Page 1 of 1
ክስታኔ
Posted: 14 Jul 2026, 01:11
by Horus
Re: ክስታኔ
Posted: 14 Jul 2026, 01:29
by Horus
መስቀል በር እያንኳኳ ነው!
ፊቃቆ ፣ በአክራሚ (እንቁጣጣሽ) ሰሞን ልጃገረዶች አበባና አክርማ የሚሰበስቡበት የልጃገረዶች በዓል ነው ! አክርማ ሴቶች ስፌት የሚሰሩበት ስንደዶ ሲሆን ለጋው አክርማ ፊቃቆ ይባላል በክስታኔኛ! እራሱ የበዓሉ ስም ፊቃቆ ይሉታል ሴቶቹ!
ክስታኔ አዲስ አመትን አክራሚ ብሎ ነው የሚጠራው!
በጣም የቅርብ ጓደኛሞች የሆኑት የሰፈር ልጃገረዶች በስማቸው አይጠራሩም! ዬጎስቴ ነው የሚባባሉት ! ጊስት ንግስት ፣ ጊስቴ ንግስቴ ማለት ሲሆን ዬጎስቴ የንግስቴ ማቆላመጫ ነው! እጅግ ውብ አጠራር ነው! ወንዶች ደሞ ሞጎ ነው የምንባባለው ! ጓዴ እንደ ማለት ነው!
ይህ በመስቀል ከሚደረገው አዳብና የተለየ የልጃገረዶች ብቻ ባህል ነው።
Re: ክስታኔ
Posted: 14 Jul 2026, 22:30
by Horus