Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ በመሆኑ ከሀበሻ ጋር አንነጋገርበትም ፡ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት የዘር ፍጅት ቅስቀሳ በአብይ ምክክር ኮሚሽን

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Aug 2026, 09:26

ተመልከት የዘር ፍጅት ቅስቀሳ
ይህ ሰው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንትና የአዲስ አበባን ጉዳይ በዋነኛነት ያስያዙት ሰው ነው። ፅንፉን አቋም ይዞ እንዲያስተባብር በኦህዴድ ሰዎች ኃላፊነት የተሰጠው ነው። ይህን ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ ፕሬዝደንትነቱም ቀድሞ በነበረበት ትምህርት ሚኒስትርም በርካቶችን በተለይ ከተለያየ አካባቢ የመጡ ምሁራንን ያግባባል ተብሎ ነው።
ሰውየው ግን የሚዘራው ጥላቻ ነው። ራሳቸው የኦሮሞ ተወላጆች በምክክሩ ወቅት ሰብስቦ የነገራቸውን እየፃፉት ነው። ይህ ሰው የኦህዴድ ተወካዮችን "አዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ በመሆኑ ከሀበሻ ጋር አንነጋገርበትም" እያለ ነው።
ምክክር ተብሎ ተጠርቶ "ከሀበሻ ጋር በአዲስ አበባ ጉዳይ አንነጋገርም" ይላል። ሰውየው በዚህ ጥላቻው ለፖለቲካ ስልጣን መታጨት ፈልጓል። ይህ ቅስቀሳ ታዲያ ነገ "ሀበሻ ከአዲስ አበባ ይውጣ" ለማለት ነው። በተለምዶ ሀበሻ ኢትዮጵያዊ ነው። ይህ ፅንፈኛ ኦነግን ጨምሮ ለሌሎቹ ሀበሻ ማለት ጉራጌው፣ አማራውና ትግሬው ነው። በጣም ጠበብ አድርገው ለማጥቃት ሲፈልጉት ደግሞ የሰላሌን ህዝብ ጨምሮ ኦርቶዶክሱን እንዲሁም እንደ ብሔር አማራውን ነው።
ይህ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ በአዳስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የተደረገ ነው። ይህ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ በምክክር ስም በሚደረግ ደባ የኦህዴድ ዋና አስተባባሪ በሆነ ሰው የሚደረግ ቅስቀሳ ነው። አዲስ አበባን እንደ አርሲ፣ እንደ ወለጋ፣ እንደ ሻሸመና የደም ምደር የማድረግ ፕርጀክት ነው!


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በአብይ ምክክር ኮሚሽን .. የዲሞክራሲ ጠላት ሆነው ሳለ ሌሎችን በፀረ ዲሞክራሲነት ይከሳሉ... አድኃሪው ማነው? ተራማጁስ?

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Aug 2026, 09:30

ድሬዳዋና አዲስ አበባን ያህል ከተሞችን ከህዝብ ሊቀሙ ያሰፈሰፉ ሰዎች በስራቸው ያሉትን ሌቦች ይዘንላችኋል ብለው ሊያስጨፍሩን ይጥራሉ።
የማንነት ስርቆት፣ የቀበሌ ስርቆት፣ ዋና ከተማ እስከ ምናምኑ ስርቆትና ሌላው ጠቅላላ ስርቆት የእናንተው ነው!

አድኃሪው ማነው? ተራማጁስ?

የኦህዴድ ብልፅግና ሰዎች የነ መለስ ዜናዊና በረከት ስምኦን ግርፎች ናቸው፡፡ ከነ መለስ ዜናዊ ከወሰዷቸው ትምህርቶች አንዱ ጩኸት መቀማት የሚባለው ነው፡፡ እነሱ የዲሞክራሲ ጠላት ሆነው ሳለ ሌሎችን በፀረ ዲሞክራሲነት ይከሳሉ፡፡ እነሱ የእኩልነት ጠላት ሆነው ሳለ ሌሎችን በፀረ እኩልነት ይከሳሉ፡፡ የሰላም ጠላት ሆነው ሳለ ሌሎችን በፀረ ሰላምነት ይከሷቸዋል፡፡ ዋነኛዎቹ የመሬት ወራሪና ቀማኛ ሆነው ሳለ ሌሎችን በኪራይ ሰብሳቢነት ይወነጅላሉ፡፡
የኦህዴድ ብልፅግና ሰዎችም ይህን መንገድ አስፍተውና አሳድገው ይዘውታል፡፡ ዋነኛዎቹ አድኃሪዎች እነሱ ሆነው ሳለ ሌላውን በአድኃሪነት ይወነጅላሉ፡፡ ተራማጅ ሆነው መታየትም ያምራቸዋል፡፡ ተራማጅ ከሆናችሁ እስኪ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከኦሮሞ ውጪ ያሉት ብሄሮች መብት የሚከበርበትን ስርዓት ፈጥራችሁ አሳዩን፡፡ ወገንተኝነታችሁ ከፍትህና እኩልነት ጋር ከሆነ እስከ መጀመሪያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የብሄሮችና የሃይማኖቶችን እኩልነት ተከብሮ እንየው፡፡ እንወክለዋለን የምትሉት ህዝብ ቁጥር የምትሉትን ያህል ከሆነ ለምን ዲሞክራሲን እንጦር ትፈሩታላችሁ? ለምን አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ህዝቦች መብት አክብራችሁና አስከብራችሁ ዲሞክራትነታችሁን አታረጋግጡልንም? ስለ ተራማጅነታችሁ እንድናምናችሁ ለምን ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሃይማኖትን መብትና እኩልነት አረጋግጣችሁ አታሳዩንም?
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ዲሞክራሲን፣ እኩልነትንና ፍትህን አስፍናችሁ ብታሳዩ እኮ ይህን ሁሉ ስለራሳችሁ ለማስረዳት አትደክሙም ነበር! ሃቁ እሱ ስላልሆነ ነው፡፡
ለዚህ ነው ስለ አዲስ አበባ የያዛችሁት አቋምም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምታራምዱት የጭፍለቃና የወረራ መንገድ ነው የምንለው፡፡ ለዚህ ነው ሁሉም ህዝብ አጀንዳችሁ የአንድን ብሄር አምባገነንነት ማስፈን እንጂ እኩልነት አይደለም የሚላችሁ፡፡ እንደ መለስና በረከት ግርፍነታችሁ በኢትዮጵያ ደረጃ ማስፈን የምትፈልጉትም የተለመደውን ኢ-ፍትሃዊነትን፣ ፀረ ዲሞክራሲን፣ የአንድ ቡድንና ብሄር የበላይነትን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ያፈጠጠ ያገጠጠ አድኃሪነት እንጅ ተራማጅነት አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም!!!
ጭራሽ የማይጠረቃ ብለውም ሌላውን ይከሳሉ? ማን ነው ከሶማሊ እስከ መተማ፣ ከሲዳማ እስከ ኤርትራ የእኔ ነው እያለ ያለው? ማን ነው ኮንዶሚኒዬም አስከፍቶ ከማስ*ወ*ረ*ር ጀምሮ በፀጥታ ኃይል ንፁሃንን አሳፍኖ በባንክ በሚሊዮን እየተቀበለ ያለው? ማን ነው ከመሬት እስከ ህገወጥ ንግድ የሚያግበሰብሰው? ማን ነው አልጠረቃ ብሎ የኢትዮጵያውያንን ኑሮ ያናጋው? እናንተ አይደላችሁም ወይ?

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በአብይ ምክክር ኮሚሽን .... በሚዲያ እንደሚሉት ሳይሆን የሴራ መድረክ ነው። የፖለቲካ ብልጫ መውሰጃ ነው!

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Aug 2026, 09:33

ሌላ የሴራ መድረክ እንጅ ችግር መፍቻ አይደለም‼
በየ ክልሉ ወረዳና ቀበሌ ይሰጠን ጥያቄ የሚያነሱ፣ በተለይ በአማራ ክልል በኦህዴድ ድጋፍ የክልል ጥያቄ ያነሱ፣ አማራ ክልልን በንዑስ ማንነት ሰበብ የሚያበጣብጡ በአዲስ አበባ ጉዳይ አግዙን ተብለዋል።
ኦህዴድ በምክክር ኮምሽን ሰበብ ከማን ጋር ህብረት እየፈጠረ፣ በተለይ የአማራውን ጥያቄ ለእነ ማን አሳልፎ ሊሰጥ እንዳሰበ መገመት ቀላል ነው። የአገር ችግር እፈታለሁ በሚል ቀን ከሌት እያወራ እያጠናከረ ያለው ግን ተነጣዮችን፣ ግጭት ቀስቃሾችን ነው።
በምክክር ስም የሚያደርጉት ደባ ተጨማሪ ችግሮችን ይዞ የሚመጣ እንጅ የአገር ችግር የሚፈታ አይደለም የምንለው ለዚህ ነው። ትህነግ "የፌደራሊስት ኃይል" እያለ አማራን ያቆሰለባቸውን ተነጣይ ኃይሎች ኦህዴድ "በአዲስ አበባ ጉዳይ አግዙኝ እንጅ ጥያቄያችሁን እፈታለሁ" እያለ ነው።
ምክክር ከሆነ ማለቅ ያለበት በተዘጋጀው አዳራሽ ነው። ነገር ግን ለይምሰል ነው የፈለጉት። የሴራ መድረክ ነው። አማራውን ጨምሮ ሌላው በራሱ ጉዳይ ስለተወጠረ ጊዜውን መጠቀም አለብን ብለው ነው! መድረኩም በሚዲያ እንደሚሉት ሳይሆን የሴራ መድረክ ነው። የፖለቲካ ብልጫ መውሰጃ ነው!


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: አዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ በመሆኑ ከሀበሻ ጋር አንነጋገርበትም ፡ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት የዘር ፍጅት ቅስቀሳ በአብይ ምክክር ኮሚሽን

Post by MINILIK SALSAWI » 11 Aug 2026, 23:14

“የእኔ ሚና ውስን ነው፤ ሌሎችን ጠይቁ” የምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኃላፊ!
“የኢትዮጵያ ህልውና የተቋጠረው አዲስ አበባ ላይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ጉዳይ ከተበላሸ ኮሚሽኑ ያሳካዋል ተብሎ የታለመለት ዓላማ ገደል ይገባል፡፡ ስለዚህ የአዲስ አበባን ጉዳይ በተጣደፈ ሁኔታ ሳይሆን ጊዜ ወስዶ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ጊዜ ይሰጠው፡፡ ካስፈለገ የኮሚሽኑን የስልጣን ጊዜም ማራዘም ይቻላል፡፡ ያ የማይሆን ከሆነ ደግሞ በአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት አለመደረሱን ገልጾ ጉዳዩን ማሳለፍ ያስፈልጋል፡፡ አዲስ አበባን ጉዳይ በድምፅ ለመወሰን መሞከርም ጥሩ አይሆንም፡፡” ተብሎ ምክክሩን እየታዘቡ በሚገኙ ምሁራን ሃሳብ የቀረበላቸው ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ “የእኔ ሚና ውስን ነው፡፡ በኮሚሽኑ ውስጥ ያለኝ ተጽዕኖም እንደምታስቡት አይደለም፡፡ እስኪ ሌሎች ኮሚሽነሮችን አነጋግሩ፡፡” በማለት መለስ ሰጥተዋል፡፡
በእርግጥ ምክክሩን በወሳኝነት የሚዘውሩት ወ/ሮ ሂሩት ገ/ስላሴ ኦዳ (ኦነግ) እና የስልጣን ተስፈኛው ዶ/ር ዮናስ አዳዬ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በቅርቡ በሞት የተለዩት አቶ ዘገዬ አስፋውም ቁልፍ ሰው ነበሩ፡፡ ሌሎች ለይስሙላ በማሟያነት የገቡ ናቸው፡፡ እነዚህ ናቸው ከኦህዴድ ብልፅግና ሰዎች ጋር እየመከሩ ሂደቱን እየመሩት የሚገኙት፡፡
መነሳት ያለበት ጥያቄ ግን “ታዲያ ፕሮፌሰሩ በዚህ ደረጃ አቅም የለሽ ከሆኑ የሀገርን የወደፊት እጣ-ፈንታ በሚወስን ሂደት ውስጥ ለምን መሳተፋቸውን ቀጠሉ?” የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱ ወደፊት እንደሚወጣ የታወቀ ነው፡፡ ምክንያቱ ምንም ሆነ ምን ግን ምክክር ተብዬውን እየዘወሩት ያሉት ወ/ሮ ሂሩት እና ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ናቸው፡፡ ዶ/ር ዮናስ አዳዬ አብይ የዶክትሬት ዲግዬን ሰርቼበታለሁ የሚለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የሰላምና ደህንነት ተቋም ዳይሬክተር ተደርጎ የቆየ ሰው ሲሆን፣ ይህን ድራማ እንዲመራ የመጣ ሰው ነው፡፡ ድራማውን ከጨረሰ በኋላ “ብልፅግና ነህ ብልፅግና ነህ እያሉ ይበልጥ ብልፅግናን እንድወደው አደረጉኝ” ብሎ አዲስ የተገባለትን ሹመት እንደሚቀበል ይጠበቃል፡፡ “የእኔ ሚና ውስን ነው” ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያም ነገ በየሚዲያው እየቀረቡ “የደረሰብኝ አንዳች ተጽዕኖና ጫና የለም” እንዲሉ እንደሚደረግ ግልፅ ነው፡፡
በትህነግ ዘመን የአጣሪ ኮሚሽን መሪ ተደርገው የነበሩት ዶ/ር መኮንን ዲሳሳ መጨረሻ ላይ “ኢህአዴግ ነህ ኢህአዴግ ነህ እያሉ ዘምተው ወደ ኢህአዴግ እንድጠጋ አደረጉኝ” ብለው እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ታሪክ በሌላ መንገድ ራሱን እየደገመ ነው፡፡

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

"አዲስ አበባን irrelevant እናደርጋታለን" .... ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን።

Post by MINILIK SALSAWI » 11 Aug 2026, 23:18

"አዲስ አበባን irrelevant እናደርጋታለን"
ሽመልስ አብዲሳ ከ6 አመት በፊት የተናገረው
"አዲስ አበባ ላይ መፍትሄ የሚያመጣው ሶስት ነገር ነው፣ አንደኛው ሰውን ማስፈር ነው፣ በስራ፣ ከማውራት በስራ፣ አትጠይቁን የምንችለውን እያደረግን ነው። ሁለተኛው አዲስ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ነው። አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ እየሰራን ነው። ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን።
ዝም ብሎ አዲስ አበባን በስራችን እናስገባለን ብሎ መለፍለፍ አይደለም። እንዴት ታደርገዋለህ ፣ ፈንጂውን እንዴት ታፈነዳዋለህ? አሁን እኛ ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌላው ክልል ከልክ በላይ እየተጎዳ ነው። ይህ ደግሞ እየሆነ ያለው የፌዴራሉን መንግሥት ኦሮሚያ ስለተቆጣጠረው ነው። የፌዴራሉ መንግስት መከፈል አለበት ብለን ከሌላው ህዝብ ጋር ተጨንቀንበት እየሰራን ነው።
ስለዚህ ይሄንን ስናደርግ irrelevant ትሆናለች አዲስ አበባ። ሶስተኛ አዲስ አበባ ላይ ያለው ሌላ economic option መፍጠር ነው። ለዚህ በቂ ዝግጅት አድርገናል። አሁን በቅርቡ ለጨፌ እናቀርባለን እድሉ ስላለን። ይሄንን አድርገን ነው እንጅ የምንፈታው ሰውም ማባረር አንችልም። ሰው መግደልም አንችልም። ማጫረስም አንችልም። እንዲህ አድርገን ነው ነገሩን የምንፈታው ብለን ነው እየሄድን ያለነው። ስለዚህ ከፈጣሪ ጋር፣ ከእውነት ጋር፣ እየሰራን ካለነው ስራ ጋር፣ ከእናንተ ጋር ከሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ጋር ብልፅግና ይቀጥላል። የኦሮሚያን ብልፅግና እናረጋግጣለን!
ምስራቅ አፍሪካን እንመራለን! ኢትዮጵያን እንደምትመቸን አድርገን እንገነባታለን! እየገነባናትም ነው። ስለዚህ መክዳት፣ መከዳት የሚባለው ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም፣ እንዲህ አይነትም ቦታ የለም፣ እንዲህ አይነት አመለካከትም የለም ይህንኑ ለማለት ነው በርቱ! በግልፅ ስለተናገራችሁን አመሰግናለሁ ልላችሁ እፈልጋለሁ።" See less

Post Reply