ይህ ዘመን የፍርድ ወይም የስምንተኛዉ ሺህ ዘመን ነዉ ተብሏል።
ክርስትያኖች መጽሓፉን ኣንብባችሁ በቀላሉ የሚገባችሁ መሆን ኣለባችሁ።
ስለዚህ በዚህ የፍርድ ወይም የስምንተኛዉ ሺህ ዘመን እስቲ በጣም ቀላል ጥያቄ መልሱ።
መጽሓፉ ዉስጥ የተጻፉትን የስደት ዘመን እና የስቅለት ዘመን ክፍሎች ብቻ መልሳችሁ መላልሳችሁ ኣንብቡ።
መላልሳችሁ ካነበባችሁ በኋላ በዚህ ዘመን እግዝኣብሔር ፊት ለፊታችሁ ፍንትዉ ኣድርጎ እንደ መስታዉት ዉስጥ የምያሳያችሁ የትኛዉን ዘመን ነዉ ትላላችሁ?
ኣማኝ የሆነችሁ ሁሉ ይህን ኣስተያየት ማንበብ እዚሁ ኣቁሙ እና የእራሳችሁን መልስ ካገኛችሁ በኋላ የሚከተለዉን የእኔን ኣስተያየት ኣንብቡ።
የእኔ ግምት፥
1) በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ዉስጥ እና ከኢትዮጵያ ዉጪ የሚታየኝ የኢትዮጵያዊያን ሁኔታ የምያስታዉሰዉ እና ፍንትዉ ኣድርጎ የምያሳየዉ የስድት ዘመን መከራን ነዉ።
2) የኢትዮጵያዊያን ወዲህ ወድያ መባዘን፣ የማያይ እግዝኣብሔር ዬለም ማለት እና ተዓምራትን የምያሳይ እግዝኣብሔር ቢኖር ነዉ ማለት የስደት ዘመንን መገለጥ ነዉ።
3) እግዝኣብሔር ኣለ ብሎ ማሰብ የኣዕምሮ መዛበት ነዉ ማለት እና ቀድሞ ኣይቶ ኣስቀድሞ የምያሳይ እግዝኣብሔር የምያይ ቢሆን ነዉ ማለት የስደት ዘመንን ነዉ።
4) እግዝኣብሔር ዬለም እያለ እየሱስ በሉኝ ያለ የስደት ዘመን የኣሕዛብ ጣዖትነት ይመስላል።
5) ቅዱስ መንፈስ ኢትዮጵያዊያንን ለማሰባሰብ ሲለፋ እርኩስ መንፈስ ኢትዮጵያዊያንን ለማዋከብ ይለፋል።
ስለ ፍርድ ዘመኑ እጅግ የሚገርመዉ እግዝኣብሔር ዬለም ብሎ እየሱስ በሉኝ ያለዉ፥
1) ሕዝብ መሃል ገብቶ እየተራወጠ ሕዝብን የምያወራጭ መሆኑ፣
2) እግዝኣብሔር ኣለ ብለዉ የምያምን ቤተሰብ መሃል ገብቶ እየሱስ በሉኝ ማለቱ ጥቂቶች ናቸዉ።