Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member+
Posts: 5299
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ይድረስ ለአርቲስት ሜላት ቀለመወርቅ ባለሽበት - ስለ የማነ ባርያ ዜማዎችና ግጥሞች - የቻላችሁ አድርሱላት!

Post by Meleket » 27 Jul 2026, 05:43

Meleket wrote:
27 Jul 2026, 05:31
Please wait, video is loading...

አርቲስት ሜላት ቀለመወርቅ፡ የብርቁን ኤርትራዊ የጥበብ ሰው የየማነ ባርያን የፍቅር ዜማ ማንጎራጎርሽ ለየማነ ባርያ ሙዚቃ ያለሽን ክብር ይገልጻል። ቢሆንም ግን የየማነ ባርያ ሙዚቃዎች የህዝብ ብሶትንም የሚገልጹ ይገኙበታል። ለምሳሌ እዚህ እታች የቀረበው ዜማ እጅግ ትልቅ መልእኽት ያለው ነው፡ እና አንቺ ሆንሽ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች፡ በአማርኛ በኦሮምኛ በወዘተኛ ብታንጎራጉሩት መልእኽቱን ለብዙዎች ለማዳረስ ይችላል።

እስቲ ለሜላት እነዚህን የየማነ ባርያ ሙዚቃ ግጥሞች ግርድፍ የአማርኛ ትርጉሞችን ላኩላትና፡ ሙዚቆቹን ፈልጋ በማድመጥ ለህዝብ ጀሮ ታድርሳቸው።

የየማነ ቤተሰቦች ስስታሞችና የገንዘብ ሰዎች እንዳልሆኑ እንገምታለን፡ የማነ ሙዚቃዎቹ ለብዙዎች እንዲደርሱ እንጂ ለገንዘብ አይደለም የሰራቸው ብለን እናምናለን እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር!

አርቲስት ሜላት ቀለመወርቅ፡ ለእንጉርጉሮሽ ምስጋናችን ይድረስሽ፡ ባለሽበት!

Meleket wrote:
14 May 2025, 11:20
EBS ላይ በቅርቡ የቀረቡ ሙዚቀኞችን ለማመስገን ያህል ነው። ይህቺን የየማነ ገብረሚካኤል ሙዚቃ እታች ባስቀመጥነው ግጥም መሰረት እስቲ ለማንጎራጎር ሞክሩ! የብዙ ኢትዮጵያውያንን የልብ ምት የምትገልጽ ሙዚቃ በመሆኗ እነ ቴዲ ኣፍሮ እስቲ ኣንጎራጉሯት ለማለት ያህል ነው! ሙዚቃ ዓለም ኣቀፋዊ ቋንቋ ነዉ!
Meleket wrote:
26 Sep 2023, 04:36
ጊታር ወዳዶች ይህቺ ዜማ እንዳታመልጣችሁ . . . .

በተለያየ ምክንያት ወደ ተለያዩ ሃገሮች የተሰደዱ እልፍ ኣእላፍ ኢትዮጵያውያን ይቺን የየማነ ባርያ ዜማ ከነግጥሟ ለማጣጣም እድል ካገኙ፡ የኤርትራ ህዝብ የማነ ገብረሚካኤል (ባርያ)ን ለምን እንደሚወደው ፍንትው ብሎ ይታያቸዋል። የማነና በዚህች ዜማው ውስጥ የተሳተፉ ሙዚቀኞች ምን ያህል ከሱ ሓሳብ ጋር እንደተጣጣሙ ለማዬት የጊታሪስቱን ቁዘማ በመስማት ለመመስከር ይቻላል።

የማነ በግጥሙ እንዳብራራው ስደት አሁን አይደለም የጀመረው፡ ብዝበዛ፡ የሰውን መመኘት፡ በሃይል ብቻ የማመን የጡንቸኞች ኣባዜ ወዘተ ከጥንት የነበረ ነው፡ ገና የሰው ልጅ ሳይሰለጥን። አሁንም ባልሰለጠኑት ህዝቦች መካከል ይህ እኩይ ተግባር ስላለ፡ ስደትም ቀጥሏል። ስደት የሚያቆመው ጨቋኝና ተጨቋኝ የሌለበት ሁኔታ በትግል መጐናጸፍ ሲቻል ብቻ ነው ይለናል፡ ሰላምም በልመና ሳይሆን በትግል እንደምትገኝም ግልጽ አድርጎልናል ነብዩ የማነ ባርያ።

https://sonichits.com/video/Yemane_Bary ... he_Yu_Sdet

ስደት

ዛሬ ገና ኣይደለም የጀመረው ስደት፡
እርስበእርስ ውጊያና ጭካኔና ሁከት፡
ከጥንት የቆዬ ነው ዓለም ስትፈጠር፡
ገና ሳይሰለጥን ሰው ሳለ ኋላቀር።

ይሸጥም ነበረ የሰው ልጅ በዋጋ፡
ታስሮ በሰንሰለት ተመዝኖ ስጋ።
አጥንትና ስጋ ወርደው ወደ ገበያ፡
ለጭካኔያችን ጥግ ሆነዋል መታያ።

ከጥንት ከጥዋቱ ዓለም ሳትሰለጥን፡
ያኔ ጀምሮ ነው ሰላም የጠፋችን።

አሁን በዚህ ዘመን በስልጡኑ ግዜ፡
የሰውን መቀማት የኃይለኛ አባዜ፡
ኣልቀረም ገና ኣለ፡ ይሻዋል ኑዛዜ።
ስለሆነም ስደት አሁንም ቀጥሏል፡
ከግፈኞች ሽሽት ይበልጥ ተፏፉሟል።

አንዳንዴ ጦርነት ሰላምን ይጠራል፡
ጡንቻ ሲተባበር ገዢን ይዘርራል።
የጭቁኖች ትግል በፍጹም አይጠፋም፡
ጦርነትን አልፋ ትመጣለች ሰላም።

ሰላም አትገኝም በመለማመጥ፡
ሰው እስካላቆመ የሰው ደም መምጠጥ፡
በሃሳብ ተባብሮ በዝባዥን መዘርጠጥ።

ሰላም አትገኝም በመሞዳሞድ፡
ሰው እስካላቆመ የሰው ስጋ መጎመድ፡
ኃይልን አስተባብሮ ገዥን ማርበድበድ፡
ግፈኛን ደርምሶ በኃይል መናድ።

ጨቋኝና ገፊ፡ ገዢ ኃይል ሳይጠፋ፡
የሰላም ዘንባባ ኣትበቅልም በተስፋ፡
የሰላም ዘንባባ ኣትመጣም በተስፋ።


ሱዳን ውስጥ የማነ በስደት ይኖር በነበረበት ወቅት፡ ወላጅ እናቱ ሊያዩት ወደ ሃገረ ሱዳን ያመራሉ። ወቅቱ ብርቱ ረሃብና ድርቅ የነበረበት ግዜ ነበር። እህልም ስኳርም ያኔ እጅግ ተወዶ ነበር ኣሉ፡ ታድያ ዬዋሁ የማነ ጆንያ ሙሉ ስኳርና ውሃ ቤቱ በራፍ ላይ ያስቀምጣል። ማንም ኣላፊ ኣግዳሚ የተራበና የተጠማ ዜጋ ስኳሩን እየበጠበጠ እንዲጠጣው መሆኑ ነው። ታድያ እናቱ ይሄን ጆንያ ሙሉ ስኳር በራፋቸው ደጅ ላይ መተውን በማዬት፡ ለሚስቱ “ልጄ እባክሽ ይህን ጆንያ ሙሉ ስኳር ወደ ቤት ውስጥ አስገቢው፡ ለምን በራፍ ላይ በጸሃይና ንፋስ ይሰጣል” ይላሉ። የየማነን ባህርይ ጠንቅቃ የምታውቀው ሚስቱ ሃረገወይንም “ኣዬ እማማ፡ ይህችን ጆንያ ስኳር ወደ ቤት ካስገባኋት፡ የማነ ሌላ ጆንያ ስኳር ገዝቶ እዛችው ቦታ ላይ ያስቀምጣል!” እንዲህ ነው የማነ ባርያ፡ የመስጠት ምሳሌ በመሆን በኤርትራውያን መካከል ሁሌም የሚዘከረው።

የዓለም የስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ይህንን ከተካፈልን ዘንዳ፡ በቀጣይ ደግሞ ከዜሞቹ የኣንዷን ግጥሞች እንካፈላለን።
https://www.facebook.com/10006509781848 ... =permalink
ሌሎች የየማነ ባርያ ብርቅ ዜማዎች ይዘት የሆኑ ግጥሞችን በአማርኛ ከብዙ በጥቂቱ እዚህ መመልከት ይቻላል፡ viewtopic.php?f=2&t=328834&

በፍቃደኝነት የሙዚቃና የሰላማዊ መስተጋብር አምባሳደር በመሆንሽ ትልቅ አክብሮት እንሰጥሻለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።