Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

"አዲስ አበባ የኦሮሞ ካልሆነች አገር ይበጠበጣል" የዛቻ ኮምሽን / የምክክር ኮምሽን ተብሎ ብዙ የሚወራለት የዛቻ ኮምሽን ሆኗል።

Post by MINILIK SALSAWI » 04 Aug 2026, 23:54

"አዲስ አበባ የኦሮሞ ካልሆነች አገር ይበጠበጣል" የዛቻ ኮምሽን
የምክክር ኮምሽን ተብሎ ብዙ የሚወራለት የዛቻ ኮምሽን ሆኗል። እየዛተ ነው። ኮምሽኑ ለተወያዮቹ ሀሳቦችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ተብሎ "ምሁራን" የሚባሉ አሉት። ራሱ ኮምሽኑ የመደባቸው። እነዚህ ምሁራን የተባሉት ታዲያ ሀሳብ የሚያፍታቱ ሳይሆኑ የኦሮሞ ብልፅግናን አቋም ካልተቀበላችሁ ጉድ ይፈላል ብለው የሚዝቱ ናቸው። እነዚህን በተወያዮቹ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ላይ የሚዝቱ ምሁራን ተብየዎች የመደባቸው ምክክር ኮምሽኑ ነው። አምኘባቸዋለሁ ብሎ ነው። በእሱ ፈቃድ፣ ራሱ እያየ ነው "ይህን ካልተቀበላችሁ አገር ይበጠበጣል፣ ይፈርሳል" የሚሉት። ስለሆነም እየዛተ ያለው ኮምሽኑ ራሱ ነው። ራሱ ያዋቀረው፣ የራሱ አንድ ክፍል ነው እየዛተ ያለው!
በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ምሁር ተብዬዎቹ የቀረቡትን አማራጮች ከማስረዳት ይልቅ "የኦሮሚያ ብትሆን ይሻላል" ብለው በማያገባቸው ገብተው ውሳኔ እያስተላለፉ ይገኛል። አዲስ አበባ የኦሮሚያ ካልሆነች "አገር ይበጠበጣል" እያሉ እየዛቱ ነው ምክክር ወዘተ የሚሉን። ደግሞ ከመላ ኢትዮጵያ ለዚህ ተግባር ሰው ጠፍቶስ ነው ከአንድ ብሔር ብቻ ምሁር ተብሎ የሚቀርበው?
"አዲስ አበባ የኦሮሚያ መሆን አለባት" ብሎ በግድ ለመወሰን፣ በኃይል ለመጫን ጨፌ ኦሮሚያም፣ የኦህዴድ ስራ አስፈፃሚም፤ አብይ፣ ሽመልስና አዳነችም በቂ ናቸውኮ። ይህን ለመዛት ምክክር ኮምሽን ብሎ ማወናበድ አያስፈልግም። ከየአቅጣጫው 4000 ሰው መሰብሰብ አያስፈልግም! ይህን ሁሉ ጊዜና ሀብት ማባከን አያስፈልግም። እስካሁን ተረኞቹ በፈጣጣው ከሄዱበት የተለየ ነገር የለውም። ምክክሩ ማስመሰያ ነበር። አሁን እንደነ አብይ፣ እንደነ ሽመልስ እየዛተ ነው። የዛቻ ኮምሽን ሆኗል።
ለዛቻ ከሆነማ ብርሃኑ ጁላ አሁን ካለው ስልጣን በተጨማሪ የኮምሽኑ ኮምሽነር አታደርጉትም?

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ምክክር አይሰራም ተብላችኋል!

Post by MINILIK SALSAWI » 05 Aug 2026, 00:21

ምክክር አይሰራም ተብላችኋል!

ምክክሩን ለማስመሰያነት ሊጠቀም የነበረው ኦህዴድ "ምክክር አይሰራም" ብሎ በፈጣጣም መጥቷል። ተሳታፊውን አስፈራርቷልም። ነገሩ እንዲህ ነው። የአዲስ አበባን ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። በብልፅግና ከተለያዩ ክልሎች የመጡት ተሳታፊዎች ጭምር "አዲስ አበባ የሁላችን ከተማ ነች" አሉ። ኦህዴድ ይደግፉኛል ያላቸው ጭምር የፌደራል ከተማ መሆን አለባት በሚለው ተስማማ። የኦሮሚያ የሚባል አይሰራም ተባለ።

ከዛማ ኦህዴድ ክተት አወጀ። እንደተለመደው። የአዲስ አበባ ጉዳይ ሳይሆን ሌላ ጉዳይ ላይ ሲወያዩ የሰነበቱ የኦህዴድና የሌሎች ኦሮሞ ድርጅት አመራሮች የአዲስ አበባ ጉዳይን ወደ የሚወያየው ቡድን ሰተት ብለው ገብተው የድምፅ ብልጫ ለመውሰድ ጥረት አደረገ። አልሆነም።

እናም ኦህዴድ መጨረሻ ላይ የሚያስቅም የሚያስገርምም የሚያሳዝንም ነገር ይዞ ብቅ አለ። ምክክሩ አሁን ያለውን ህግም ሌላም ለማስተካከል ግብአት ነው ነበር ያሉት። እነ አጅሬው ግን የምክክሩ ተሳታፊ የተስማማበትን አዲስ አበባ የፌደራል ከተማ ይሁን የሚል ስምምነት "የኦሮሚያን ህገ መንግስትና የአሁኑን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አይፈቅድም" ብለው እርፍ።

ወገን!

የምክክር ኮምሽኑ የስምምነት ሀሳብኮ ህገ መንግስት ጭምር ይሻሻልበታል ተብሎ ነበር። ተውት ህገመንግስትን የኢትዮጵያ ስም ይቀየርልን ብለው በምክክሩ አቅርበዋል ራሳቸው። ህገ መንግስቱ ይቀየር ይሻሻል ወዘተ ራሱ አጀንዳ ነው። እነ አጅሬው የኦሮሚያ ሆገ መንግስት አይፈቅድም አሉ። አንፈቅድላችሁም አሉ።
መጨረሻ የእነሱ ፍላጎት ሲመክን "የህገ መንግስት ጥሰት ነው" ብለው ተሳታፊውን አስፈራሩ።

የህግ ባለሙያ ብለው ሁሉ አምጥተው ተሳታፊውን ሁልህም ስህተት ነህ ሊሉት ጥረዋል።

የሆነውን ጉድ ሁሉ መፃፍ አልችልም። አድካሚ ነው። አንድ ነገር ግን ትክክል ነው። ምክክሩን የፈለጉት ለማስመሰያነት ብቻ ነው። እነሱ የፈለጉት ካልሆነ የህግ ጥሰት አድርገው ያመጡታል።

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የዛቻ ኮምሽን / የምክክር ኮምሽን ሌንጮ ሳይቀር ሊበጠብጥ ሄደ!

Post by MINILIK SALSAWI » 05 Aug 2026, 00:25

ሌንጮ ሳይቀር ሊበጠብጥ ሄደ!
በምክክር ኮምሽኑ የዛሬ ውሎ ኦህዴድ በአዲስ አበባ ጉዳይ ብልጫ ሲወሰድበት ሂዳችሁ በጥብጡ ባለው መሰረት ሌላ አጀንዳ ላይ የሚወያዩ የነበሩ አባላቱና የሌሎች ድርጅቶች አመራሮችም ለመበጥበጥ ተልከዋል። ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል የድሮው የኦነግ አመራር ሌንጮ ለታ ይገኝበታል። ቀጀላ መርዳሳ የተባለው ግለሰብም ሌላኛው ለብጥብጥ የአዲስ አበባን ጉዳይ ወደሚወያየው ቡድን ሰተት ብሎ የገባው ነው።
እነዚህና ሌሎች ግለሰቦች ያለ ቡድናቸው ሄደው አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ብለው ተከራክረዋል። ተሳታፊውን አፋጥጠዋል።
የኦህዴድ ብልፅግናን አሳፋሪ ተግባር ያዩት ተወያዮች አዝነዋል። ተወያዮቹ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትም መቀመጫ መሆኗን ጠቅሰው ጭምር ነው ሲያስረዱ የሰነበቱት። እናም የአፍሪካውያን ዋና ከተማ የሆነችን አዲስ አበባን ነው የእኛ ብቻ አድርጉልን የሚሉት። አንድ ከጎሬ የመጡ ሰው ታዲያ የኦህዴድን ነውር አይተው፤ "አፍሪካን ጭምር ነው የምታሳፍሩት" ሲሉ ተናግረዋል።
ቢገባቸው ለኦሮሞ ህዝብም አይጠቅምም። ለኢትዮጵያ ህዝብ አሳፋሪ ነው። ለገባው ደግሞ የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባን በዚህ መጠን ሲያወርዱት ተግባራቸው በአህጉር ደረጃም አሳፋሪ ነው። የጎሬው አባት እንዳሉት።
በነገራችን ላይ ምክክሩን እኛ ነው የምንመራው የሚሉት የኮምሽኑ አመራሮች ኦህዴድ ሲበጠብጥ ምንም ማድረግ አልቻሉም። ያው ምክክር የሚባለው መቀለጃ መሆኑ የተመሰከረበት ነው።

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በምክክር ስም እየተሰራ ለሚገኘው ደባ አንደኛ ደረጃ ምስክር

Post by MINILIK SALSAWI » Yesterday, 21:37

ይቅርታ ጠይቀዋል!
የምክክር ኮምሽኑ አመራሮች ኦህዴድን በማገዝ የሰሩት ወንጀል የማይስተባበል ሲሆን ለይምሰልም ቢሆን ይቅርታ ጠይቀዋል። በምክክር ስም እየተሰራ ለሚገኘው ደባ አንደኛ ደረጃ ምስክር ሆነዋል። ሰሞኑን የአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚወያዩ የምክክሩ ተሳታፊዎች ያለፈቃዳቸው የኦህዴድን አቋም እንዲያፀድቁ ተገድደው ነበር። የምክክር ኮምሽኑ ያለ ተወያዮቹ ፈቃድ አዲስ አበባን የኦሮሞ አድርገው በማቅረብ ተሳታፊዎቹ ላይ ጫና ያደረጉ "ምሁራንን" አምጥተው "አዲስ አበባ የኦሮሚያ ካልሆነች ችግር ይፈጠራል"አስብለው ነበር። ምሁራን ተብለው በኮምሽኑ ስር በሚገኙ ግለሰቦች በኩል።
ተሳታፊዎቹ በተደረገባቸው ጫና፣ በሚሰራው ኢፍትሐዊነት ራሳቸውን ከምክክሩ ሂደት ለማግለል ጭምር እየተዘጋጁ በነበሩበት ሁኔታ፣ ትናንት የምክክር ኮምሽኑ አመራሮች ከአንዴም ሁለት ጊዜ ተመላልሰው የኦህዴድን አላማ በምክክር ስም ለማስፈፀም ለሰሩት ነውር ይቅርታ መጠየቃቸው ታውቋል። ይሁንና ይህ ይቅርታ ለይምሰል በመሆኑ የሚወሰድ ምንም እርማትም የለም። ከዚህ በተጨማሪ ለይምሰልም ቢሆን ይቅርታ የጠየቁት በአዲስ አበባ ጉዳይ እንጅ በአጠቃላይ በሂደቱ ድንኳን ሰባሪ በማስገባት፣ ጫና በመፍጠርና በማወናበድ የሚደረገው ወንጀል ላይ ቀጥለውበታል። ይቀጥሉበታልም።
በአዲስ አበባ ጉዳይ አዲስ አበባ የሁሉም እንደመሆኗ የኢትዮጵያ መዲና እንጅ ሌላ ባለቤት የላትም የሚለው ሚዛን እየደፋ ሲሄድ ኮምሽኑ ምሁራን ያላቸውን ያለ ተሳታፊ ፍላጎት ሄዳችሁ ጫና ፍጠሩ ብሎ ከማዘዝ በተጨማሪ ሌሎች ያለ ቡድናቸው ሄደው አስፈራርተዋል። በሌሎች ጉዳዮች በተደራጁ ቡድኖች የሚወያዩ የኦሮሞ ተወላጅ ፖለቲከኞች፣ የህግ ባለሙያዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ጉዳይ ወደሚወያዩት ሄደው ያደረሱት ጫናም የኮምሽኑ ስህተት መሆኑን ቢያምንም ምንም አይነት ማስተካከያ አደርጋለሁ አላለም። በሌሎች ጉዳዮችም ኮምሽኑ የኦህዴድን አቋም ለማስፈፀም እየሰራ ነው።
ሆኖም ተሳታፊዎቹ በዚህ ሁሉ ጫና ምክንያት ውይይቱን ጥለን እንሄዳለን በማለታቸው የኮምሽኑ አመራሮች የምክክር ኮምሽን የተባለውን ቀልድነት አምነው ይቅርታ ጠይቀዋል። ይቅርታው የሰሩት ወንጀልን አርመው የሚቀጥሉ ለመምሰል እንጅ ዛሬም ነገም የሚሰሩት ጉዳይ ነው!
ለጊዜው ግን ሲጨንቃቸውም ቢሆን አዲስ አበባን ለኦህዴድ ለመስጠት የሄዱበትን መንገድ አምነዋል። ትናንት ተመላልሰው ይቅርታ የጠየቁት በቀጣይ ለሚሰሩት ጊዜ መግዣ፣ እስካሁን ለሰሩት መሸፋፈኛ እንደሆነ የተደበቀ ባይሆንም ምክክር የተባለውን ቀልድነት ግን ራሳቸው ተሳታፊው ፊት ተገትረው በአንደኛ ደረጃ ምስክርነት መመስከራቸው እንደቀላል የሚወሰድ አይደለም!

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

እስከ 200 ሺህ ብር መደለያ ቀርቧል! .... ተሳታፊዎችን ነጥሎ የማውራትና የማስፈራራት

Post by MINILIK SALSAWI » Yesterday, 21:46

እስከ 200 ሺህ ብር መደለያ ቀርቧል!
ኦህዴድ ብልፅግና ሁሉም አጀንዳዎች ላይ ወስኖ የመጣ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ርብርብ እያደረገ የሚገኘው አጀንዳ 7 ላይ ነው። በሌሎች አጀንዳዎች ውሃብያን ጨምሮ ለሌሎች አጋሮቹ ዋና ተዋናይ አድርጎ ድጋፍ እየሰጠም ቀዳሚ ሚና እየተወጣም እየሰራ ነው። በልዩ ሁኔታ የያዘው አጀንዳ 7 ወይም የፌድራል ከተሞች የሚለው ነው። በዚህ አጀንዳ ስር ሁሉም ከኦሮሚያ የመጡ ተሳታፊዎች በድርጅት ውሳኔ አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ እና ሞያሌ የኦሮሚያ መሆን አለባቸው ብለው አቋም እንዲይዙ ከማድረጉ ባሻገር በማጭበርበር፣ ጫና በማድረግና በገንዘብ ጭምር በመደለል ውሳኔ ለማስወሰን እየሰሩ ነው።
አይን ባወጣ መንገድ የኦሮሞ ብልጽግና ባለስልጣናትና ተሳታፊዎች የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመከተል አዲስ አበባ የኦሮሚያ መሆን አለባት የሚል አቋም አራምደዋል። ትናንት ኮምሽኑ በሰጠው መግለጫ የመንግስት ባለስልጣናት ጫናን ለማመን ተገድዷል። በተለይ ተሳታፊዎች ስብሰባ ረግጠው ከወጡ በኋላ።
ከመወያያ አዳራሽ ግቢ ዉጪ የፌድራል እና የጸጥታ ሃይሎችን ተጠቅሞ ተሳታፊዎችን ነጥሎ የማውራትና የማስፈራራት ተግባራትን አጠናክረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በገንዘብ እና በጥቅማጥቅም መደለል ተሳታፊዎች አቋም እንዲቀይሩ ጥረት እየተደረገ ነው። ለቤተሰቦችህ ጭምር አበል ይከፈላል ከሚለው ጀምሮ እስከ 200 ሺህ ብር ድረስ የተሰጣቸውና ቃል የተገባላቸው ተሳታፊዎች እንዳሉ ታውቋል።
አወያዮችን እና ኤክስፐርት ተብለው የተመደቡ ምሁራንን በመጠቀም የተዛባ መረጃና የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲን አቋም ለተሳታፊዎች በግልጽ እና በስውር ማስረዳት አቋም ለማስቀየር የሚደረገው ሌላኛው መንገድ ነው። በተለይ ደግሞ አወያይ ተብለው የተቀመጡት ለሚፈልጉት ተሳታፊ ብቻ የመናገር አድል በመስጠትና ለሌሎች ደግሞ ሆን ብለው በመንፈግ ግልጽ አድሎ ሲያደርጉ ሰንብተዋል። ይሄም በተሳታፊዎች ዘንድ ትልቅ ቅሬታ የፈጠረና ዘግይቶም ቢሆን የኮሚሽኑ አመራሮች ያመኑት ጉዳይ ነው።
በአጠቃላይ የኦሮሞ ብልፅግና በርካታ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም፣ በማስፈራራትና በመደለል ከተሞችን የኦሮሚያ ናቸው የሚል ውሳኔ ለማስተላለፍ እየሰራ ይገኛል። ይህ መንገድ የቀጣይ ግጭቶች መጀመሪያ እንጅ የግጭትም የችግርም መፍቻ ሊሆን አይችልም!

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በማጭበርበር የተጀመረው "ኮምሽን" .... የምክክር ኮምሽን ተብሎ ብዙ የሚወራለት የዛቻ ኮምሽን ሆኗል።

Post by MINILIK SALSAWI » Yesterday, 22:26

ሰሞኑን በምክክር ኮምሽን ስም እየተደረገ ስላለው ማጭበርበር ነው እየተነገረ የሚገኘው። በሚገርም ሁኔታ ግን አሁን ማጭበርበሪያ የሆነው ይህ የምክክር ኮምሽን ራሱ ከአመሰራረቱ የእነ አብይ አህመድ የማጭበርበር ውጤት ነው።
ከተወሰኑ አመታት በፊት ብዙ ችግር ይፈታል ተብሎ የተወራለት የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የሚባል ተቋም ተመስርቶ ነበር። ታዲያ ይህ ኮሚሽን በርካታ ባለሙያዎችን ይዞ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ የድንበር ግጭት መነሻዎችን፣ የማንነት ጥያቄዎችን የህገ መንግስትና ሌሎች ጉዳዮችን አጥንቶ አቀረበ።
የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ኮምሽን ግን አንድ ችግር ገጠመው። በየክልሎቹ መረጃዎችን ሲያሰባስብ የየክልሎቹ ከፍተኛ አመራሮች ከፍ ያሉ ቅሬታዎችን አነሱ። ከትግራይ ክልል ውጭ ያሉት ክልሎች በሙሉ ኦሮሚያ መሬታችን ቀምቷል ብለው ዝርዝር መረጃ አቀረቡ። ለምሳሌ ያህል የሶማሊ፣ የአፋር፣ የጋምቤላና የቤንሻንጉል ክልሎች እንዲደሁም የሀረርና የድሬዳዋ ከተሞች ኦሮሚያ ክልል እያደረሰባቸው የሚገኘውን የመስፋፋት ፖሊሲ ተናገሩ። ብዙዎቹ ዋና ዋና ተቋሞቻቸው (ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ፓርኮች፣ ኃይቆች፣ ከተሞች በጎጎል ካርታ ወደ ኦሮሚያ አካትተውብናል ብለው ተናገሩ። የጋምቤላና ቤንሻንጉል ደግሞ የከፋ ነው። ከሁለቱ ክልሎች መሬት ቆርሰው ኮሞ ወረዳ የሚባል አሁን ኦሮሚያ የጠቀለለው አካባቢ አለ። በዚህ ከሁለቱ ክልሎች የቀሙት ወረዳን ተጠቅመው ኦሮሚያን ከሱዳን ጋር ድንበር አድርገዋል። በኦነግ ሸኔ ስም በርካታ ቦታዎችን ወርረዋል። የአዲስ አበባ ጉዳይም በዝርዝር ተጠና። የህገመንግስት ማሻሻያ ተጠና። የውጭ ባለሙያዎች ተሳተፈውባቸው የቀረቡ ጥናቶች ሲታዩ ከኦሮሞ ብልፅግና የመስፋፋት ተግባር የሚቃረኑ ሆኑ። እንደ ለመዱት ጨዋታ ፈረሰ አሉ።
እነ አጅሬው ጥናቱን ሲያዩት የእነሱን መስፋፋት ያጋለጠ ሆነ። ጥናቱም ተቋሙም ከእነሱ ጥቅም ጋር የሚጋጭ ሲሆን ስንት እንዳላወሩለት አፈረሱት። ምክክር ኮምሽን ብለው አዋቀሩ። ለማንነትና ወሰን ኮምሽን የተጠናውን ጥናት ወደ ምክክሩ አዛወርን አሉ። ዘገየ አስፋው (አሁን በህይወት የለም) እና ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያም የአስተዳዳደር ወሰንና ማንነት ኮምሽኑ አመራሮች የነበሩ ሲሆን ወደ ምክክር ኮምሽኑ አዞሯቸው።
እናም የምክክር ኮምሽኑ አሁን የሚሰራው ማጭበርበር ብቻ ሳይሆን ለአስተዳደር ወሰንና ማንነት ኮምሽኑ የተሰራው ጥናት ሊያጋልጣቸው ሲሆን ያን ተቋም አፍርሰው በማጭበርበር የመሰረቱት ነው። ምክክር ኮምሽኑ ከስር መሰረቱ የማጭበርበሪያ ተቋም ነው።

ከሽመልስ አብዲሳ ቢሮ የመጣው ትዕዛዝ
የምክክር ኮምሽኑ ከሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ቀጭን ትዕዛዝ ተላልፎለታል። በምክክር ኮሚሽን አዘጋጅነት በፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ) አወቃቀር ዙሪያ ሲካሄድ በነበረው የምክክር ላይ፣ ከኦሮሚያ ክልል ተወካዮችና አመራሮች የተደረገውን አዲስ አጀንዳ የማስገደድ ጫና በመቃወም ከኦሮሞ ብሔር ተወካዮች ውጭ ያሉ የሁሉም ክልሎችና ብሔሮች ተወያዮች መድረኩን ረግተው መውጣታቸው ይታወቃል።
ባለፉት አራት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደራዊ ወሰንና አወቃቀር ላይ አራት ዋና ዋና አማራጮች ቀርበው ውይይት ሲደረግበት የቆየ ቢሆንም፣ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ግን «አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ እና የፌዴራሉ መቀመጫ ትሁን» የሚል ላለፉት 30 ቀናት ያልተወያዩበት አዲስ አጀንዳ በኃይል እንዲካተት ተደርጓል። በዚህ ጉዳይ ላይም እንዲፈርሙ ትዕዛዝ ወርዷል።
ለመፈራረም የቀረበው ሰነድ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጽሕፈት ቤት ተዘጋጅቶ የመጣ እንደሆነም ምንጮች ገልፀዋል። ከሽመልስ አብዲሳ ጽሕፈት ቤት ተልዕኮ ይዘው የመጡ አካላት በኮሚሽኑ የበላይ የአጀንዳ አስተባባሪ አቶ ተመስገን አብዲሳ በኩል ከተመደቡበት አጀንዳ ተቀይረው፣ በተለየ ሁኔታ የአዲስ አበባንና የድሬዳዋን ጉዳይ ላይ ለማዋከብ ተልዕኮ እንዲገቡ መደረጉ ተመልክቷል።
በተጨማሪም አቶ ተመስገን አብዲሳ ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ማለትም ከዶ/ር አብዱላዚዝ ዳውድ (የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ሃላፊ)፣ ከአቶ ሀይሉ አዱኛ (የኮሙኒኬሽን ሃላፊ) እና ከአቶ ጉዮ ዋሪዮ (የፍትህ ቢሮ ሃላፊ) ጋር በመሆን ለኮሚሽኑ መመሪያና ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተሳታፊዎች በግድ እንዲፈርሙ ከፍተኛ ጫና ሲያደርጉ እንደነበር ተጋልጧል።
በተለይም ከአማራ ክልል የመጡ ተወካዮች፣ ተሳታፊዎች የቀረበውን ጫና በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ከኦሮሚያ ክልልና ከአዳነች አቤቤ አስተዳደር የተላኩ የደህንነት አባላት ክትትልና መከባ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልፀዋል። በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ከሽመልስ አብዲሳ ቢሮ የተላከው ሰነድና ትዕዛዝን «ከአንድ ወገን የተጫነን ሰነድ አንፈርምም» በማለት መድረኩንና ግቢውን ጥለው ወጥተዋል።

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

"የኦሮሞ ባለስልጣናትን እንዳትቃወሙ" የኮምሽኑ አመራር ........... ለዚህም ነው ኮምሽኑ የኦህዴድ መሳሪያ ነው የምንለው!

Post by MINILIK SALSAWI » Yesterday, 22:55

"የኦሮሞ ባለስልጣናትን እንዳትቃወሙ" የኮምሽኑ አመራር
ይህ ግለሰብ ዮናስ አዳዬ ይባላል። የ"ምክክር" ኮምሽኑ ኮምሽነር ተብሎ ከፍተኛ ኃላፊ ያደረጉት ነው። ሰውዬው ታዲያ በምክክሩ የኦህዴድ ወኪል የሚፈፅመውን ተግባር ነው እያደረገ የሚገኘው። በአዲስ አበባ ጉዳይ ውይይት ሲደረግ እየዞረ ለተሳታፊዎቹ "ይህ የመንግስት አቋም ነው ተቀበሉትና በሌሎች ጉዳዮች ብትከራከሩ ይሻላል" እያለ በይፋ የኦህዴድን ሀሳብ ለማፅደቅ እየሰራ ይገኛል።
በተጨማሪም በተለያዩ ቡድኖች የተመደቡ የኦሮሚያ ባለስልጣናት፣ የኦነግና ሌሎች አመራሮች የተመደቡበትን ቡድን ትተው በህገወጥ መንገድ የአዲስ አበባን ጉዳይ ላይ ወደሚወያየው ቡድን ሲገቡ ተሳታፊዎች ቅሬታ እንዳያቀርቡ ተከላክሏል። ተሳታፊዎች ለምን ከሌላ ቡድን ይመጣሉ ብለው ሲጠይቁ "እነዚህ ባለስልጣናት ናቸው። መቃወም የለባችሁም" እያለ የኦህዴድን ነውረኛ አካሄድ በተቋም ("ምክክር ኮምሽን") እየደገፈ ይገኛል።
የኦህዴድን በምክክር ስም ሁሉን የመጠቅለል አካሄድ በማገዝ ላይ የሚገኘው ኮምሽኑ ራሱ ነው። የኮምሽኑ አመራሮች የተለያየ ሚና ተሰጥቷቸው አንዱ ሙሉ የቃለ ጉባኤ መረጃ ሲሰጥ፣ ቀሪው በበየቀኑ የሚያስገቧቸውን ሰዎች ሁኔታ ሲሸፍን ሌላው ደግሞ በይፋ የኦህዴድን አላማ ለማሳለፍ እየቀሰቀሰ ነው።
ለዚህም ነው ኮምሽኑ የኦህዴድ መሳሪያ ነው የምንለው!


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12504
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የምክክር ኮምሽን .... ተሳታፊዎቹ በፀጥታ አካላት ሲዋከቡ ሰንብተዋል።

Post by MINILIK SALSAWI » Yesterday, 23:10

ምክክር እያሉ ፖሊስም አስገብተዋል!

"ኢትዮጵያ እየመከረች" ነው እያሉ ጥያቄ ሲነሳባቸው ደግሞ ወደ ተመካካሪዎቹ ፖሊስ ይልካሉ። ትናንት በማረጋጋት ስም ፖሊስ አስገብተው እንደነበር ተገልፆአል። ባለፉት ቀናት ተሳታፊዎቹ በፀጥታ አካላት ሲዋከቡ ሰንብተዋል። በግል የሚያደርጉት ማዋከብ አልበቃ ሲል ፖሊስ ጭምር ይልኩባቸዋል። የሚገርመው ደግሞ ሁሉም ፖሊሶች የኦሮሞ ተወላጅ እንደሆኑ ታውቋል።

እስኪ ጠይቁ‼
የምክክር ኮምሽኑ ተሳታፊ የሆነ የምታውቁትን ሰው ጠይቁ! በሰውም ቢሆን አጠያይቁ! የጌታቸው ረዳ ቡድን፣ የደብረፅዮን ቡድን፣ በአጠቃላይ በየቀኑ ወደ አዳራሽ የሚገቡት የትህነግ ተወካዮች ምን እያሉ ነው ብላችሁ ጠይቁ! እኔ ደጋግሜ ያረጋገጥኩትን ደግሞ ልንገራችሁ!
አዲስ አበባ ያለው የጌታቸው ረዳ ቡድንም፣ ከመቀሌም (ከደብረፅዮን ቡድን) ከትግራይ ኮታ በእጥፍ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ከኦሮሚያ ቀጥሎ በየቀኑ ያለ ከልካይ ወደ አዳራሽ የሚገቡት የትህነግ ወኪሎች ናቸው!
የሁለቱም ክፋይ አቋማቸው አንድ ነው። ዋና የትግራይ የሚሉት አጀንዳ ይልቅ የኦሮሞ ብልፅግናን አቋም በመደገፍና ከአማራ ክልል የመጡ ተሳታፊዎች የሚያነሱትን ነጥብ በመቃወም ነው ጊዜያቸውን እያጠፉ ያሉት። በቃለመጠይቅ ወዘተ አዲስ አበባን ለኦህዴድ እንደሚሰጡት መሪዎቻቸው በምክክር መድረኩ የተሳተፉት አዲስ አበባን የኦሮሚያ ናት ብለው ሽንጣቸውን ገትረው እየተከራከሩ ነው። በየቀኑ የሚደግፉት የኦህዴድን ነውረኛ አቋም ነው። ከዚህ ባሻገር አማራን ገዥ፣ በዝባዥ አድርገው የሀሰት ትርክት ሲዘሩ፣ ሲያቀሳስሩ ነው የሚውሉት። በዚህ ሂደት አገዛዙን በመደገፍ እየሰሩ ያሉት ውሃብያና የሁለቱ የትህነግ ወኪሎች ናቸው።
የሞት ሽረት ትግል ላይ ነኝ የሚለው የመቀሌው ቡድን የላካቸውም፣ ከትህነግ አካሄድ ተለውጫለሁ የሚለው የጌታቸው ረዳ ቡድን በአንድነት የአገዛዙ ዋስና ጠበቃ፣ አነታራኪ ሀሳቦችን በማምጣት ፀረ አማራ አቋም ይዘው ጥላቻ ሲዘሩ ነው የሚውሉት።
ተሳታፊው እስኪገርመው ድረስ ከኦህዴድ በላይ ኦህዴድ ብልፅግና ሆነው እየተወኑ ያሉት ለግልፅ አላማ ነው። ኦህዴድ በምክክር ስም እያራመደ ያለው አቋም አገር የማፍረስ ስልት ነው። ይህ ደግሞ ለትህነግ አላማው ነው። ትህነግና ኦህዴድ አንድ አቋም የተጋሩት አገር ማፍረስ፣ ማዋረድ የጋራ አጀንዳቸው ስለሆነ ነው። ሁለቱም እርስ በእርስ ለመግጠም የጦርነት ነጋሪት እየመቱ በኢትዮጵያ ላይ ግን አብረው ተባብረው ይዘምታሉ።

Post Reply