Page 1 of 1

የቆዳ ጥበብና የጫማ ኢንጉስትሪን አለም አቀፍ ደረጃ ላይ የሰቀለው የጉራጌ ክህሎት

Posted: 30 Jul 2026, 14:18
by Horus
የዛሬ 60 አመት made in sodo ይባሉ ነበር! አዞ ሸራ ጫማን ፈልስፎ የቻይና ሸራ ጫማን የተፎካከረው መርካቶ !


Re: የቆዳ ጥበብና የጫማ ኢንጉስትሪን አለም አቀፍ ደረጃ ላይ የሰቀለው የጉራጌ ክህሎት

Posted: 30 Jul 2026, 14:38
by Odie
Horus wrote:
30 Jul 2026, 14:18
የዛሬ 60 አመት made in sodo ይባሉ ነበር! አዞ ሸራ ጫማን ፈልስፎ የቻይና ሸራ ጫማን የተፎካከረው መርካቶ !

ይሄ ስራተኛና ስላምተኛ ትእግስተኛ ህዝብ👏

Re: የቆዳ ጥበብና የጫማ ኢንጉስትሪን አለም አቀፍ ደረጃ ላይ የሰቀለው የጉራጌ ክህሎት

Posted: 30 Jul 2026, 14:59
by Horus
ኦዴ
እኔ ልጅ ሆኜ የማውቀውን ልንገርህ ። ከ7ኛ ጀርባ ያለው ሰፈር አዲስ ከተማ ይባላል ። አዲስ ከተማ ውስት ሁለት የሥራ ሰፈሮች ነበሩ ፤ አንዱ ሰራተኛ ሰፈር ይባል ነበር ። እዚያ ማንኛውም አይነት የብረታ ብረት መሳሪያዎች ቢላ፣ ማረሻ ፣ ጦር ፣ እና የጦር መሳሪያ ጠብመንጃ ሁሉ የሚጠገነው እዚያ ነበር ። ጥይት ሁሉ ይሰሩ ነበር ። ያን የሚያቀሳቅሱት የሰባት ቤቶች በበኞች ነበሩ ። ከዚያ ወረድ ስትል ቀጭቃጭ ሰፈር ነበር ። እዚያ ደሞ ልዩ ልዩ ከጠፍጣፋ ብረት የሚሰሩ ምጣድ ፣ ማንደጃ፣ መቁሊያዎች ሁሉ ይሰሩ ነበር ። ያን የሚያቀሳቅሱት የክስታኔ ጥበበኞች ነበሩ ። ከዚያም ተያይዞ የቤት ክዳን ቆርቆሮና ዛሬ ሕንጻ የሚሰራበት እስቲል ኢንዱስትሪውን የሚያንቀሳቅሱት እነሱ ናቸው ።

ምን ማለት ይቻላል! ጉራንዝ አኩሪ ሕዝብ ነው ! ትግስት ብቻ ሳይሆን ዝምተኛ ሕዝብ ነው! የጉራጌ ባለኃብት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ነው ግ ን ማንም አያውቃቸውም! ጉራ ስለ ማይወዱ!