Page 1 of 1

የቀረበላቸውን "የይቅርታ ሰነድ" የፈረሙ እና ውድቅ ያደረጉ የሽብር ተከሳሾች በተለያየ ክፍል እንዲታሰሩ መደረጉ ተገለፀ

Posted: 13 Aug 2026, 10:34
by MINILIK SALSAWI
ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ የተከፈተባቸው "የሽብር ክስ እንዲቋረጥ" የቀረበውን "የይቅርታ ሰነድ" የተቀበሉ እና ውድቅ ያደረጉ ተከሳሾች የታሰሩበት ክፍል እንዲለያይ መደረጉን ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ።

የተከሳሾቹ ማቆያ እንዲለያይ የተደረገው "በይቅርታ ሰነዱ ምክንያት ከተፈጠረ አለመግባባት" ጋር በተያያዘ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።

የሽብር ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የሕዝብ ተወካዮች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ሌሎች ተከሳሾች፤ "መንግሥት የይቅርታ ሰነድ" እንዳቀረበላቸው ሦስት ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።



ታሳሪዎቹ፣ "ይቅርታ ጠይቀው ክሳቸው እንዲቋረጥ እና ከእስር እንዲለቀቁ" ለቀረበላቸው ጥያቄ የተለያየ ምላሽ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ከማክሰኞ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም. ጀምሮ "የይቅርታ ሰነዱ" ላይ ፊርማቸው ያኖሩ እና የተቃወሙት ተከሳሾች የነበሩበት ማቆያ ክፍል እንዲለያይ መደረጉንም ምንጮቹ አስረድተዋል።

ቢቢሲ ስለ ጉዳዩ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ወዲያውኑ ምላሽ አላገኘም። የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽንን አስተያየት ለማግኘት ጥያቄ ቀርቧል።

ሰነዱን ላይ እንደማይፈርሙ ከገለጹ ተከሳሾች መከካል የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሐንስ ቧያለው፣ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው እና ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለ ማርያም ይገኙበታል።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎቹ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ዳዊት በጋሻው፣ አባይ ዘውዱ እና ገነት አስማማውም ሰነዱን ውድቅ ካደረጉት መካከል እንደሆኑ ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ዝርዝሩ https://www.bbc.com/amharic/articles/ckgdpd288vgo