Page 1 of 1
የዘር ፍጅት ፉከራ : አዲስ አበባን አሜን ብላችሁ ካልሰጣችሁን እንተላለቃለን ! ብልፅግና በፉግግር ኮሚሽን
Posted: 10 Aug 2026, 09:11
by MINILIK SALSAWI
ኦህዴድ አዳራሽ ውስጥ በማጭበርበር፣ በኮምሽኑ አመራሮችና ባለሙያ ብሎ ባስቀመጣቸው ጫና፣ በገንዘብና ማስፈራሪያ አልችል ሲል ከትናንት ጀምሮ በዩቱዩብና ፌስቡክ ሰራዊቱን አሰማርቶ "አዲስ አበባን አሜን ብላችሁ ካልሰጣችሁን እን*ተ*ላ*ለቃ*ለን" አይነት የዘር ፍጅት ፉከራውን እያሰማ ነው!
ምክክሩ ለይምሰል ነው ያልነው ለዚህ ነው!
የኦሮሞ ብሔርተኞች (አገዛዙን ጨምሮ) ተባብረው እንዲተላለፍ የፈለጉት ዛቻ ነው። በምክክሩ አሜን ብላችሁ ካላፀደቃችሁልን ተወያዮቹም ከአዳራሽ አትወጡም እየተባለ ነው። አገር ይፈርሳል እያሉ ለማስፈራራት ነው። እነ ሽመልስ ዝም አሉም ነው የሚለው ይህ ሰውዬ።
በርካታ ክልሎችን በሸኔ ስም እያስወረረ ግዛት የሚያስፋፋው ኦህዴድ የሚዲያው ሸኔ በኩል አቋሙን አስተላልፏል። ምክክሩ ለይምሰል ነው።
ተሳታፊዎችን ለማጭበርበር ጥረዋል። በኮምሽኑ አመራሮች ጭምር ለማግባባት ሞክረዋል። በገንዘብ ለመደለል ጥረዋል። የፓርቲ አቋም ነው ተቀበሉ ብለው በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል። አዋክበዋቸዋል። አሁን በይፋ እኛ የፈለግነውን ካላደረጋችሁ እናጠቃችኋለን እያስባሉ ነው።
ይህን ሁሉ የሚያደርጉት በህዝብ ይሁንታ ስለማይችሉ ነው። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት የፈሰሰባት፣ የኢትዮጵያ ከተማ እንጅ የቡድን ንብረት ስላልሆነች ነው።
https://facebook.com/reel/1798446027697021
“ለምን በዚህ ደረጃ ዘቀጡ?”
የኦህዴድ ብልፅግና ሰዎች ለምን በዚህ ደረጃ ዘቀጡ ብለው የሚጠይቁ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ “በዚህ ደረጃ ከሞራል መሠረት መውረድ ይቻላል ወይ? በዚህ ደረጃ ያፈጠጠ ያገጠጠ ኢ-ፍትሃዊነት አለ ወይ? የያዙት መንገድ ለእነሱስ እንደ ቡድን ይጠቅማቸዋል ወይ?” ብለው የሚጠይቁ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ እውነትም ህሊና ላለው አካል እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ተገቢ ነው፡፡
እነሱ ግን በደላይ-ህሊና (false consciousness) ተጠቅተዋል፡፡ ልክ የትህነግ አምባገነኖች “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድን” ሲዘምሩን እንደቆዩት፣ እነዚህም በአሸናፊነት ስሜት ህሊናቸውን አጥተዋል፡፡ እነ አብይ በአማራውና በሌሎም ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ለስልጣን እንደበቁ ማሰብ ተስኗቸዋል፡፡ በራሳቸው የፖለቲካ ችሎታ ለስልጣን የበቁ ይመስላቸዋል፡፡ ለራሳቸው የሚነግሩትን ውሸት እያመኑበት መጥተዋል፡፡ የትህነግ ሰዎች ለራሳቸው የሚነግሩት ውሸት አምነውበት “ኢህአዴግ ቢያንስ 100 አመት በስልጣን ላይ ይቆያል” ሲሉን እንደነበረው፣ የኦህዴድ ብልፅግና ሰዎችም የራሳቸውን ውሸት አምነው እየቃዡ ነው፡፡ እነ መለስ ዜናዊና በረከት ስምኦን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማስተማር ሲንደፋደፉ ቆይተው እንደተሸነፉት፣ እነ አብይም የኢትዮጵያ ታሪክ አስተማሪዎች ሆነው ብቅ ብለዋል፡፡
ትልቁ ሀገራዊ ፈተናችን የትህነግ ሰዎች ሲሸነፉ ሀገርን ዋጋ እንዳስከፈሉት ሁሉ እነዚህም ኢትዮጵያን ዋጋ የሚያስከፍል መርዝ እየተከሉ መሆኑ ነው፡፡
እነ መለስ "ምን ያመጣሉ?" ብለው የቡድን ጥቅም ሲያግበሰብሱ እንደነበረው እነ አብይ የአገር መዲናን ጭምር የመቀማት እብሪት ውስጥ ናቸው!
ለእነሱ ኃላፊነት እንደዚህ ነው! ች በአዲስ አበባ ስም ቁጭ ብላ "የኦሮሚያ ትሁን" እያለች ትቀሰቅሳለች። የምትቀሰቅስበት ስልክ፣ ጊዜው ሆነ ስልጣኑ ሌላው የአዲስ አበባብልፅግና በምግግር ኮ
Posted: 10 Aug 2026, 09:17
by MINILIK SALSAWI
ለእነሱ ኃላፊነት እንደዚህ ነው!
ለስሙ የአዲስ አበባ ከንቲባ ነች! የአዲስ አበባ ህዝብ መሪ ተደርጋ ነው የምትጠራው። ስራዋ ግን አዲስ አበባን ለኦሮሚያ ማስረከብ ነው። በአዲስ አበባ ስልጣን፣ በአዲስ አበባ ሙሉ ሰዓት፣ በአዲስ አበባ ቢሮ፣ በአዲስ አበባ በጀት ለኦሮሚያ እየቀሰቀሰች ነው!
የሰሞኑ የምክክር ኮምሽን ጉዳይ ሲጦፍ የተለያዩ ሰዎች ጋር እየደወለች አዲስ አበባ የኦሮሚያ ተብላ እንዲወሰን ጫና አድርጉ እያለች ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞች ተጠራርተው የመጡትም ለዚህ ይመስላል።
በነገራችን ላይ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ትሁን የሚለውን የኦህዴድ በሴራና ማስፈራሪያ እየተጋፈጡ የሰነበቱት ከተለያየ አካባቢ የመጡ ኢትዮጵያውያዊያን ናቸው። ከእነዚህ መካከል ለማስፈራራትም በገንዘብ ለመደለልም ጥረት ተደርጓል። ልክ አዳነች እንደምታደርገውም እየተደወለ ጫና የሚደርስባቸው አሉ።
አዳነች በአዲስ አበባ ስም ቁጭ ብላ "የኦሮሚያ ትሁን" እያለች ትቀሰቅሳለች። የምትቀሰቅስበት ስልክ፣ ጊዜው ሆነ ስልጣኑ ሌላው የአዲስ አበባ ነው። በአዲስ አበባ ሀብትና ንብረት፣ በአዲስ አበባ ስም ለኦሮሚያ ትሰራለች። ለእነሱ ኃላፊነት እንደዚህ ነው! ለእነሱ ስልጣን እንደዚህ ነው።
“በአዲስ አበባ ላይ ያለንን አቋም አሻሽለናል!” የኦህዴድ ማጭበርበሪያ
የኦህዴድ ማደናገሪያ (Convince እና Confuse) ተጠናክሮ ቀጥሏል! ኦህዴድ ብልፅግና ሰዎችና ጭፍሮቻቸው በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የያዙት ሀገርን መቀመቅ ውስጥ የሚጨምር አጀንዳ በሌሎች ብሄሮች ተወካዮች የጋራ ጥረት ተቀባይነት ሲያጣባቸው ሌላ የማደናገሪያ አጀንዳ ቀይሰው መጥተዋል፡፡ ትናንት የየብሄሩን ተወካዮች በተናጠል እያገኙ “በአዲስ አበባ ላይ ያለንን አቋም አሻሽለናል፤ አዳምጡንና የጋራ እናድርገው” በማለት ሲያደናግሩና ሲቀጥፉ ውለዋል፡፡ ውይይቱን በተናጠል ከየብሄሩ ተወካዮች ጋር ሲሄዱበት ውለዋል፡፡ በተለይ ከአማራ ብልፅግናዎች ጋር ያደረጉት ደግሞ አላማቸውን እስኪያሳኩ ልመናም የታከለበት ነው፡፡ እንደተለመደው ከአሁን ቀደም ከነበሩ የአማራ ክልል አመራሮች እግር ስር በመውደቅ የፓርቲ ሊቀመንበሩነቱንንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱንም ሌላውንም እንደተቆጣጠሩት መሆኑ ነው፡፡ “የለመደች ጦጣ…” ነው ነገሩ! ለምነው "እሽ"ካሰኙ በኋላ በጅልነታቸው ሲስቁባቸው ነው የሚያመሹት። ኦህዴድ ብአዴንን ብዙ ጊዜ አጃጅሎታል።
ኦህዴድ ከተለያዩ አካባቢ ለመጡ የምክክሩ ተሳታፊዎች እየዞረ አግኝቶ “መሬት አንፈልግም፡፡ እኛ መኖር የምንፈልገው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ትምምን (trust) መገንባት አለብን፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባ ስትሰፋ ለሚነፋቀለው ሕዝባችን፣ ቆሻሻ ለሚጣልበት ዕውቅና ስጡልን፡፡ ይህን ደግሞ በፈለጋችሁት ቃል ቀምሩት፡፡” እያሉ እንደተለመደው የማጃጃል ስራቸውን ሲያከናውኑ አምሽተዋል። ይህን እያደረጉ ያሉት ብዙ ያወሩበት ምክክር ኦላ ሊሆን ስለሆነ ነው። ነገርዬው እንደተለመደው ውሻ በቀደደው ጅብ እንደሚባለው፣ የተለየ የኦሮሞን ልዩ ተጠቃሚነት የሚገልፅ ጉዳይ በማስገባት ቀስ በቀስ ለማስፋት ነው፡፡ አንድ እግር በመሬት (one step at a time) የሚበላው የትህነግ ስትራቴጂ መሆኑ ነው፡፡ ሲችሉ በማስፈራራት ካልሆነ ደግሞ በመለመንና በማባበል ዓላማቸውን ለማስፈፀም ሌት ከቀን እየሠሩ ነው፡፡
ለመሆኑ አዲስ አበባ ወዴት ነው የምትሰፋው? ሸገር ከተማ ብለው ያጠሯት መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም እኮ፡፡ ደግሞስ ስለ ቆሻሻ የሚወራው በዚህ ዘመን ቆሻሻ ማዳባሪያና ነዳጅ በመሆኑ አዲስ አበባ ለራሷ ትጠቀምበታለች እንጂ ለምን ወደ ሌላ ቦታ ትወስደዋለች? ዓላማቸው ሌላ ነው፡፡ ዓላማቸው አዲስ አበባን መዋጥ ነው፡፡ ለጊዜው በደላይ ህሊና ስለተጠቁ አይገባቸውም እንጂ ይህ ደግሞ ለእነሱም አይጠቅምም፡፡
ኦህዴድ ብልፅግናዎች ዛሬም የተመለደውን የማደናገሪያ ስትራቴጂያቸውን በመቀጠል “ይህን ካላደረግን የኦሮሞ ወጣት አያስቀምጠንም” እያሉ ነው፡፡ “የአዲስ አበባ ወጣትስ? የአማራ ወጣትስ? የትግራይ፣ የአፋር፣ የሶማሊ፣ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ወጣትስ? የሲዳማ ወጣትስ? የደቡብ ወጣትስ? የጋምቤላ፣ የቤንሻንጉል፣ የደቡብ ምእራብ ወጣትስ?” ተብለው መጠየቅ አይፈልጉም፡፡ “መላው የኢትዮጵያ ህዝብስ? በላብና በደማቸው ከተማዋን የገነቧት አዲስ አበቤዎችስ?” የሚል የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄ የሚያነሳባቸው ጠላታቸው ነው፡፡
እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባን ጉዳይ ከቀሩት 500 ተወያዮች ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የብልፅግና አባላትና አመራሮች ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ አጀንዳ አደራጅተው ለ500 ተሳታፊዎች እንዲያቀርቡና ድምጽ እንዲሰጥበት ከተመረጡት ሰዎች ውስጥ ደግሞ ከ96 በመቶ በላይ የብልፅግና አባላት ናቸው፡፡ እንግዲህ አዲስ አበባን በተመለከተ መስማማት ያልቻሉት ራሳቸው ብልፅግናዎች ናቸው፡፡ በብልፅግና ደረጃ የፓርቲ አቋም ተብሎ በራሱ በአብይ አህመድ የተሰጠ ስልጠና ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከኦህዴድ ብልፅግና ውጪ ያሉት በሙሉ የአዲስ አበባ ጉዳይ በልዩ ጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡ አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያውያን መሆኗ በማያሻማ መልኩ መቀመጥ አለበት፡፡ ከዚያም አልፎ የአፍሪካ መዲና ናት፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ህልውና ተቋጥሮ ያለው አዲስ አበባ ላይ ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵየን ህልውና ማስቀጠል የምንፈልግ ከሆነ የአዲስ አበባን የመላው ኢትዮጵያውያን ከተማነት ማረጋገጥ አለብን፡፡ ካልሆነ ችግር እንፈታለን ብለን ከባድ ችግር እንፈጥራለን፡፡ ሀገር እናድናለን ብለን ሀገር የሚያፈርስ መርዝ እንተክላለን፡፡” በማለት ሲከራከሩ ሰንብተዋል፡፡
የአማራ ብልፅግና አባላት የአዲስ አበባን ጉዳይ አሳልፎ ሰጥቶ ሊገጥመው የሚችለውን ተጨማሪ ትግልና እዳ ያውቀዋል፡፡ የሌላው ብሄር ተወካይም በየህዝቡ መጠየቁ አይቀሬ ነው፡፡ ስለሆነም ህሊና ያለው ለሀገሩና ለወገኑ ማሰብ ነበረበት። ግን ለራሱ ለግሉ ብሎ (ከታሪክ ተጠያቂነትም ጭምር ለመዳን) ሽንጡን ገትሮ መታል ይገባ ነበር፡፡ ትግሉ የእኩልነትና የፍትህ ትግል በመሆኑ ክቡር ትግል ነው፡፡ እንደተለመደው የኦህዴድ ብልፅግና (Convince እና Confuse) ስትራቴጂ ሰለባ የሚሆን ካለ እዳው ለሀገርም፣ ለቤተሰብም፣ ለራስም ነው መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
የብልፅግና አንጃዎች ኦህዴድ ስላጃጃላቸው፣ የህዝብ አላማ ስለሌላቸው ቢተውት ትግሉ የህዝብ ነው። የአዲስ አበባ ጉዳይ አገር የማስቀጠል ጉዳይ ነው። ዘር ፍጅትን ቀድሞ የመከላከል ትግል ነው። ትግሉ ለእኩልነት በሚታገሉ እና እኩልነትን በሚታገሉ መካከል ነው፡፡ ትግሉ ለፍትህ በሚታገሉ እና ፍትህን በሚታገሉ ሃይሎች መካከል ነው፡፡ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ዘላቂ ህልውና የሚጠቅመው እኩልነትና ፍትህ አሸናፊዎች ሆነው ሲወጡ ብቻ ነው፡፡
ለአዲስ አበባ የተሻለው መፍትሔ የአዲስ አበባ ሁኔታ፣ ታሪካዊ ክርክርና የጋራ መፍትሔ:_
Posted: 10 Aug 2026, 09:20
by MINILIK SALSAWI
ለአዲስ አበባ የተሻለው መፍትሔ
የአዲስ አበባ ሁኔታ፣ ታሪካዊ ክርክርና የጋራ መፍትሔ:_
አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ ያላት ከተማ ነች። የከተማዋ ታሪካዊ አመጣጥ፣ የመሬት ታሪክ እና የማንነት ጥያቄ ከአማራና ኦሮሞ ታሪካዊ ትርክቶች ጋር ተያይዞ ለረጅም ጊዜ ክርክር ያስነሳ ጉዳይ ነው። የተለያዩ ቡድኖች ስለከተማዋ ታሪካዊ አመጣጥና ግንኙነት የተለያዩ ትርክቶችና አተያዮች አሏቸው። ይህንን ውስብስብ ታሪካዊ ጉዳይ በአንድ ወገን የባለቤትነት ትርክት ብቻ ለመፍታት መሞከር የተጨማሪ ፖለቲካዊና ሕገ-መንግሥታዊ ክርክር ያመጣል። ስለዚህ ዘላቂ መፍትሔ አንዱን ወገን አሸናፊ እና ሌላውን ተሸናፊ ከማድረግ ይልቅ የሁሉንም ጥቅም የሚያስተናግድ የጋራ አሸናፊነትን የሚያረጋግጥ (win-win) የሕገ-መንግሥታዊ አቀራረብ መፍጠር ነው። በዚህ አቀራረብ አዲስ አበባ የአንድ ክልል ዋና ከተማ ከመሆን ይልቅ ራስ-ገዝ እና የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ ሆና መቆየት ይገባታል።
ይህ ማለት የኦሮሚያን ሕጋዊና ታሪካዊ ጥቅሞች መካድ አይደለም፤ እንዲሁም የአማራ ሕዝብ ከከተማዋ ጋር የሚያያዙ ታሪካዊና ባህላዊ ትርክቶችን መካድ አይደለም። ይልቁንም የተለያዩ ታሪካዊ ትርክቶች በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲኖሩ የሚያስችል የጋራ መድረክ መፍጠር ነው።
በዚህ መሠረት ኦሮሚያ ወይም ማንኛውም ሌላ ክልል በአዲስ አበባ የመንግሥት ተቋም፣ የአስተዳደር መቀመጫ ወይም ተወካይ ቢሮ ለማቋቋም ከፈለገ፣ ይህ በከተማዋ ራስ-ገዝነትና በከተማ ምክር ቤቱ ፈቃድ መሠረት ሊፈጸም ይችላል። እንዲህ ያለው ሥርዓት አዲስ አበባን የአንድ ክልል ዋና ከተማ ሳያደርጋት፣ ለሁሉም ክልሎች እኩል የሆነ የፌዴራል መዲና እንድትሆን ያስችላል።
ይህ አቀራረብ የአማራና የኦሮሞ ታሪካዊ ትርክቶችን በአንድ ወገን የባለቤትነት ውድድር ውስጥ ከማስገባት ይልቅ፣ አዲስ አበባን የጋራ የፌዴራል መዲና አድርጎ በመያዝ የጋራ ጥቅም እንዲፈጠር ያደርጋል። ኦሮሚያ በከተማዋ የሚኖረውን ሕጋዊ ግንኙነትና ጥቅም ማስጠበቅ ትችላለች። አማራም ሆነ ሌሎች ክልሎች ከፌዴራል መዲናዋ ጋር እኩል ተቋማዊ ግንኙነት ይኖራቸዋል። በዚህም አዲስ አበባ የግጭት ምንጭ ከመሆን ይልቅ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገናኙበት፣ የሚተባበሩበት እና የጋራ ጥቅም የሚያሳድጉበት የፌዴራል መድረክ እንድትሆን ያስችላታል።
በመጨረሻም፣ የአዲስ አበባ ጉዳይ የአንድ ብሔር ወይም የአንድ ክልል የበላይነት ጉዳይ ከመሆን ይልቅ የፌዴራል ሥርዓቱ እንዴት የተለያዩ ታሪካዊ ትርክቶችን፣ የነዋሪዎችን መብት፣ የክልሎችን ጥቅም እና የከተማዋን ራስ-ገዝነት በአንድነት ሊያስተናግድ እንደሚችል የሚፈትን ጉዳይ ነው። ራስ-ገዝ የፌዴራል መዲና፣ ለሁሉም ክልሎች እኩል ተደራሽነት፣ እና የከተማ ምክር ቤቱ የመፍቀድ ሥልጣን የሚያጣምረው አቀራረብ የታሪካዊ ክርክሩን ወደ የጋራ ጥቅም፣ ትብብርና አንድነት ሊቀይር የሚችል የጋራ ድል (win-win) መፍትሔ ይሆናል።
የ“ልዩ ጥቅም” ጽንሰ-ሐሳብ ችግር፦
በአዲስ አበባና በኦሮሚያ መካከል የሚነሳውን ጉዳይ በትክክል ለመተንተን “ልዩ ጥቅም”፣ “የመንግሥት መቀመጫ” እና “የክልል ዋና ከተማ” የሚሉት ጽንሰ-ሐሳቦች በግልጽ መለየት ይገባል። እነዚህ ተመሳሳይ የሕግ ወይም የአስተዳደር ጽንሰ-ሐሳቦች አይደሉም።
በሕገ-መንግሥቱ የተጠቀሰው “የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም” በቀጥታ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ዋና ከተማ የሚያደርግ ወይም በከተማዋ ላይ የክልሉን የአስተዳደር ሥልጣን የሚያቋቁም ጽንሰ-ሐሳብ አይደለም። ልዩ ጥቅም ከከተማዋ ጋር በተያያዙ የኦሮሚያ ሕጋዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ልማታዊ ጥቅሞች ላይ የሚመሠረት ልዩ ግንኙነት ተደርጎ መታየት ይችላል።
በተለይም አዲስ አበባ በጂኦግራፊ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በቀጥታ የተከበበች በመሆኗ፣ የከተማዋ የኢኮኖሚና የከተማ ልማት እድገት በአካባቢው ያሉ የኦሮሚያ ማኅበረሰቦችና ከተሞች ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። የመጓጓዣ መስመሮች፣ የመሬት አጠቃቀም፣ የውሃና የኃይል አቅርቦት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የንግድና የሥራ ገበያ ግንኙነት እና የከተማ መስፋፋት የመሳሰሉ ጉዳዮች የከተማዋን እና የአካባቢዋን ክልል በተቀናጀ መልኩ እንዲታዩ ያስፈልጋል።
ስለዚህ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ዋና ከተማ ማድረግ ወይም የክልሉን የአስተዳደር ሥልጣን በከተማዋ ላይ ማስፋፋት የግድ አይደለም። ይልቁንም የከተማዋ እና የኦሮሚያ ክልል የጋራ ኢኮኖሚያዊና ልማታዊ ጥቅሞችን የሚያስተናግድ የተቋማዊ ትብብር ሥርዓት መፍጠር ይበልጥ ተገቢ ነው። ይህም በዋናነት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትና በኦሮሚያ ሕዝብና ተወካዮቹ መካከል በተቋማዊ ውይይትና በስምምነት መፍታት የሚገባው ጉዳይ ነው። እንደ ጉዳዩ ባሕርይ የፌዴራል መንግሥት የማስታረቅ፣ የማስተባበርና የጋራ ልማት ማዕቀፍ የመፍጠር ሚና ሊኖረው ይችላል።
ይህ አቀራረብ የኦሮሚያ ክልልን ጥቅም በተግባራዊና በኢኮኖሚያዊ መልኩ እንዲጠበቅ ያደርጋል። በተመሳሳይም የአዲስ አበባን ራስ-ገዝነትና የከተማዋን የዴሞክራሲ አስተዳደር ሳይጎዳ የከተማዋ እድገት በአካባቢዋ ላይ የሚያመጣው ጥቅምና ተጽዕኖ በጋራ እንዲታይ ያስችላል።
በዚህ መልኩ “ልዩ ጥቅም” የአንድ ከተማ የባለቤትነት ወይም የክልላዊ የበላይነት መሠረት ሳይሆን፣ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ የአካባቢ ልማት፣ ትብብርና የጋራ ኃላፊነት ለመፍጠር የሚያገለግል ሕገ-መንግሥታዊ መርህ ሊሆን ይገባል። ይህ አዲስ አበባን የግጭት ማዕከል ከማድረግ ይልቅ በኦሮሚያ፣ በሌሎች ክልሎች እና በፌዴራል መንግሥት መካከል የልማት፣ የትብብርና የአንድነት መድረክ እንድትሆን ያግዛል።
ከኦሮሚያ ጋር ያለው ልዩ ግንኙነት የከተማዋን ራስ-ገዝነት፣ የነዋሪዎችን እኩል የዴሞክራሲ ተሳትፎ ወይም የከተማ ምክር ቤቱን ሥልጣን ከገደበ የዴሞክራሲ መርሆችን የሚጎዳ ነው።
የአዲስ አበባ ራስ-ገዝነትና የዴሞክራሲ መርሆዎች
አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ በመሆኗ ከማንኛውም ክልላዊ መንግሥት የተለየና ራስ-ገዝ የሆነ ሕገ-መንግሥታዊ ደረጃ ሊኖራት ይገባል። ይህም ከተማዋ የራሷን ጉዳይ በራሷ በመምረጥ በሚመጣ የከተማ አስተዳደር እንድትመራ እና የነዋሪዎቿ የዴሞክራሲ ተሳትፎ በራሳቸው በመረጡት ተወካዮች እንዲገለጽ ያስፈልጋል።
በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ጋር የተያያዙ ማናቸውም ልዩ ድንጋጌዎች የአዲስ አበባን ራስ-ገዝነት እና የከተማውን ምክር ቤት ሕጋዊ ሥልጣን በሚገድቡበት መጠን በጥንቃቄ ሊታዩ ይገባል። የአንድ ክልል ልዩ ጥቅም ወይም ልዩ የውሳኔ ሥልጣን በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ከተመረጡ የከተማ ተወካዮች ሥልጣን በላይ እንዲሆን ከተደረገ፣ ይህ የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የእኩልነት እና የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያዛባል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማዋን አስተዳደር በነፃና በእኩል መርህ የሚመርጡ ከሆነ፣ የከተማዋ ውስጣዊ ጉዳዮች በዋናነት በከተማው ምክር ቤትና በሌሎች በሕግ የተቋቋሙ የከተማ ተቋማት መወሰን አለባቸው። ከኦሮሚያ ጋር ያለው ልዩ ግንኙነት ይህንን የዴሞክራሲ መርህ ሊያስቀር ወይም ሊያዳክም የሚችል የበላይ የአስተዳደር ሥልጣን ለክልሉ ሊሰጥ አይገባም።
በሌላ በኩል፣ ይህ ማለት የኦሮሚያ ሕዝብ ወይም ክልላዊ መንግሥት ሕጋዊ ጥቅሞች መታወቅ የለባቸውም ማለት አይደለም። ሕገ-መንግሥቱ የሚያውቀው ልዩ ግንኙነት በእኩልነት፣ በዴሞክራሲ፣ በሕግ የበላይነት እና በአዲስ አበባ ራስ-ገዝነት መርሆዎች ውስጥ መተግበር ይገባዋል።
በመሆኑም ተገቢው አቀራረብ አዲስ አበባን ራስ-ገዝ፣ የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ እና ለሁሉም ክልሎች እኩል የሆነ የፌዴራል መዲና አድርጎ ማየት ያስፈልጋል። ከኦሮሚያ ጋር ያለው ልዩ ግንኙነትም የከተማዋን ራስ-ገዝነት ሳይገድብ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች የዴሞክራሲ መብቶች ሳያዳክም እና የተመረጡ የከተማ ተቋማትን ሥልጣን ሳያሳንስ መከናወን ይገባዋል።
በተጨማሪም፣ አንድ የክልል መንግሥት የመንግሥት አስተዳደራዊ መቀመጫውን ወይም የተወሰነ የመንግሥት ተቋሙን በአዲስ አበባ ለማቋቋም ከፈለገ፣ ይህ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ፈቃድና በከተማዋ ሕጎች መሠረት መፈጸም ይገባል። ይህ አቀራረብ የከተማዋን ራስ-ገዝነት ከማክበር በተጨማሪ፣ በፌዴራል ሥርዓቱ ውስጥ በክልሎች መካከል ያለውን የመንግሥታት-መካከል ግንኙነት (intergovernmental relations) እና ትብብር ያጠናክራል። በዚህ መልኩ አዲስ አበባ የአንድ ክልል ማዕከል ሳትሆን፣ ሁሉም ክልሎች በእኩልነት ሊጠቀሙባት የሚችሉት የፌዴራል መዲና ሆና ትቆያለች።
ይህ አቀራረብ በረጅም ጊዜ ሊነሱ የሚችሉ የአዲስ አበባ ደረጃ፣ የክልሎች መቀመጫ እና የመንግሥታት-መካከል ግንኙነት ጥያቄዎችን በተመጣጣኝና በዘላቂ መልኩ ለመፍታት ያስችላል። እያንዳንዱ ክልል የአስተዳደራዊ መቀመጫውን በአዲስ አበባ ለማቋቋም እንዲችል፣ በከተማዋ ራስ-ገዝነት እና በከተማ ምክር ቤቱ ሕጋዊ ሥልጣን መሠረት የሚደረግ ሥርዓት መዘርጋት ከአንድ ክልል ጋር ብቻ የተያያዘ መፍትሔ ከመፍጠር ይልቅ ለሁሉም ክልሎች የሚሠራ የጋራ መርህ ይፈጥራል።
በአንፃሩ፣ አዲስ አበባን በአንድ የክልል ሕገ-መንግሥት ውስጥ የዚያ ክልል ዋና ከተማ አድርጎ መደንገግ፣ ለምሳሌ በኦሮሚያ ክልል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 6 ላይ እንደ ክልሉ ዋና ከተማ ማካተት፣ ከአዲስ አበባ ራስ-ገዝነትና ከፌዴራል መዲናነቷ ጋር የሚፈጠሩ የሕግና የሥልጣን ግጭቶችን ያስነሳል። ከዚህ በላይም፣ እንዲህ ያለ አቀራረብ ለሌሎች ክልሎች ተመሳሳይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርግ የሕግና የአስተዳደር ምሳሌ ሊፈጥር ይችላል።
ስለዚህ የአዲስ አበባን ደረጃ ከአንድ ክልል ጋር ብቻ በማያያዝ ከመወሰን ይልቅ፣ ከተማዋን ራስ-ገዝና የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ አድርጎ በማስቀመጥ፣ ማንኛውም ክልል በከተማ ምክር ቤቱ ፈቃድ እና በጋራ የሕግ ሥርዓት መሠረት በአዲስ አበባ የመንግሥት ተቋም ወይም አስተዳደራዊ መቀመጫ እንዲኖረው መፍቀድ ይበልጥ ዘላቂ መፍትሔ ነው። ይህ የአንድ ክልል ልዩ ጥቅምን ከማስጠበቅ ይልቅ ለሁሉም ክልሎች እኩል የሚተገበር መርህ በመፍጠር፣ ትብብር፣ እኩልነትና መረጋጋት ያጠናክራል።
፤ “የመንግሥት መቀመጫ” እና “የክልል ዋና ከተማ” ተመሳሳይ የሕግ ጽንሰ-ሐሳቦች አይደሉም።
የመንግሥት መቀመጫና የክልል ዋና ከተማ የሕግ ልዩነት
በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል መካከል የሚነሳውን የደረጃና የመቀመጫ ጥያቄ ለመረዳት “የመንግሥት መቀመጫ” እና “የክልል ዋና ከተማ” የሚሉትን ሁለት ጽንሰ-ሐሳቦች መለየት ያስፈልጋል።
የመንግሥት መቀመጫ (seat of government) ማለት የአንድ መንግሥት ዋና የአስፈፃሚ፣ የሕግ አውጪ እና የሌሎች የመንግሥት ተቋማት አስተዳደራዊ ማዕከል የሚገኝበት ቦታ ነው። ይህ በራሱ የከተማዋን ሕጋዊ ሉዓላዊነት ወይም የሌላ አካል ክልላዊ ባለቤትነት አያመለክትም። ሌላ መንግሥት በአንድ ከተማ ውስጥ የመንግሥት ተቋማቱን ማስቀመጥ መቻሉ ከዚያ ከተማ የሕገ-መንግሥታዊ ደረጃ ጋር በራሱ አይቃረንም።
በአንፃሩ የክልል ዋና ከተማ (state/regional capital) ማለት የአንድ ክልል የፖለቲካና የአስተዳደር ማዕከል የሆነች ከተማ ነች። ይህ ሁኔታ ከክልሉ የግዛት እና የአስተዳደር ሥልጣን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። ስለዚህ አንድ ከተማን የክልል ዋና ከተማ ብሎ መደንገግ ከተማዋ የክልሉ አስተዳደራዊ ማዕከል መሆኗን ከማሳየት በላይ የክልሉን ሥልጣንና የከተማዋን የራስ-ገዝ ሥርዓት በሚመለከት የሕግ ጥያቄዎችን ሊያስነሳ ይችላል።
ይህንን ልዩነት ከአዲስ አበባ አንፃር ስንመለከት፣ አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ እና ሙሉ የራስ-ገዝ አስተዳደር ያላት ከተማ መሆኗ ከማንኛውም ክልል ዋና ከተማ ከመሆን የተለየ የሕገ-መንግሥታዊ ባህሪ ይሰጣታል። በመሆኑም አንድ ክልል በአዲስ አበባ የመንግሥት ተቋማቱን ወይም የአስተዳደር መቀመጫውን ማቋቋም ከተማዋን የዚያ ክልል ዋና ከተማ ከማድረግ ፍጹም የተለየ ጉዳይ ነው።
በዚህ መሠረት፣ ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ የክልሉን የመንግሥት ተቋማት ለማስቀመጥ ወይም ከተማዋን ለአስተዳደራዊ መቀመጫነት ለመጠቀም የሚፈልግ ከሆነ፣ ይህ በከተማዋ ራስ-ገዝነት እና በከተማ ምክር ቤቱ ሥልጣን መሠረት ሊፈጸም ይችላል። ይህ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ አያደርጋትም፤ እንዲሁም የከተማዋን የራስ-ገዝ ሕገ-መንግሥታዊ ደረጃ አይቀይርም።
ይህ አቀራረብ ከአንድ ክልል ጋር ብቻ የተያያዘ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ ለሁሉም ክልሎች በእኩልነት የሚተገበር መርህ ይፈጥራል። ማንኛውም ክልል በአዲስ አበባ የመንግሥት መቀመጫ፣ ተወካይ ቢሮ ወይም ሌላ የአስተዳደር ተቋም ማቋቋም ከፈለገ፣ ይህ በከተማው ምክር ቤት ፈቃድና በከተማዋ ሕጎች መሠረት ሊፈጸም ይችላል። ይህም የአዲስ አበባን ራስ-ገዝነት እያከበረ በተመሳሳይ ጊዜ በፌዴራል ሥርዓቱ ውስጥ የመንግሥታት-መካከል ግንኙነትን፣ ትብብርንና ተቋማዊ ቅርበትን ያጠናክራል።
ስለዚህ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ዋና ከተማ ማድረግ ወይም የክልሉን የአስተዳደር ሥልጣን በከተማዋ ላይ ማስፋፋት የግድ አይደለም። ይልቁንም የከተማዋ እና የኦሮሚያ ክልል የጋራ ኢኮኖሚያዊና ልማታዊ ጥቅሞችን የሚያስተናግድ የተቋማዊ ትብብር ሥርዓት መፍጠር ይበልጥ ተገቢ ነው።
ይህም በዋናነት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትና በኦሮሚያ ሕዝብና ተወካዮቹ መካከል በተቋማዊ ውይይትና በስምምነት መፍታት የሚገባው ጉዳይ ነው። እንደ ጉዳዩ ባሕርይ የፌዴራል መንግሥት የማስታረቅ፣ የማስተባበርና የጋራ ልማት ማዕቀፍ የመፍጠር ሚና ሊኖረው ይችላል።
ይህ አቀራረብ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ከመካድ ይልቅ በተግባራዊና በኢኮኖሚያዊ መልኩ እንዲጠበቅ ያደርጋል። በተመሳሳይም የአዲስ አበባን ራስ-ገዝነትና የከተማዋን የዴሞክራሲ አስተዳደር ሳይጎዳ የከተማዋ እድገት በአካባቢዋ ላይ የሚያመጣው ጥቅምና ተፅዕኖ በጋራ እንዲታይ ያስችላል።
በዚህ መልኩ “ልዩ ጥቅም” የአንድ ከተማ የባለቤትነት ወይም የክልላዊ የበላይነት መሠረት ሳይሆን፣ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ የአካባቢ ልማት፣ ትብብርና የጋራ ኃላፊነት ለመፍጠር የሚያገለግል ሕገ-መንግሥታዊ መርህ ሊሆን ይገባል። ይህ አዲስ አበባን የግጭት ማዕከል ከማድረግ ይልቅ በኦሮሚያ፣ በሌሎች ክልሎች እና በፌዴራል መንግሥት መካከል የልማት፣ የትብብርና የአንድነት መድረክ እንድትሆን ያግዛል።
ቀጣዩ ዘር ፍጅት ለሁሉም የሚያሰጋ ነው!
Posted: 11 Aug 2026, 23:31
by MINILIK SALSAWI
ቀጣዩ ዘር ፍጅት ለሁሉም የሚያሰጋ ነው!
ማንኛውም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ የአንድን ወገን የፖለቲካ ጥያቄ ለማስፈጸም ወይም አዲስ የታሪክ ውዝግብ ለመፍጠር ሊውል አይገባም። የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ዋና ዓላማ የአገሪቱን የሕግ ሥርዓት ማጠናከር፣ የሥልጣን ወሰኖችን በግልጽ መወሰን፣ የዜጎችን እኩል መብት ማረጋገጥ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰላም ማስፈን እና ዘላቂ ልማትን ማስቻል መሆን አለበት።
ዓለም አቀፍ ተሞክሮው ይህ ነው። ከእውነትና ህግ የተጣላው ኦህዴድ ደግሞ ህግ ማሻሻል የፈለገው ለቡድናዊ ጥቅም ነው። ኦህዴድ ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ ማሻሻያ የሚፈልገው ቀጣይ ውዝግብን በመፍጠር ነው።
በተለይም የአዲስ አበባን ሕገ መንግሥታዊ ሁኔታ የሚመለከት ማሻሻያ፣ ከተማዋን በክልላዊ ቁጥጥር ሥር በማስገባት ወይም የነዋሪዎቿን የራስ-አስተዳደር መብት በመቀነስ አዲስ የባለቤትነት ክርክር የሚያስነሳ እንዳይሆን በርካቶች ሲቃወሙ ቆይተዋል። አሁንም እየተቃወሙ ነው። ይልቁንም የከተማዋን የፌዴራል ዋና ከተማነት፣ የነዋሪዎቿን ሙሉ የራስ-አስተዳደር መብት እና የኦሮሚያን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም በግልጽና በሚያስተማምን የሕግ ማዕቀፍ ማስታረቅ አለበት እያሉ ነው። ኦህዴድ ደግሞ በማጭበርበር፣ በማስፈራራት ከፌደራል ዋና ከተማነት አውርዶ፣ የነዋሪዎቿን መብት ነጥቆ፣ የራስ አስተዳደር መብትን ገፍፎ አንዴ በክልል ስር፣ ሌላ ጊዜ የጋራ ጥቅም እያለ እያወናበደ ነው።
ማሻሻያ መሠረት የታሪክ ትርክትን ለአንድ ወገን ማስረከብ ሳይሆን፣ ለሁሉም ዜጎች የሚሠራ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ዘላቂ የሕግ ሥርዓት መገንባት መሆን ሲኖርበት ኦህዴድ ግን አዲስ አበባን ከህዝብ ነጥቆ ከአሁን ቀደም እንደተናገሩት እርባና "እርባና ቢስ ማድረግ" ነው። የቡድን ጥቅምን ለማጋበስ ተብሎ የሚደረግ ማሻሻያ የነገን ትውልድ አዲስ የባለቤትነት፣ የወሰን እና የማንነት ግጭት ውስጥ የሚጥል፣ እንደ ኦህዴድ ልምድና አካሄድ ለዘር ፍጅት የሚዳርግ ነው። ይህም በመሰረታዊነት የህግ የማሻሻያውን ዋና ዓላማ የሚቃረን ነው። የኦህዴድ አካሄድ ህግን፣ ዓለም አቀፍ ተሞክሮን፣ እውነትን ጨምሮ በጎ ነገሮችን ሁሉ የሚቃረን ነው።
በአጭሩ፣ ሕገ መንግሥት መሻሻል ያለበት ሰላምንና ልማትን ለረጅም ጊዜ ለማስጠበቅ እንጂ፣ አዲስ ታሪካዊ ውዝግብና የፖለቲካ ግጭት ብሎም የዘር ፍጅት ማዘጋጃ አይደለም።
ኢትዮጵያውያንም የኦህዴድን አካሄድ አምርረው መቃወም ያለባቸው መሰረታዊ የህግ ማሻሻያ ትርጉምን አዛብቶ ለዘር ፍጅት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መጨቆኛ ስርዓት ግንባታው ማንም ላይ የሚደርስ መሆኑ ነው። በእርግጥም ሁሉም የሚኖሩባት አዲስ አበባ ላይ የሚፈፅመውና በቀጣይ ያሰበው ሁሉም ኢትዮጵያ ላይ የተቃጣ እንደሆነ ግልፅ ነው። የዘር ፍጅት ዝግጅትን በማሻሻያና ምክክር ስም ሲያመጡት ጉራጌውም፣ ዶርዜውም፣ ሶማሊውም ሌላውም የጥቃቱ ሰለባ ነው። ባለፉት አመታት ከአዲስ አበባ የተገፋው ሁሉ በቀጣይ የህግ ሽፋን ሲያገኙ የባሰ ነገር ይገጥመዋል።