Page 1 of 1

የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 27 Jun 2026, 15:12
by Naga Tuma
ከስደት በኋላ እስራኤላዊ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት የጥንት ኢትዮጵያ ቀዳማዊ የአሓዱ ኣምላክ ነብይ አክናተን የተባለ ታላቅ ፈረዖ የነበረ መሆኑ ታሪክ ተገኝቷል።

ወይም

ኢትዮጵያ የስደት ንስሃ እንጂ የስቅለት ንስሃ ኣልነበራትም።

ወይም

ሃጥዓት ዉስጡ የተጻፈ መጽሓፍን ቅዱስ ማለት ሃጥዓት ነዉ

Re: የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 27 Jun 2026, 19:59
by Naga Tuma
የስደት ንስሃ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያልገባችሁ፥

መሠረቱ ኣይሁዳዊ የተባለዉ ስግመንድ ፍሪዩድ እና መሠረቱ ግብጣዊ የሆነዉ አህመድ ኦስማን የጻፉት ታሪክ የእስራኤል ፕሮፌት ሙሴ ተብሎ ይታወቅ የነበረዉ ከስደት በፊት ፈረዖ አክናተን የተባለዉ ነበር እንጂ እስራኤላዊ ኣልነበረም ነዉ።

ፈረዖ አክናተን በምድር ላይ ቀዳማዊ የአሓዱ ኣምላክ ነብይ የነበረ መሆኑ በታሪክ ይታወቃል።

አህመድ ኦስማን የጻፈዉ መጽሓፍ ዉስጥ ፈረዖ አክናተን ለስደት ከመዳረጉ በፊት ግዜያዊ የጥንት ኢትዮጵያ መሪ ሆኖ ነበር ተብሏል።

ግዜያዊ መሪ የሆነዉ የወቅቱ መሪ መንግድ ሄዶ ስለነበረ ነዉ ይላል።

የወቅቱ ዋና መሪ ከመንገድ ሳይመለስ በፊት የዋናዉ መሪ ንግስት በግዜያዊ መሪ ፈረዖ አክናተን ላይ ሕዝብ ኣሳምጻ ከግዜያዊ መሪነቱ ተነስቶ ለስደት ተዳረገ ይላል።

የመረጥኳችሁ ጎሳ ማለት እና የተረገሙ ጎሳ ማለት የመጣዉ ከዛ በኋላ መሆኑ ይመስለኛል።

ቀዳማዊ የአሓዱ ኣምላክ ነብይ ፈረዖ አክናተን እርግማን ኣለዉ ማለት ጉዳዩ ኢትዮጵያን ይመለከታል ማለት ይሆናል።

እኔ ኢትዮጵያ የነበረባት ንስሃ የምላዉ ይህ ነዉ።

የእርግማኑ ምክንያት የወቅቱ ንግስት የነበረችዉ ናት ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

የስግመንድ ፍሪዩድ እና የአህመድ ኦስማን መጽሓፎችን ያነበብኩኝ ከሃያ ዓመታት በፊት ቢሆንም ሁለት የጥንት ፈረዖዎች መሳይ ስሞችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ያስተዋልኩኝ በቅርብ ግዜ ነዉ።

ሜይ 11፣ 2026፣ እና ሜይ 18፣ 2026፣ ያየሁዋቸዉ ሕልሞች የፈረዖዎች መሳይ ስሞች ያላቸዉን ሁለቱ ቤተሰቦችን ይመለከታል።

ሕልም ማንም የምያይ ቢሆንም ሕልሞቹን ያየኋቸዉ ቀኖች በእኔ ቀጠሮ ኣለመሆናቸዉ እጅግ የሚደንቁ ናቸዉ።

Re: የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 29 Jun 2026, 14:59
by Naga Tuma
በዚህ የፍርድ ዘመን የተባለ ግዜ የአሓዱ ኣምላክ ቀዳማዊ ነብይ ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያላወቅክ ሆነ ተዓምራዊ ዜናዉን ሰምተህ ኢትዮጵያዊ የነበረን እስራኤላዊ ነበረ ማለት የክህደት ሃጥዓት ነዉ ማለት የማትችል የዘመኑ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ዘላለማዊ ንስህ ኣይሆንብህም?

እንደ ኣንድ ግለሰብ የእኔ ምክር ይህ ተዓምራዊ ዜና ተሰማ ማለት ቀድሞ በመነሳት የክህደት ሃጥዓትን ማረም ሃላፊነቱ ያለበት ባለቤቱ ነዉ ማለት ነዉ። ይህ የኣንድ ግለሰብ ምክር ሃያ ዓመታት ገደማ ሆኗል።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ለካ ኣንተ ነህ! ብሎ የመከረዉ ሃምሳ ዓመታት በላይ ሆኗል።

Re: የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 04 Jul 2026, 12:59
by Naga Tuma
በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ህዳሴ ማለት የተለመደ ነዉ።

አምስት መቶ ዓመታት ገደማ በፊት ኣዉሮፓ ዉስጥ ሬይነሳንስ ማለት የተለመደ ሆነ።

ሬይነሳንስ የማለት ጥልቀትን ላስተዋለ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ህዳሴ ማለት እና ሬይነሳንስ ማለት መካካል በጣም ግዙፍ ልዩነት ኣለ።

የኣዉሮፓ ሬይነሳንስ ማለት ከክርስትና በፊት የኖረ የጥንት ግሪክ ስልጣኔ ተጠንቶ ዳግም መወለድ እንደማለት ነበር።

ከክርስትና በፊት የነበረ የጥንት ግሪክ ስልጣኔ ተገኝቶ ዳግም መወለድ ማለት የካቶሊክ ቤተክርስትያንን መሠረት የነቀነቀ ነበር።

በዚህም ምክንያት ሶስት ቦታዎች የተሰነጠቀ ሆነ።

እኔ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የምለዉም ከክርስትና በፊት የነበረዉ የጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ ተገኝቶ ዳግም መወለድ ማለት ነዉ።

የዚህ የጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ መሠረት ጥንታዊነቱ እና ጥልቀቱ ከቅድመ ስደት በፊት የነበረዉ የአሓዱ ኣምላክ ማለት ቀዳማዊ ነብይ ታሪክ መገኘት ነዉ።

የዚህ ጥንታዊ ታሪክ መገኘት ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን መሠረት የነቀነቀ ነዉ።

ምክንያቱም የአሓዱ ኣምላክ ጥንታዊ እና ቀዳማዊ ነብይ እስራኤላዊ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ነበረ ማለት ከክርስትና በፊት መሠረቱ ኢትዮጵያ ወደነበረዉ የጥንት ኢትዮጵያ ሃይማኖት ይመልሳል ማለት ነዉ።

ጁዳይዝም፣ ክርስትና፣ እና እስልምና ከአሓዱ ኣምላክ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ተዋረድ ናቸዉ ማለት እኔ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የምለዉ እየሩሳሌም እና መካ ማለት መሠረቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሆነዉ ይታደሳሉ ማለት ይሆናል። ባህላዊ ሃይማኖት ይዘዉ ለሺህዎች ዓመታት የኖሩት ኢትዮጵያዊያንም መሠረቱ ኢትዮጵያ የሆነዉ ሃይማኖት ኣካል ይሆናሉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ይህን የምለዉ ለራስ ወይም የራስ ሃገር ወዳድነት ማድላት ሳይሆን የአሓዱ ኣምላክ ጥንታዊ ቀዳማዊ ነብይ እስራኤላዊ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ነበረ የሚል ታሪክ ገሃድ ስለሆነ ነዉ።

ስለዚህ የዚህ ሃገር ስለሃይማኖት ጉዳዮች ምክክር የኢትዮጵያ ህዳሴ ብሎም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ መሪ ማድረግ የሚችል ነዉ።

Re: የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 04 Jul 2026, 17:00
by Abere
የጋላ ድንበር እንደ ጋላክሲ ማቆምያ የለውም ይባላል- ከአንዱ ጋላክሲ ወደ ሌላው ትገባለህ እንጅ ። ይህ ነገር እንደት ነው? እናንተ ቃልቻ ቆሪጦች ካርታ የላችሁም እንደ?

Re: የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 10 Jul 2026, 21:59
by Naga Tuma
ሌላ ተጨማሪ ሀሳብ ለመስጠት ወደዚህ ርዕስ ስመለስ ይህን የጨቅላ አስተያየትህን ኣነበብኩኝ።

ኣልበርት ኣይንስታይን እና እኔ የኖርንበት ጋላክሲ የኣንተ ኣዕምሮ ዉስጥ ያለች ጋላክሲ ኣይዴለም ማለት መቼ ነዉ የሚገባህ?

ብትመከር ኣይገባህም። ምክር ኣትሰማም ተብለህ ብትሰደብ ኣይገባህም።

በሽታህ ምንድነዉ?

ያለ ወንድ ፍሬ ሴት ወንድ ልጅ ወልዳ ኣቀፈች የሚለዉ የጥንት ተረት ነዉ?

ወይም ጋላክሲ ኣለን ብላችሁ ያለን ጋላክሲ ዉስጥ እግዝኣብሔር ዬለም በሉ ነዉ?

ወይም እግዝኣብሔር ዬለም በሉ ማለት ነዉ?

ወይም እግዝኣብሔር ዬለም ያለዉን ክርስቶስ በሉ ነዉ?

ወይም የኣዕምሮ ባርነት ነዉ?

ወይስ ሌላ በሽታ ነዉ?
Abere wrote:
04 Jul 2026, 17:00
የጋላ ድንበር እንደ ጋላክሲ ማቆምያ የለውም ይባላል- ከአንዱ ጋላክሲ ወደ ሌላው ትገባለህ እንጅ ። ይህ ነገር እንደት ነው? እናንተ ቃልቻ ቆሪጦች ካርታ የላችሁም እንደ?

Re: የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 10 Jul 2026, 22:12
by Naga Tuma
የሃገር ምክክር ራዕይ በአረት ቃላት፥

አሓዱ ዓምላክ ህያዉ ነዉ።

እኔ እንደገባኝ ከሆነ ይህ ራዕይ ከስደት ዘመን እስከ ፍርድ ዘመን የሰነበተ እና ለዘላለም ምክክር ይሆናል።

Re: የኢትዮጵያ የሃገር ምክክር በኣንድ ዐረፍተ ነገር

Posted: 13 Jul 2026, 19:25
by Naga Tuma
ቀድሞ ነበር እንጂ ለቀዳማዊ ነብይ ዉዳሴ
ኣሁን ምን ያረጋል የሌለን ለመድሃኒት ዌድሴ

ሓምሌ ቀን 5፣ 2018፣ ዓም