Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12374
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አበዳሪ ተቋማት የህዝብ ቆጠራ አካሂዱ የሚል አጀንዳ ይዘው መጥተዋል።

Post by MINILIK SALSAWI » 07 Jul 2026, 23:50

በኢትዮጵያ የሕዝብ ቆጠራ ከተካሄደ ሃያ ዓመታት ሊደፍን ነው። ብሄርን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አደረጃጀት ላላት ኢትዮጵያ የህዝብ ቆጠራ ሌላው የፍልሚያ ሜዳ ነው። ቆጠራ እንዳይደረግ የሚፈልጉ የፖለቲካ ቡድኖች መኖራቸውም ምስጢር አይደለም።ኢትዮጵያ በ 10 ዓመት አንዴ መካሄድ የሚገባውን ሀገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ ካካሄደች ሁለት አስርት ዓመታት ሊሞላት ጥቂት ጊዜያት ብቻ ቀርተዋታል። በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እውን መሆን ያልቻለውና በተደጋጋሚ የተራዘመው 4ኛው አገራዊ ቆጠራ፣ አሁንም የሚካሄድበት ትክክለኛ ቀን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስከሚወሰን ድረስ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጲያ ስታትስቲክስ ማሻሻያ አዋጅን ያጸደቀ ሲሆን፤ የአዋጁ መጽደቅ የመረጃ አሰባሰብ እና ስርጭት እንዲሁም እርስ በርስ የሚጋጩ መረጃዎችን በማስቀረት ሂደት ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ነው ተብሏል፡፡ በተሻሻለው አዋጅ ውስጥ ከተካተቱት ልዩ ድንጋጌዎች መካከል፤ ከመንግስት ምደባ፣ ከአገልግሎትና ስልጠና ክፍያዎች፣ እንዲሁም ከልማት አጋሮች ከሚገኙ ድጋፎች የተደራጀ ሆኖ በመንግስት የበጀት አስተዳደር ሕግ እንዲመራ፤ ክልሎች የራሳቸውን የስታትስቲክስ ህግ ማውጣት ቢችሉም፤ ድንጋጌዎቹ ከዚህ አዋጅ መሠረታዊ መርሆዎች ጋር የተጣጣሙ ወይም ይበልጥ ጥብቅ የሆኑ ደረጃዎችን የያዙ እንዲሆኑ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ከአምስት ዓመት በፊት ብዙ ወጪ ከወጣበት በኋላ የታቀደው ቆጠራ ተሰርዟል። አበዳሪ ተቋማት ቆጠራ አካሂዱ የሚል አጀንዳ ይዘው መጥተዋል። በጉዳዩ ላይ ዋዜማ ያሰናዳችውን ዝርዝር ዘገባ አንብቡት- https://cutt.ly/myqFfcIE