Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Selam/
- Senior Member
- Posts: 18447
- Joined: 04 Aug 2018, 13:15
Post
by Selam/ » 28 Jun 2026, 09:29
1.ከኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ
2.የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
3.የሰንበትን ቀን አክብር
4.አባትና እናትህን አክብር
5.አትግደል
6.አታመንዝር
7.አትስረቅ
8.በሐሰት አትመስክር
9.የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
10.ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ ፡
-
Naga Tuma
- Member+
- Posts: 7776
- Joined: 24 Apr 2007, 00:27
Post
by Naga Tuma » 28 Jun 2026, 17:17
“Horus” wrote:
አሕዛብ ሆይ የክርስትና ዕምነት ነፃ ያወጣሃል፣ አያስፈራራህም!
Selam/ wrote: ↑28 Jun 2026, 09:29
1.ከኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ
2.የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
3.የሰንበትን ቀን አክብር
4.አባትና እናትህን አክብር
5.አትግደል
6.አታመንዝር
7.አትስረቅ
8.በሐሰት አትመስክር
9.የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
10.ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ ፡
እግዝኣብሔር ዬለም እያሉ የሃያሉ እግዝኣብሔርን ስም መጥራት ሃጥዓት ነዉ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በእግዝኣብሔር ስም እየማለ እግዝኣብሔር ዬለም ያለ ሊገዛሽ የሞከረ ነበረ ወይስ ኣልነበረም?
እግዝኣብሔር ያልተገለጠበት ስፍራ ፈንጠዝያ ብኩን ነዉ።
ሰኔ ቀን 21፣ 2018፣ ዓም
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15843
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 28 Jun 2026, 17:39
እነ ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ሥር እናውላለን የአውሬ ግልገሎች ደግሞ ከየት ብቅ ብቅ አሉ? ገና የሕይወትን ሰፊ እና ጥልቅ ውቅያኖስ ሳይቀዝፉ በእምቧቀቅላ እድሜያቸው በእራሳቸው ላይ ምላጭ እየሳቡ ነዋ! በኃጥያት ተጸንሰው በኃጥያት የሚያድጉ ትውልድ መብዛቱ ያሳዝናል -ዘመድ እናት አባት ያሸነፉ - በየጨለማው በየጉድጓዱ ጸያፍ ሃጥያት የሚፈጽሙ - የአረማዊ እምነት ተላላኪ ወይም ቫይረስ ተሸካሚ እና አስተላላፊዎች።
እግዚአብሄር ዕውቀት ይገለጥላቸው ፤ ፀጸት ምን እንደሆነ እንድረዱ የእርሱን አልፋ እና ኦሜጋ ( የአምላኮች አምላክ፤ የንጉሶች ንጉስ፤ የጌቶችም ጌታ መሆኑን) መሆኑን በአንደበታቸው እንድመሰክሩ ዕድሜ ከቸራቸው - መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው ሲያስተምሩ እንሰማ ይሆናል። በተፈጥሮ ላይ ጣታቸውን የቀሰሩ አንዳንዶቹ እስርቤት ሳይቀር መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው ገብተው፤ አንደበት ሁሉ ለአንተ ይገዛል፤ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይሰግዳል ብለዋል። እጅ ሰጥተዋል። እኔ የሚገርመኝ ለምን የግል ህይወታቸውን አይታገሉም፤ ከፈጠራቸው አምላካቸው ጋር ግብግብ የሚገጥሙት? ኢትዮጵያ የተረገመ ትውልድ እየመጣ ተቸገረች።