Page 1 of 1

ከአፈ-ሙዝ ወደ አፈ-ምክክር ሽግግር

Posted: 17 Jul 2026, 14:09
by DefendTheTruth
ሁሉም ነገር በኃይለ-ቃል ጀምሮ ወደ ኃይለ-እርምጃ ነበር የምሄደዉ፣ ይህ ደግሞ ታሪካዊ ስብራታችን ሆኖ ቆይቶዋል፣ ወደ ኃላ አስቀርቶናል፣ ከነበረን ከፍታ ወደ ዝቅታ አዉርዶናል፣ ደሃ አገር አድርጎናል፣ ኃላ ቀር አድርጎን አስቀርቶናል፣ ሄዶ ሄዶም የባሕር በር አልባ ና የጆኦግራፊ እስረኛ አድርጎናል። አሁን ከዚህ ባሕል ወጥተን ና ሁሉንም ነገር በአፈ-ሙዝ ለመፍታት ከመሞከር፣ ወደ ነባራዊ ባሕላችን ና በንግግር፣ ዉይይት፣ እርቅ ና ካሳ የመሳሰሉ ባህላችን፣ አፈ-፣ምክክር መመለስ አለብን፣ ለልጆቻችን የተሻለች አገር ለማስተላለፍ። ከራስ ወዳድነት ወጥተን፣ ወደ የጋራ ጥቅም መታገልን መስጀመሪያ መረሀ-ግብር ነዉ፣ የብሔራዊ ምክክር ጉባዔ። ታሪክ ቀያሪ ክስተት!

የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክት!