በአዲስ አበባ ከተማ እና ነዋሪወቿ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ ..... ከ አፋብን ፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
Posted: 15 Aug 2026, 23:29
"በአዲስ አበባ ከተማ እና ነዋሪወቿ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል"
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ !
ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም
ዘረ ፈጁ የብልፅግና አገዛዝ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል ስም በኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂደው የድራማ መድረክ የህዝብ ውክልና የሌለበት፣ ተጨማሪ ቀውስ የሚያዋልድ እና የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የተነደፈ የአረመኔው አገዛዝ የፖለቲካ አሻጥር መሆኑን ከዚህ በፊት ባወጣነው መግለጫ አቋም መውሰዳችን ይታወቃል።
ሆኖም ግን አገዛዙና አጋሮቹ ይህንን ከጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ ያቀረብንላቸውን ጥሪ በመተው ''በምክክር'' ስም የከተሞችንና አካባቢዎቻቸውን የታሪክ፣ የዴሞግራፊ፣ መልክአምድራዊና የይዞታ ቅርፃቸውን ለማዛባትና በተለይም ነባር የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችንና የአማራን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የጥፋት መንገድ ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል።
አዲስ አበባ ከተማ እንደገና ከመቆርቆሯና ከአሁኑ መጠሪያዋ ቀደም ብሎ ''በራራ'' በመባል የምትታወቅ፣ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በጦርነት ሳቢያ እስከወደመችበት ጊዜ ድረስ የአማራ ነገስታት መቀመጫና የአማራ ህዝብ ጥንተ-ርስት እንደሆነች የታሪክ መዛግብትና አርኪዮሎጂያዊ ማስረጃዎች በግልፅ ያረጋግጣሉ።
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል አዲስ አበባ ከተማን በድጋሚ ሲቆረቁሯት፣ ባዶ መሬት ላይ ሳይሆን የአባቶቻቸውን ታሪካዊ ይዞታ፣ ርስትና ውርስ መነሻ በማድረግ ነው። ይህ ታሪካዊ እውነት ሊሸረሸርም ሆነ ማንም አምባገነናዊ አገዛዝ በጊዜያዊ ስልጣን ህዝብ ባላመነበት ፖለቲካዊ ውሳኔ ሊሰርዘው የማይችለው ፅኑ የታሪካችን አንድ አካል ነው።
ከተማዋ የአማራ ጥንተ-ርስት መሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሂደት የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ መኖሪያ፣ የባህልና የኢኮኖሚ ማዕከል፣ እንዲሁም የአንድነት ተምሳሌት ሆና ተገንብታለች። ከዚህ አኳያ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መናገሻና የዓለም አገራት የዲፕሎማሲ ማዕክል መሆኗን ሙሉ በሙሉ ያምናል፤ ይቀበላልም።
በዚህ መነሻ፣ ከተማዋ የብዝኃነትና የጋራ እድገት ማዕከል እንጂ የአንድ ዘረ ፈጅ አገዛዝ ብቸኛ መጫወቻ ስፍራ ልትሆን እንደማትችልም ድርጅታችን ያረጋግጣል። የአማራ ህዝብ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገሪቱ በስፋት በሚኖርባቸው አካባቢዎች፤ ፍትሐዊ የስልጣንና የሀብት ተጠቃሚነቱ መረጋገጥ እንዳለበት ድርጅታችን ያምናል።
በአሁኑ ወቅት፣ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ አዲስ አበባን በብቸኝነት የአንድ ወገንና ብሔር በበላይነት እንዲቆጣጠራት ለማስቻል የሚሰራው ሕግን የጣሰ፣ የዴሞግራፊና የጂኦግራፊ ለውጥ በምንም መልኩ ሕጋዊ፣ ሞራላዊ፣ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።
አገዛዙ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል የፖለቲካ ሽፋን በከተማዋ ላይ የሚያካሄደው ሴራና አሻጥር
የከተማዋን ነባር ኗዋሪዎች መብት የሚጥስ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያነቷን የሚክድና ታሪካዊ እውነታውን ለማዛባት የተሸረበና የአንድ ቡድን የበላይነትን በህዝባችን ላይ በኃይል ለመጫን ያለመ በመሆኑ፣ የዚህን አምባገነን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር መላው የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንዲያወግዙት፣ እንዲቃወሙትና እንዲታገሉት በድርጅታችን አፋብን ስም ጥሪ እናቀርባለን።
እንዲሁም በከተማዋ ቀደም ብለው ይኖሩ የነበሩትም ይሁን አሁንም የሚኖሩት 80 በመቶ ( በ1999 ዓ.ም በተካሄደው ህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት) የሚሆኑት ነባር ኗዋሪዎች አማራዎች ናቸው። በመሆኑም የህዝብ ስብጥርንም ሆነ ታሪካዊ እውነታን በኃይልና በተሳሳተ ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመቀየር የሚደረገውን ማንኛውም የአገዛዙን ሴራ አጥብቀን የምንታገለው መሆኑን እንገልፃለን።
የአማራ ህዝብ በገዛ አገሩ ከገጠመው ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ ባሻገር ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የትጥቅ ትግል ውስጥ ለመግባት ካስገደዱት ምክንያቶች መካከል፦
በአዲስ አበባ ከተማ በአገዛዙ የተደቀነው የዴሞግራፊ ለውጥ አደጋ፣ የከተማዋን ቀደምት ባለቤቶችና ነባር ኗዋሪዎች በማፈናቀልና ማንነታቸውን በማጥፋት፣ የአማራ ህዝብ ከከተማዋ ጋር ያለውን ታሪካዊ እና ማህበራዊ ትስስር በመበጣጠስ ከህዝቦች ተፈጥሯዊ መስተጋብር ውጭ በሆነ መልኩ የባህል፣ የቋንቋና የተለያዩ አመለካከቶችን በኃይል ለመጫን የሚደረገው ሩጫ ይገኝበታል።
በመሆኑም፣ ድርጅታችን አፋብን ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ውስጣዊ አንድነቱንና አደረጃጀቱን ጠብቆ በመጓዝ፣ አምባገነኑና ከፋፋዩን አገዛዝ በጀመርነው ትግል ከስሩ ነቅለን በመጣል፣ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚስማማ፣ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያከብር ሥርዓተ መንግስት በመገንባት ፍትህ፣ እኩልነትና የሕግ የበላይነትን ከመትከል ባሻገር አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያና ዋና ከተማ፤ የአንድነትና የእድገት ማዕከል ሆና እንድትቀጥል ይታገላል።
አገሪቱ ከገባችበት ጥልቅ የህልውና፣ የፍትህና የእኩልነት ቀውስ መውጣት የምትችለው የህዝቧን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በኃይል በማፈን፣ አገሪቱን የማያቋርጥ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በማስገባት ወደ ገደል እየመራት ያለውን ዘረ ፈጁን የብልፅግና አገዛዝ፤ በሕዝባዊ ትግል ሙሉ በሙሉ መገርሰስ ሲቻል ብቻ መሆኑን አፋብን በፅኑ ያምናል።
በስተመጨረሻ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ በአዲስ አበባ ከተማና በህዝባችን ላይ በምክክር ስም የጠነሰሰው ዓይን ያወጣ የፖለቲካ አሻጥር የፈጠረው የህልውና በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)