Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7762
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

አያነ፣ ኤበ ወይም ምርቃት፣ እና አባሬ ወይም እርግማን

Post by Naga Tuma » 17 Jul 2026, 00:33

ስለ መለኮታዊ ነገር እኔ ሆነ ብዬ ያጠናሁ ኣይዴለሁም።

መለኮታዊ መሠይ ክስተቶችን እያስተዋልኩ ወይም ያስተዋልኩ እየመሰለኝ በየቀኑ ይደንቀኛል።

ማንም ሰዉ ሕልም የምያይ ወይም የሚቃዥ ቢሆንም እኔን የሚደንቀኝ ቀጠሮ ሳልይዝ ሕያዊ የሚመስሉ ሕልሞችን ማየት ነዉ።

በልጅነቴ አያነ እና አያንቱ ሲባል የሰማሁ ቢሆንም ሆነ ብዬ ኣላጠናኋቸዉም።

አያነ ማለት በዓል ወይም በእንግሊዘኛ ሆሊ እንደማለት ነዉ።

አያነ አባ ማለት የአባት ኣምላክ እንደማለት ነዉ። በባህል የአባት ኣምላክ የሰዉ ጠባቂ ነዉ ይባላል። በስም ዓብ ከሚባለዉ ጋር የሚገናኝ መሆኑን ኣላዉቅም።

ኣያንቱ ማለትን በትክክል መተርጎም ያስቸግረኛል።

አያነ ነቢ በባህል የሚከበር በዓል ነዉ።

መነሻዉ ከዬት እንደሆነ ኣላዉቅም። ነብ ማለት እና ነብይ ማለት ተመሳሳይ ቃላት ቢሆኑም መሠረታቸዉ ኣንድ መሆኑን ኣላዉቅም።

መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ አያነ የተባለ፣ ለምሳሌ አያነ ነቢ መቼ የተስተዋለ ይሆን?

ኣንዴ የተስተዋለ አያነ የሚጠፋ ነዉ ወይስ መጥፋቱን የማይፈቅድ ይሆን?

ምርቃት ማንም ይመርቃል። እርግማንም ማንም መርገም ይችላል።

ተገቢ መሆኑ እና ኣለመሆኑ ሌላ ጥያቄ ነዉ።

ምርቃት ሆነ እርግማን የተመረቀዉ ላይ ሆነ የተረገመዉ ላይ ይህ ነዉ መባል የሚቻል ተፅዕኖ እንዳለዉ ማወቅ ይቻላል ወይስ ማወቅ በፍጹም ኣይቻልም?