ አስገራሚ ትዕዛዝ ሰጠች።
ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉት አጀንዳዎች ብዙዎቹ አጨቃጫቂ ጉዳይም አማራጭም አልቀረበባቸውም። እናማ ሂሩት ወደ አዳራሽ ገብታ "የሚቃረኑ አማራጮች መቅረብ የለባቸውም። ሁለት አማራጮች ካሉ ወደ አንድ አጠቃልላችሁ አቅርቡ። አንዱ አንደኛውን የሚቃረን አማራጭ ለመንግስት አናቀርብም" ብላ ትዕዛዝ ሰጥታ ወጣች። ስለ አዲስ አበባ ነውኮ።
ልብ በሉ። ምክክር ኮምሽኑ የሚያቀርበው ምክረ ሀሳብ ነው። ምክረ ሀሳብ አንድም ሁለትም ሶስትም ሊሆን ይችላል። በእስካሁኑ አሰራራቸውም የተወያዮቹን ሀሳብ በምክረ ሀሳብነት እናቀርባለን ነው ያሉት።
ይህ ብቻ አይደለም። የኦሮሞ ብልፅግና አቋም የንዑሳን ሀሳብ ሆኖ መውደቅ ሲኖርበት አማራጭ ሆኖ እንዲያልፍ ያደረገው ኮምሽኑ ነው።
ይህም ብቻ አይደለም። በ500 ቡድኖች ሀሳብ እጅ ተወጥቶ እንዳይወሰን ያደረጉት የኦህዴድ ሀሳብ ውድቅ ስለሚሆንባቸው ነው።
ወደ ዋናው የሂሩት ጉዳይ እንመለስ!
ዛሬ የኦህዴድ ሰዎች ከአዳራሽ የወጡት የሂሩትን ሀሳብ ይዘው ነው። ሂሩት ለኦህዴድ ሰዎች ግንባር ቀደም ነች። ትናንት ሂሩት "ሁለት አማራጭን ለመንግስት አናቀርብም። አንድ አማራጭ አድርጉት" አለች።
ዛሬ ኦህዴድ "የእኛን ሀሳብ ብቻ ብቸኛው ምክረ ሀሳብ አድርጉልን" ብሎ ነው። ይህ ስላልተቻለ ነው። ከአዳራሽ ወጥቶ የዋለሁ።
ደግማችሁ ልብ በሉ!
የኦህዴድ ሀሳብ የልዩነት ሀሳብ ሆኖ ነው ያለፈው። ውድቅ መሆን ነበረበት። የልዩነት ሀሳብ ውድቅ ነው። የተሸነፈ ነው።
ያች የልዩነት የተባለች ሀሳብ ትናንት ዳር ዳሯን በሂሩት ገብረስላሴ ኦዳ በኩል "አንድ ብቻ ይሁን" ተባለ።
ዛሬ ኦህዴድ በጥሬው የትናንቷን የሂሩትን ሀሳብ አመጣት።
የአዲስ አበባ ጉዳይ በዚህ ሁሉ ነው እያለፈ ያለው!
ከዚህ በተጨማሪ በኮምሽኑ የአዲስ አበባ ጉዳይ አድራጊ ፈጣሪ ዮናስ አዳዬ ነው።
በአዲስ አበባ ጉዳይ የኮምሽኑን ሰዎችም ተወያዮችንም በማግባባት ኦህዴድ የወከለው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌን ነው!
የአዲስ አበባ ጉዳይ በዚህ ሁሉ መሃል የከበዳቸው እውነት ስለሆነ ብቻ ነው።
የሆነ ሆነና ምክክሩ አያስፈልግም የሚለውን የኦህዴድ ሀሳብ የምትመራው የኮምሽኑ ምክትል ነች። ከሂደቱ ውጭ፣ ከመርህ ውጭ፣ ከአሰራሩ ውጭ ሁለት አማራጭ አናቀርብም ብላ የኦህዴድን በራሱ ድግስ ማመፅ የምትመራው ሂሩት ናት። ከአሁን ቀደም ሌሎች ራሳቸው የሰሯቸውን ሂደቶች አፍርሰዋል። ይህኛው ግን ገራሚ ነው። ምክክሩ አይረባም እያሉ ያሉት የኮምሽኑ አመራሮችና አዛዣቸው ኦህዴድ ነው!

Post Reply