ላሊበላው የአበረ አጎትና ሚስቱ የተጋቡት በአጎቴ ተዝካር ላይ ነው
Posted: 04 Jul 2026, 00:40
እኛ ቤትና አጎቴ ቤት ባልና ሚስቶቹ ላሊበላዎች ልክ ዶሮ ሲጮህ በር ላይ ቆመው ያንን የልመና ዜማቸውን እየተቀባበሉ ላንድ ለ15 ውይም 20 ደቂቃ ያዘንቡት ነበር ። በምን በምን ወራት እንደ ሚመጡ አሁን ረስቼዋለሁ ። የሚበላ ምግብና ገንዘብ ነበር የምንሰጣቸው ። ተደጋግመው የሚመጡት ተመሳሳይ ወንድና ሴት ነበሩ ። ከዚያ አጎቴ አረፈና በተዝካሩ ድግስ ተጋቡ ። በተዝካሩ ላይም በነሱ የማሞገስና መወድስ ዜማ ሕዝቡን ሁሉ አስለቀሱት ።
ዛሬ ግ ን የላሊበላዎች ልመና እንደ ጉዳይ ተቆጥሮ ወሎዬ ጎጃሜ እየተባባሉ በቪዲዮ ሲፋጁ ገረመኝ
ዛሬ ግ ን የላሊበላዎች ልመና እንደ ጉዳይ ተቆጥሮ ወሎዬ ጎጃሜ እየተባባሉ በቪዲዮ ሲፋጁ ገረመኝ