Page 1 of 1

5 ከተሞች በፋኖ ተያዙ.... ወረዳው ነፃ ወጣ/ከባድ ትንቅንቅ!.....2መኪና ሙሉ ቁስለኛ ተጫነ

Posted: 28 Jul 2026, 01:40
by MINILIK SALSAWI

5 ከተሞች በፋኖ ተያዙ.... ወረዳው ነፃ ወጣ/ከባድ ትንቅንቅ!.....2መኪና ሙሉ ቁስለኛ ተጫነ

Posted: 28 Jul 2026, 03:13
by MINILIK SALSAWI
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ‼️

መደራጀት ስንጀምር እንደ ሞኝ የቆጠሩን ነበሩ። እንደ እብሪተኛ የተመለከቱንም ነበሩ። መሰልጠን እና መደራጀት ስንጀምር ማንንም ተማምነን አልነበረም። ትላንትን ከዛሬ ጋር ባሰናሰለ ነገንም ባመላከተ ስልታዊ ትንተና ላይ መቆማችን ደፋር እንድንሆን ስላስቻለን እንጅ።

ገና ከፕሪቶሪያ ስድስት ወራት አስቀድሞ በህግ ማስከበር ስም በእንጭጩ የማክሰም ዘመቻ ሲከፍቱብን የአማራ ህዝብ ከጎናችን በመቆሙ እርሾ ሆነን መቀጠል ቻልን።

ያገለገላቸውን የአማራ ልዩ ኃይል በክህደት በትነው ጦርነቱን ሲጀምሩት ትጥቃቸውን ቀምተን ጥርስ አልባ እናደርጋቸዋለን ብለው ነበር። በምላሹ የሆነው ግን የቀድሞ አለቆቻቸው የአባቶቻችንን ቤልጅግ እና ምኒሽር መንጠቃቸው ያሳደረብንን ቁስል አልዘነጋንም እና በገፍ ያመጡትን የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በገፍ ተቀበልናቸው። የሞተበትን ለመቅበር፣ የቆሰለበትን ለማንሳት ወኔ እንዲኖረው የሚያደርግ ዓላማ አልታጠቀምና ከጦርነት ወደ ጦርነት የሚያዞሩትን "ምስኪን" ሰራዊት በየ ጥጉ አዝረከረክነው።

ሲጀምሩ ቀበቶ እናስፈታለን ያሉ ጦረኞች መሀል ላይ ህዝብ ነው የወጋን ብለው በየደረሱበት ጭፍጨፋ ፈፀሙ። ያጋጠማቸው የበለጠ መዝረክረክ ሆነ። እንደገና ሽፍታ ናቸው አላማ የላቸውም አሉን። የህዝብ ተቋም ጠብቀን፣ ለወጉን ምህረት አድርገን፣ ኃይል ገንብተን፣ ሰራዊት አደራጅተን በራሳቸው ተተኳሽ ተዋግተን አሳዬናቸው። ህዝብ አደራጅተን፣ መልክ እና ደርዝ ያለው ፖለቲካ ሰርተን ራቁታቸውን ስናስቀራቸው አንድ አይሆኑም የተከፋፈሉ ናቸው የሚል ፕሮፖጋንዳ ጀመሩ።

የጠላትን ረጅም እጆች ሰብረን፣ ትግላችንን የጡረታ መውጫ ሊያደርጉ የቋመጡትን ጥግ አስይዘን፣ የፍላጎት ቡድኖችን ቅርብ አዳሪ ህልሞች አክሽፈን፣ የውስጣችንን ግላዊ እና ቡድናዊ ፍላጎቶች ገርተን ግዙፍ ድርጅት መስርተን መጣን።

ከዚህ ጎን ለጎን የአብይ አህመድ አገዛዝ በቀጣናው ህዝብ ላይ ያወጀውን የጥፋት ዘመቻ በልዩ ስልት ብቻችንን መክተን በአፍሪካ ቀንድ አዲስ እና አስተማማኝ ኃይል መሆናችንን አስመሰከርን።

አፋብን አይፀናም ብለው ክፉ የተመኙትን አፍ አስይዘን ማዕበል ሳያናውጠን በመርህ ላይ ቆመን እና ፀንተን አሃዶቻችንን አዋህደን የጠላትን ሁለንተናዊ ርብርብ በመቋቋም ትላልቅ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተቀዳጅተናል።

ከረግረጉ መውጣት ያልቻለው ብልፅግና ከኤደን ባህረ ሰላጤ እስከ ቀይ ባህር ያሉ አጀንዳወችን በማንሳት ትኩረት ለማስለወጥ ቢሞክርም አልሆን ሲለው ተባብረው ሊመቱኝ ነው ብሎ የሚጨፈጭፈውን ህዝብ የሙጥኝ እንዲልርገነዋል።

ዓላማችንን ለኢትዮጵያውያን አስረድተን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የለውጥ ኃይሎች አሰባስበን በአማራ ላይ ይሳቡ የነበሩ ቀስቶችን ወደ አገዛዙ እንዲዞሩ አደረግን። የቅርብ እና የሩቅ ጎረቤት አገሮች ከተለመደው የዲፕሎማሲ አካሄድ ወተው ከህዝብ ትግል ጎን እንዲቆሙ አድርገናል።

በዚህ ምክንያት ሽፍታ ናቸው፣ ዓላማ ቢስ ናቸው፣ ዋሻ ናቸው አይነት ፕሮፖጋንዳወች አፈር ለብሰው ከውጭ ሀይሎች ጋር ተባበሩብኝ ይሉትን እዬዬ ተያይዞታል።

ብልፅግናወች "በምርጫ ድግስም" ሆነ በብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የማይመክቱት ማዕበል እየመጣባቸው መሆኑን ውቃቤያቸው የነገራቸው ይመስላል። ሁለት ምርጫ አላቸው። ጦርነት አቁሞ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ወይም የሽንፈትን ፅዋ መጎንጨት!

ብርሃኑ ጁላ ጡረታ ልወጣ? የተተኪው ዝግጅት፣ .... በምክክሩ ተሳታፊዎች መካከል ብጥብጥ ተነሳ

Posted: 28 Jul 2026, 14:11
by MINILIK SALSAWI