Page 1 of 1

GERD 2.0

Posted: 13 Aug 2026, 21:24
by Horus
KOYSHA DAM


Re: GERD 2.0

Posted: 13 Aug 2026, 22:23
by Axumezana
GERD was the begining ! It was TPLF led EPRDF that started Koysha dam!

Re: GERD 2.0

Posted: 13 Aug 2026, 23:50
by Horus
Axumezana wrote:
13 Aug 2026, 22:23
GERD was the begining ! It was TPLF led EPRDF that started Koysha dam!
TPLF - THE CANCER OF ETHIOPIA.

Re: GERD 2.0

Posted: 13 Aug 2026, 23:59
by Axumezana
Horus you can not eliminate history !

Re: GERD 2.0

Posted: 14 Aug 2026, 04:18
by Meleket
Meleket wrote:
10 Sep 2025, 03:40
Meleket wrote:
09 Sep 2025, 10:24
ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

መለስ ወዲ ኣለማሽ ኣባይን ባይገድብ
ኢትዮጵያ ነበረች ዓይን-ዬሌላት ቅንድብ:mrgreen:

ኢንጅነር ስመኘዉ የዓባዩ መሃንዲስ
የጎንደሩ ቅዱስ፡
መስቀል አደባባይ በመንፈስ ሚቀደስ

ለኒህ ሁለት ፈርጦች የምድረ ኢጦብያ፡
ስላስመሰከሩ ያላቸውን ሙያ፡
ልዑል ክብር ኣላት ሃገረ ኤርትርያ!

በወዲ ዜናዊ "ተስሎ ተጠርቦ"፡
ሕወሓት ወያኔ "ቦተሊካ ጠግቦ"፡
ምድረ ኢትዮጵያዊን በጥበብ ሰብስቦ፡
በኢሕኣዴግ ዘመን አባይን ገድቦ፡
ግሩም ተግባር ሰርቷል "ለሃገሩ" አስቦ።


እኛ ኤርትራዉያን የመሃል እና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር፡ ለዓዲዃላዋ የእታችን ልጅና የሴራ ቦተሊካ ሰለባ ለሆነው ለጎንደሬው መሃንዲስ የቋጠርንላቸው ስንኝ መሆኑ ነው።

ግእዛዊው 2018 ዓ.ም. የሰላም የተመስገንና የጸጋ ዘመን ይሆን ዘንድ ተመኝተናል ለመላው የዓለም ህዝብ!

ተጣፈ "በዘመነ ጽምዶ" - በዘመነ ማርቆስ ዋዜማ




viewtopic.php?f=2&t=367260&p=1578536#p1578536

Re: GERD 2.0

Posted: 14 Aug 2026, 04:34
by Meleket
viewtopic.php?f=2&t=304316&start=60
Selam/ wrote:
03 Sep 2025, 18:00
Endorsed!

Meleket wrote:
03 Sep 2025, 09:11
ፎተሊካዉ ይቆይልንና . . . . ኢንጅነር ስመኘው በቀለና ጠቅላዪ መለስ ዜናዊ ነብስ ይማር ብለናል። ለሃገራችሁ ብልጽግና ከማንም በላይ የበኩላችሁን አሻራ አኑራችኋልና፡ በልማት አርበኝነታችሁ ሃገራችሁ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ሰላም ወዳድ ያፍሪካ ቀንድ ህዝቦችም ይዘክሯችኋል!

ብልጽግኖች ግን የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ገዳይ ለምንድን ነው በይፋ ለህዝብ ያላሳወቁት? ኢንጅነሩን ማን ገደላቸው? ለምን? ነፍሳቸውን በገዛ እጃቸው አጥፍተዋል ከተባለስ፡ በምን ምኽንያት? በምንና በማን ተጽእኖ? ለህዝብ መታወቅ ይገባዋል። ኣይደለም እንዴ!

የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ፡ ባለቀ ሰዓት የተከሰቱ አካላት፡ ጠቅላይ አብዪም ሆኑ ዶ/ር ብርሃኑ እንዲሁም ዲያቆን ዳንኤል እና ዶ/ር አረጋዊና ወዘተ እኛ ነን ከመሰረቱ የሰራነው ብለው ጉራ እዬነዙ ከሆነ፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር እዬታዘብናቸው እንደሆንን ለመግለጽ ያህል ነው! ምንም ቢሆን ግድቡን በቁርጠኝነት አስጀምሮ፡ ከግማሽ በላይም ሰርቶ ያሳያችሁና መንገዱን ያሳያችሁ የዓዲኳላዋ እህታችን የኤርትራዊቷ የማህጸን ፍሬ ከትንታጉ ጎንደሬ ኢንጅነር ጋር በመናበብ ነውና!

ይመቻችሁ!

Meleket wrote:
20 Sep 2022, 09:35
ወደር ዬሌለውና የተሻለው ኣማራጭ "ኣካፋውን ኣካፋ፡ ዶማውንም ዶማ" ማለት ብቻ ነው፡ በጨዋነት! :mrgreen:
Selam/ wrote:
20 Sep 2022, 07:15
ወይ ሙሉውን መመስገን ወይንም ሙልጭ ተደርጎ ሙሉውን መሰደብና መጠላት ነው ያለበት የሚባልበት የደንቆሮዎችና የጎጠኞች ዘመን ነው ያለነው።

እዚህ መረጃ ፎረም ላይ የተሰገሰጉትም እንክርዳዶች፣ በድፍኑ ከመጥላት ወይንም ከመቃወም ውጭ ቅንጣት የምታክል ሚዛናዊነት የላቸውም። አንዲት ጥሩ ነገር መዘህ ብታመሰግን፣ ጠጉራቸው እስኪረግፍ የሚንጨረጨሩ እንዳሉ ሁሉ፣ ስለ ጥፉቶቹ በፍፁም መስማት አንፈልግም የሚሉት አባጨጓሬዎችም እልፍ አእላፍ ናቸው። ይኸ ትልቅ ዝቅጠት ነው።

በኔ በሰላም ቤት ይኸ የጎጠኛ አስተሳሰብ አይሰራም። ጥፋት መስሎ የታየኝን እሸነቁጠዋለሁ። በጭፍን አልጠላም፣ በጭፍን አልወድም። አንዱ ወያኔ፣ ሌላው ኤርትራዊ፣ ኦሮሞ ወይንም ጉራጌ እንዲሁም ወላዋይ እያለ ስም ሲለጥፍልኝ አቋሜ ትክክል መሆኑን ያረጋግጥልኛል።

ይኸን ካልኩኝ በኋላ፣ በአባይ ግድብ የኢትዮዽያ ህዝብ በወያኔዎች በሚያሳፍር ሁኔታ ተዘርፏል ተመዝብሯል። የኤርትራውያኖችም ንብረት እነሱ ኪስ ውስጥ ነው የገባው። የአንድ የኤርትራዊ ጎረቤቴን ወርቅ ቤት፣ በራሱ ስም ለውጦ ፍጥጥ ያለው የወያኔ የሌባ አይነ ደረቅ ሁሌ ሳስበው ምንም አይነት የርህራሄና ይሉኝታ መንፈስ ስላልተፈጠረበት ይገርመኛል። መሬቷ ትቅለለውና፣ አቻምና ወንዝ ተሻግሮ ወደመጣበት ሄዷል።

Meleket wrote:
20 Sep 2022, 04:01
ንወድሰብ እንተሃብካዮ ናቱ፡ ኣቦይእዝጊ ከምኡ ኢዩ ዚፈቱ!” እንዲሉ ያገራችን ሰዎች፤ “ሳታዳላ እውነትን በመግለጥ ሰዎችን እንደዬስራቸው በትክክል ከመዘንክ፡ እግዚኣብሔር እንዲያ ነው የሚወድ” እንደማለት ነው! እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ የቀድሞው የኢትዮጵያዊ ጠቅላዪን ነፍስኄር ኣቶ መለስ ዜናዊን እንደምንወቅሳቸው ሁሉ ያለንን ኣድናቆት የምንገልጽባቸው ኣጋጣሚዎችም ኣሉ። :mrgreen:

የኤርትራ ጉዳይ በኤርትራ ነጻነት ዋዜማና ወቅት የኣቶ መለስ ሚና

ኣቶ መለስ ዜናዊ፡ ማንም ኤርትራዊ ተራ ይሁን ወደል ካድሬ በዲፕሎማሲውና በቦለቲካው ረገድ ያላደረገውን፡ ድንቅ ስራ ለኤርትራችን ሰርተዋል። ይህም በኤርትራ የነጻነት ዋዜማ፡ መላው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብን “የኤርትራን ህዝብ የራስ ዕድል በራስ የመወሰን መብትን እንዲቀበል” ህዝቡ በሚገባው ቋንቋ ቅልብጭብጭ ኣድርገው በመግለጽ፡ በርካቶችንም በማሳመን፡ በፖለቲካው ረገድ ለኤርትራችን ትልቅ ውለታ ውለዋል። እንዋጋለን ለሚሉ የደርግ ትራፊዎችንም “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ” በማለት ቁርጣቸውን ነግረዋቸዋል።

የሪፈረንደምን ውጤትና የሃገረ-ኤርትራን ነጻነት እውቅና በመስጠት፡ ለኤርትራ ነጻነት ማንም ኣካል ሊሰጠው ከሚችል እውቅና በበለጠ መልኩ፡ የሃገረ ኢትዮጵያን መንግሥት በመወከል፡ ድንቅ ተግባር ከውነዋል። ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ይህንን ውለታቸውን ወትሮም ኣንዘነጋም።

ይህን ስንል ግን ኣቶ መለስ፡ ኣላስፈላጊ የድንበር ግጭት ሲከሰት፡ ከወዲሁ እንዲፈቱትና በሰላም እልባት ላይ ሊያደርሱት የሚገባን ጉዳይ ችላ በማለት፡ በኤርትራችን ላይ ጦርነት በማወጅ፡ ህዝባችንን በዓይን ቀለም የቦለቲካ ፈሊጥ በመዝረፍ፡ ሃገራችንን ማዕቀብ እንዲደረግባት እንቅልፍ ሳይተኙ ያደሩበትን ሁኔታና ወደባችንን የገመል መጠጫ እንድናደርገው የተመኙበትን የምቀኝነት ተግባራቸውን በፍጹም ኣንረሳውም እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች።

የኣባዪ ግድብን በተመለከተ

የኣባዪ ግድብ የኢትዮጵያውያን ግድብ መሆኑን የምንረዳ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ግድቡን ለመገደብ ቆርጦ በመነሳትና በድፍረት ስራውን በመጀመር ኣቶ መለስ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ውለታ መዋላቸውንም እናውቃለን። :mrgreen: ነገር ግን የግድቡን የመሰረት ድንጋይ በሚያኖሩበት ወቅት፡ “በዓይን-ቀለም የቦለቲካ ፈሊጥ” ከኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራውያን ዜጎች በጠራራ ጸሃይ በተዘረፈ ገንዘብ መሆኑን ስለምናውቅ፡ ኣቶ መለስን እንቃወማቸዋለን። ከዚህ በተረፈ ለትግራይ የዘረፋ ኩባንያቸው ከለላ በመሆን፡ ስኳር በማትነን፡ በ97 ምርጫ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን በጠራራ ጸሃይ በመረሸን ወዘተ ያካሄዱት እርኩስ ተግባር፡ ኢትዮጵያውያንን ስለሚመለክት ጉዳዩን ለኢትዮጵያውያን እንተውላቸዋለን። ኢትዮጵያዊው የህዳሴ ግድብ ሲወሳ ግን “በዓይንቀለም የቦለቲካ ፈሊጥ” የተዘረፈውንና ለህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ ማኖሪያ የዋለውን ኤርትራዊ ሃብት፡ የታሪካችን ኣካል በመሆኑ ዛሬም ነገርም ከነገወዲያም እናስታውሰዋለን እናወሳዋለንም፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:
Selam/ wrote:
17 Sep 2022, 05:38
Credit where credit's due - Meles Zenawi on Abay







Re: GERD 2.0

Posted: 14 Aug 2026, 09:52
by DefendTheTruth
Axumezana wrote:
13 Aug 2026, 22:23
GERD was the begining ! It was TPLF led EPRDF that started Koysha dam!
We know for sure that "TPLF led EPRDF" mafia started many more projects, but we are also aware that the group has never finished the overwhelming majority of those projects.

Do you deny?

In that case the puzzle remains why the group is known for starting projects but not for actually finishing them?

Do you have a clue?