Page 1 of 1

ቤት ማለት እና ሃገር ማለት

Posted: 17 Jul 2026, 16:57
by Naga Tuma
ይህን ኣስተያየት መስጠት የፈለኩኝ ከጥቂት ወራት በፊት ነበር።

ኣስተያየቱን ያመነጨዉ የመድረኩ ኤርትራዊ ተሳታፊ ኣስደንጋጭ ኣስተያየትን ማንበቤ ነበር።

ኣስተያየቱን ያነበብኩኝ በኣጋጣሚ ነበር። ካነበብኩኝ በኋላ ኣስተያየት ለመስጠት ግዜ ኣልነበረኝም።

የደነቀኝን እና ኣስደንጋጭ የመሰለኝን ኣስተያየት መርሳት ኣልቻልኩም።

ለኣስተያየቱ መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ሁለት በጣም ቀላል ምሳሌዎችን ያሰብኩኝ በወቅቱ ነበር።

በዚህ ዘመን ቤት ማለትን ዱር የማይኖር ሰዉ ካልሆነ በቀር የማያዉቅ ሰዉ ዬለም። በዚህ ዘመን ዱር ዉስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቢፈለጉ ከኣማዞን ጫካ ዉጪ የሚገኙ ኣይመስለኝም።

የሰዉ ልጅ ዱር ዉስጥ ከመኖሩ ቤት ሰርቶ ወይም ገንብቶ መኖርን መፍጠር የጀመረዉ ጥንት ግዜ ነዉ።

ጥንት ግዜ ቤት ሰርቶ መኖርን የፈጠረዉ የሰዉ ልጅ የመንግስት መዋቅር ያለበትን ስፍራ ኣበጅቶ ሃገር ማለትን መፍጠርም በቅርብ ዘመናት የጀመረ ብርቱ ፍጡር ነዉ።

ቤት እና ሃገር ወይም የመንግስት መዋቅር ያለበት ስፍራ ሁለቱም መታየት የሚችሉ ከለላ ወይም ባዉንደሪ ኣላቸዉ።

ቤትን እያንዳንዱ የሰዉ ልጅ የሚሰራዉ ኣይዴለም።

የመንግስት መዋቅር ያለበትን ስፍራም እያንዳንዱ የሰዉ ልጅ የምያበጅ ኣይዴለም።

የቤትን ጥቅም ኣስተዋዮች የሆኑ የቤተሰብ ኣባለት ሁሉ የሚገነዘቡት ነዉ።

ከጠራራ ፀሓይ እና ከከባድ ዝናብ ከለላ ይሆናል።
ሰዉ ሲርበዉ ምግብ ሠርቶ ለመመገብ ይሆናል።
በስፍራዉ ዉሃ ኣስቀምጦ ለጥም መወጫ ይሆናል።
ከዱር ጨለማ ከለላ እና ለእንቅልፍ ማረፍያ ይሆናል።
ልጅ ወልደዉ የሚስሙበት እና ለወግ የምያደርሱበት ስፍራ ይሆናል።
ኣብሮ ተግቶ ለማደግ እና ኣብሮ ለመበልፀግ የማቀጃ ስፍራ ይሆናል።
የዘመዶች እና የእንግዶች ማስተናገጃ ይሆናል።
ለኣለመግባባት የሽምግልና ስፍራ ይሆናል።
ሐዘን ሲሆን ከወገን ጋር መሸኛ እና ከሐዘኑ ማገገምያ ስፍራ ይሆናል።

ይህን ሁሉ ኣዋቂ ይስታል ለማለት ሳይሆን ለማስታወስ ያህል ነዉ።

የቤት ጥቅምን የምያዉቅ የቤተሰብ አባት የመሰለዉን እና የምያዉቀዉን ያህል ተግቶ ለመስራት ይነሳል።

ቤት ሲሰራ ያየ መንገደኛ ቆሞ ያግዛል። ቤት ለእንግዳ የሚባል ይሆናል።

ቤት ተሠራ ማለት የቤተሰብ አባላት ለየብቻ ሆነ ተባብሮ ትግል ኣቆመ ማለት ኣይዴለም። ቤት ማለት በየቀኑ እየታገሉ የሚኖሩበት ስፍራ ነዉ።

ቤት ዉስጥ መኖር የለመደ ሰዉ ከቤት ዉጪ ልኑር የማይል ነዉ። እንደ ጥንት ግዜ ዱር ዉስጥ መኖር እንግዳ ነገር ይሆንበታል።

ሃገር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ኣፄ ዮሓንስ ያሉትን መከለስ ሆነ መበለዝ የሚቻል ኣይመስለኝም።

እኔ መጨመር የሚችል ኣስተያየት ካለ ሃገር ማለት የመንግስት መዋቅር ያለበት ስፍራ ማለት ነዉ ያልኩኝን ነዉ።

ቤት መስራት እንደምያለፋዉ የመንግስት መዋቅር ያለበት ስፍራን ማዋቀርም ያለፋል።

የመንግስት መዋቅር ያለበት ስፍራ ተዋቀረ ማለት በመዋቅሩ ስር የገቡት ሕዝብ ዕለታዊ ትግል ኣቆመ ማለት ኣይዴለም።

የመንግስት መዋቅር ማቆምን የመራ ሰዉ ማነዉ ጥያቄ በመዋቅሩ ዉስጥ ወይም ከመዋቅሩ ዉጪ ሊነሳ ይችላል።

ጆርጅ ዋሺንግተን ብቸኛ ሰዉ ነዉ። ኣፄ ቴዎድሮስ ብቸኛ ሰዉ ነበሩ። ኣፄ ምኒልክ ብቸኛ ሰዉ ነበሩ። ኣፄ ሀይለ ሥላሴ ብቸኛ ሰዉ ነበሩ።

ጆርጅ ዋሺንግተን መርቶ ካቋቋመዉ የመንግስት መዋቅር ይልቅ ኣፄ ቴዎድሮስ፣ ኣፄ ምኒልክ፣ እና ኣፄ ሀይለ ሥላሴ መርተዉ የተቋቋሙት የመንግስት መዋቅሮች በጣም ጥልቅ የታሪክ መሠረት ነበራቸዉ ቢባል ስ ህተት ኣይመስለኝም።

የተለያየ መሠረት ኖሯቸዉ የተለያየ መናወጥ ያጋጠማቸዉ ምክንያቱ ምን ይሆን፧

በእኔ አስተሳሰብ ኣንዱ ምክንያት በመንግስት መዋቅር ዉስጥ እና ከመንግስት መዋቅር ዉጪ የሚደረጉ ትግሎችን ኣንጻራዊ ጥቅሞችን እና ጉዳቶችን የማመዛዘን አቅም ማነስ ነዉ።

ይቀጥላል …