ብሄራዊ ምክክር ፤ አዲሱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ካልቸር
Posted: 16 Jul 2026, 23:03
ካልቸር እና ባህል በጣም ተቀራራቢ ትርጉምና ቢኖራቸው አንድ ነገር አይደሉም ። ካልቸር ማንኛው በተፈጥሮ ሳሆን በሰው ልጅ እጅ የተሰራና የሚሰራ ነገር ማለት ነው። እርግጥ በጠባቡ ሲወሰድ ካልቸር የኑሮ ዘዴ ፣ አንድን ነገር የማድረጊያ መንገድ ወይም ብልሃት ማለት ነው። በዚህ ትርጉሙ ባህል ጋር አንድ አይነት ነገር ነው። ባህል ፣ ብሂል ፣ ብልሃት ፣ ዘዴ ፣ መንገድ ማለት ነው።
በኢትዮጵያ አሉ የሚባሉት ጎሳዎች 86 ቢሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትና ሊኖሩ የሚችሉት ባህላዊ የፖለቲካ ካልቸሮች ፣ የስምምነትና ማህበራዊ መስተጋብር ስልቶች ከ100ና ከዚያም በላይ ሊሆኑ ይችላሉ ። እያንዳንዱ ጎሳ እንደ እንሰሳ በስርዓት አልባ መንጋነት የሚኖር ሳይሆን እያንዳንዱ ጎሳ ለዘመናት የተጠቀመበት የሕግ ፣ የሞራል፣ ያስተዳደር ፣ የፍትህ እና ማህበራዊ ባህሎች ፣ ዘዴዎች አሉት ።
እነዚህ ከ100 በላይ የሚሆኑ የስርዓት አይነቶች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ተዘግበው ተጠንተው አንድ ብሄራዊ ክላቸር አልተደረጉም ።
ዛሬ የተጀመረው ብሄራዊ ምክክር የመጀመሪያው ሙከራ ነው። እርግጥ ዳያሎግ ማለትና ምክክር የተለያየ ትርጉም አላቸው ። ከሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች መሃል የሚደረግ ንግግር ኮንቨርሴሽን ወይም ውይይት ነው። ዳያሎግ ወደ ክርክር ይጠጋል ። በኢትዮጵያ እስካሁን በሰፊው የሚታወቀው የዳያሎግ አይነት ሙግት የሚባለው ነው።
በጉራጌኛ ዎገት (የነገር ስም) ፣ ውግግት (ግስ) ላይ ላዩን ሙግት ቢመስልም በትክክል ምክክር እና ዲሊበሬሽን የሚባለው ነው። ሽማግሎችና ያገር መሪዎች ተራ በተራ ተማክረው ፣ ተሟግተው እና ተወያይተው አንድ ውሳኔ የሚደርሱበት የፖለቲካና ሶሺያ ባህል ውግግት ይባላል። ለምሳሌ በጎርደና ሴራ ፣ በጆካ ሴራና ሌሎችም የመስቃን ወለኔና ስልጤ ሴራዎች የሚከወነው ይህ የውግግት ካልቸር ነው።
ይህን ካልቸር እኔ ስለማውቀው አነሳሁት እንጂ እያንዳንዱ ጎሳ የመሳሳይ የውግግት ወይም ምክክር ሴራ አለው። በእኔ እምነት ይህ አንድ ወር የሚፈጅ ብሄራዊ ምክክር ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ለመጅመሪያ ግዜ አንድ ወጥ ፣ ዘመናዊ ብሄራዊ የውግግት ስርዓት ወይም ካልቸር ይኖራታል ።
የአንድ አገር ብሄራዊ አገር በቀል የፖለቲካ ካልቸር የሚበልጽገው በዚህ አይነት ሂደት ነው።
እኔ ዛሬ ላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብሆን ኖር ለዶክትሬት ዲግሪ የምጽፈው ዲሰርቴሽን ይህ ጉዳይ ወይም ርዕስ ይሆን ነበር ። የጽሁፌ ቶፒክም " አዲሱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ካልቸር" ይባል ነበር።
ሆረስ ዐይነ ብርሃን