የቀድሞ ኢትዬጵያ መሪዎች የታራክን ስህተትና እጥፋት በሚገባ ቢያውቁም አንድን ብሔር በሌላኛው ላይ ለማነሳሳት ሲሰሩ አልታዩም። በብሔርተኝነትና በዘረኝነት የምንጠላው መለስ ዜናዊ ጭምር እንዲህ በግልፅ የአንድን ማህበረሰብ ቁስል ከመቶ ሃምሳ አመታት በኋላ በማስታወስ ግጭትን አልጠመቀም።
በጎጃም ዓብይ አህመድ በግልፅ አፄ ዬሃንስ የጎጃምን ሕዝብ እንደጨፈጨፈ ተናግሯል። ይህ ተንኮሉ ጉጃምን ትግሬ ላይ ለማስነሳትና አማራና ትግሬ ተናበው አብረው ስልጣኑን እንዳይገረስሱቡት ያደረገው መርዛማ ፖለቲካው ነው።
በጎጃም አፄ ዬሃንስ አስከፋ ግፍ መፈፀማቸው ግልፅ ቢሆንም ታሪክ በታሪክነቱ መወሳት አለበት ፤ እንዳይደገም ትምህርት መቅሰምያ መሆን አለበት እንጂ ለመኮርኮርያ እና ግጭትን ለመጥመቅ መሆን የለበትም።
የዓብይ ካድሬዎችም የሚያመልኩት መደዴ ክፉ ሰው መሆኑንም ከዚህ መረዳት አለባቸው። (ጂዜአ)