Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 44055
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

THE HISTORICAL SIGNIFICANCE OF THE ETHIOPIAN NATIONAL DIALOGUE

Post by Horus » 15 Jul 2026, 12:27

የፈረንሳዩ እውቅ ሶሺያል ሂስቶሪያን ዦርዥ ሩዴ ስለ ፈረንሳይ አርሶ አደር ጸረ ፊውዳል አመጽ ይህን ብሎ ነበር። የፈረንሳይ ፔዘንተሪ በሞናርኪው ላይ አምጾ ወጥቷል ፤ ግ ን ግቡን ሳያሳካ ተሽንፎ ተመልሷል ። ሆኖም ይህ መደብ የሞናርኪውን ስርዓት አሸንፎ ሬፑፕሊክ ባያቆምም አምጾ በመውጣቱ ብቻ እራሱን ላንዴም ለሁሌም የተለወጠ መደብ አድርጎታል ሲል ሕዝቦች አንድ በሚፈጽሙት ተግባር እንዴት አስተሳሰብና ስነልቡናቸው እንደ ሚለወጥ ይነግረናል።

የዛሬው የኢትዮጵያ አገራዊ ጉባኤም ልክ እንደ ፈርሳይ አርሶ አደሮች ነው ። ከዚህ ጉባኤ በኋላ ኢትዮጵያ አዲስ ሬፑፕሊክ ታቁም አታቁም አሁን ላይ ማወቅ አይቻልም ። ከዚህ ጉባኤ በኋላ ኢአትዮጵያ አዲስ ሕገ መንግስት ትፍጠር አትፍጠር አሁን ላይ ማወቅ አይቻልም ። ከዚህ ጉባኤ በኋላ ኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ስርዓት ታቋቁም አታቋቁም አሁን ላይ ማወቅ አይቻልም ።

ነገር ግ ን አንድ ነገር በርግጠኘት ማወቅ ይቻላል ። ያም የኢትዮጵያ ልሂቃን የፖለቲካ ዲስኮርስና ህሳቤ ፣ የፖለቲከኞች መላ ምትና እስመ ነጋ ፍልስምና ። ልብወለዳዊ የፖለቲካ ቲኦሪ ላንዴም ለሁሌም ይለወጣል ።

ይህ ብቻ አይደለም ። ከዚህ ጉባኤ በኋላ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሳይንስ የሚባል መስክ ይወለዳል ። ማለትም በሁለተኛ ደረጃና ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ህሳቤ ምንድን ነው? ኢትዮጵያ በም አይነት የፖለቲካ ሃሳብ ወይም ቲኦሪ ነው የምትመራው? የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የሚመነጨው ከየት ነው? ወተርፈ የሚባሉት የፖለቲካ ፍልስፍና ፣ ንድፈ ሃስብ ፣ ዝዬና ትግበራ ምርምሮች አሁን አገራዊ ፣ ውስጣዊ ፣ ብሄራዊ ፣ ኢትዮጵያዊ መሰረት ያገኛሉ ።

ስለሆነም የመጨረሻ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውና እጅግ ታሪካዊው ክስተት ሆኖ በታሪክ ይመዘገባል ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ሆረስ ዐይነ ብርሃን
Last edited by Horus on 15 Jul 2026, 13:31, edited 3 times in total.





Tiago
Member
Posts: 3507
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: THE HISTORICAL SIGNIFICANCE OF THE ETHIOPIAN NATIONAL DIALOGUE

Post by Tiago » 15 Jul 2026, 21:04

There is no point discussing with you as you care more about how much the seventh grade madman pays you.
ቆሻሻ


Post Reply