Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 44080
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by Horus » 26 Jun 2026, 00:50


eden
Senior Member
Posts: 10247
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by eden » 26 Jun 2026, 01:07

luxury shouldn’t be priority. at least, we shouldn’t celebrate luxury considering the living conditions.

Horus
Senior Member+
Posts: 44080
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by Horus » 26 Jun 2026, 01:14

eden wrote:
26 Jun 2026, 01:07
luxury shouldn’t be priority. at least, we shouldn’t celebrate luxury considering the living conditions.
You are out of this class. አስመራና መቀሌ ላይ ትኩረት አድርጊ! Be humble. This is beyond you. Thank you.

ኢትዮጵያ ከባንዳዎችና ከግብጽ ገረዶች ከተፋታች ሰነበተኮ!


eden
Senior Member
Posts: 10247
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Post by eden » 26 Jun 2026, 02:22

Horus,

Hear me out

Wealth inequality is not unique issue to provinces and countries, as you know, it’s global.

It’s unsustainable. Worsening inequality results in disastrous outcomes for humanity.

Dr. Merera told us yemibelawn yata hizb mengstun yibelal . We saw this play out, and it’s going to continue to. This is not local or regional issue. I think you don’t disagree here as someone who read and debated about world problems for half a century.

አገሬን እወዳለው ያዙኝ ልቀቁኝ ትልና ግን ደሞ መቀሌ, ባህርዳርና ጎንደርን ዘውትር ትዘነጥላለህ. ይህ ታድያ አገር ወዳድ ወይስ … ?

Affable
Member
Posts: 865
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by Affable » 26 Jun 2026, 12:56

Eden መራራ የሚበላው ያጣ ህዝብ መሪውን ይበላል ካለ ዘመን ያስቆጠረ መስሎኝ። ከዛ “ ትንቢት” በሃላ መንግስቱን የሚበላ የተራበ የአገራችን ህዝብ ግን አልተከሰተም።
ንዋይ ባላቸውና በሌላቸው መሀል ያለው ልዩነት በጣም ከሰፋ ለህብረተሰብ እድገት ጠንቅ ነው ያልሽው እውነትነት አለው። ያ ሀቅ በርግጥ USA ውስጥ የጎላ እውነትነት አለው ከ Ethiopia በበለጠ ዛሬ። ያ ማለት ኢትዩጺያ ውስጥ አስፈሪ የ ሀብት ልዩነት በህዝባችን መሀል የለም ማለት አይደለም። አለ። ያውም አስፈሪ የሆነ። አስፈሪነቱ ሀብት ያካበቱት አብዛኞቹ ትራይባል ፓለቲከኞች መሆናቸው ነው።
አወ አጎቶችሽ አሁንም ከተጠያቂነት አያመልጡም ባይ ነኝ።
እኔ ከ Ethiopia ስወጣ ጉቦ የሚባል ቃል ፣ አለአግባብ መበልፀግ የሚባል ነገር በአብዛኛው ለህብረተሰቡ ባዳ concept ነበር።
አጎቶችሽ አዲስአበባ ከገቡ ከብዙ አመቶች በሃላ ወደ አዲስ አበባ ሄድኩ። የታዘብኩት የዝርፊያ ባህል በጣም አስደነገጠኝ።
ያ ባህል አሁን በቀላሉ ይከስማል የሚል ቅንጣት እምነት የለኝም።
አወ በጣም የጎላ የህብረተሰብ የ ኢኮኖሚ አቅም አለመጣጠን አደጋ ይኖረዋል። ያን inequalityን የፈጠረው ግልፅ የወጣ ዝርፊያ ሲሆን ደሞ ችገሩን በጣም ያባብሰዋል።
Luxury apartments መሰራቱ ላይ ስህተቱ አይታየኝም። ገንዘቡ ያለው ይገዛል። የመግዛት አቅሙ የመጣው በዝርፊያ ከሆነ ያ totally is a different thing.

Horus
Senior Member+
Posts: 44080
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by Horus » 26 Jun 2026, 13:13

ኤደን
ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ ይልና አበሻ ብልት ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ ብሎ ይደግመዋል ። መራራ ጉዲና ፈሪ ፣ አንድም በርግጥ አምኖበት የሞተለት ሃሳብ የሌላው የዉሃ ላይ ኩበት ነው። የመረራ ጸሃይ ጠልቃለች ። ያው ሰው ሲያረጅ ጉልበቱ ይሞትና ልቡ ግ ን አይሞትም። አይደለም በኢትዮጵያ ፍጹም በበለጸጉት አገሮች ሃብታና ድሃ አለ ። ነገር ግ ን ድህነት የሚጠላ ፣ የሚወገዝ ፣ የሚናቅ ፣ የሚወገድ ነገር እንጂ እየተወደሰ እንክብካቤ የሚደረግለት ባህልም ሆነ እምነት አይደለም ። ድሃ ያለው አንድ አማራጭ ነው ፣ እሱም ሃብታም መሆን ነው። እንጂ ሃብታም ድህነትን ለማክበር ወደ ታች አይወርድም ። ሃሳብና አንጎል አለኝ የሚል ሰው ድህነትን ወደ ሃብታምነት እንዴትና መቼ እነለውጥ ለሚለው መፍትሄ ማቅረብ ነው ያለበት ። አለቀ ። ኢትዮጵያ ሃብታም አገር የምትሆነው ሃብታሞችን በማክበር ፣ ድሆችን ሃብታም በማድረግ ፣ ሃብታምነትን በማድነቅ ብቻ ነው! የድህነት ባህልና ለድህነት ዝና መዝፈን ይቁም ብሏል አቢይ አህመድ አባ ደምር! ያ ደሞ የሚመቸኝ ፍልስፍና ነው ። እጅግ አድርጌ የምወዳት ኢትዮጵያን ሃብታም ሆና ከማየት ልቤን የሚያሞቀው ነገር የለም ። ይህን ሳልሽኮረመም እናገራለሁ!

eden
Senior Member
Posts: 10247
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by eden » 26 Jun 2026, 20:00

Horus,

ምን ያህል የሃብት አለመመጣጠን ሲደረስ ነው ላንድ ማህበረሰብ (ሃብታሙንም ጨምሮ) አጥፊ የሚሆነው ትላለህ?

ለምሳሌ የአሜሪካን ምሳሌ ውሰድና, ምን ትላለህ?
Total wealth held by the wealthiest 1% (about $55 trillion) roughly equals the combined wealth of the bottom 90%.

Horus
Senior Member+
Posts: 44080
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by Horus » 26 Jun 2026, 20:27

eden wrote:
26 Jun 2026, 20:00
Horus,

ምን ያህል የሃብት አለመመጣጠን ሲደረስ ነው ላንድ ማህበረሰብ (ሃብታሙንም ጨምሮ) አጥፊ የሚሆነው ትላለህ?

ለምሳሌ የአሜሪካን ምሳሌ ውሰድና, ምን ትላለህ?
Total wealth held by the wealthiest 1% (about $55 trillion) roughly equals the combined wealth of the bottom 90%.
አንቺ አቢይን ስለ ጠላሽ ያለም ሃቅ አይለወጥም! በማንምና በምንም አይነት መለኪያ የኢትዮጵያ ገበሬ በይው የከተማ ሰራተኛ ሕዝብ ከምንም ግዜ የተሻለ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ዛሬ ነው። ይህን ማለት ደሃ የለም ፣ ችግር የለብንም ማለት አይደለም ። ዛሬ ከድሮ የሚለየው ስልጣን በመቀማቱ የተበሳጨው ወያኔ ቆሞ የቀረው ፣ የከሸፈው አሳፋሪው የኤርትራዊ ግብጽ ገረዶች እና ዛሬ የበቀሉት ሙጃዎች ፋኖና ኦላ ብዙ ቲክ ቶክና ዩ ቲኡብ ስላስጮሁ የመሬርቱን ሃቅ አይለውጠማ ። የግብጽ ሱዳን እና ሻቢያ ቅጥረኞች ይህን ሁሉ ሲንጫቹና ሴት ሲደፍሩ ፣ ሰው ሲገድሉ አንድ ሰው እንኳን ደግፎአው ሰልፍ ወጥቶ አያውቅም ! የጽምዶ ጩሀት ዉሾችና ድመቶች እንኳ አይደግፉትም ። አለቀ ! የወደቀው ወያኔና ፋኖ ሕዝቡን ሊንቅና ሊሰድብ ይችላል! ያ ግ ን የሽንፈት ምልክት ነው። Your opinion is worth a penny. Facts rule the universe.

Horus
Senior Member+
Posts: 44080
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by Horus » 26 Jun 2026, 20:37


eden
Senior Member
Posts: 10247
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: CHAKA: THE YEKA MOUNTAIN NEW CITY - 4,000 LUXURY HOMES

Post by eden » 26 Jun 2026, 21:03

Horus,

አንድ ኢኮኖሚ አድጎ ሳለ ይህን የሚያራግብ መንግስት ከሌለ, እድገቱ ላይታይ ይችላል.

ሳያድግ ደሞ አድገናል የሚል የገጽታ ግንባታ ሲጧጣፍ, ያደገ ሊመስል ይችላል.

ወሳኙ ስታቲስቲክስ ማቅረብ ነው - መረጃ.

ኢኮኖሚው እጅጉን ሲያቆለቁል ግን ስታቲስቲክስም አያስፈልግ.

ለምሳሌ ዶክተሮች እንኳን መኖር አልቻልንም ብለው ሰልፍ ይወጣሉ. ምክንያቱም, ነገሩ ፈጥጦ ይወጣል.

ገጽታ ግንባታ የሚሰራው ትንሽ እንኳን የሚመስል ሲሆን ነው. ሃኪሞች በገፍ ወጥተው ቤተሰብ ማስተዳደር አልተቻለም ሲሉ ግን, ካድሬ ሰሚ የለውም.

የስጋ ቤት አምፖል በየጎዳናው ስላንጠለጠልክ, እድገት እና ብልጽግና መጣ ማለት አይደለም. ይህ ቁጭ በሉ ነው - ማለት ፕሮፓጋንዳ ነው!

በርግጥ ከልብህ መስሎህ የፕሮፓጋንዳው ሰለባ ሆነህ ይሆን ብዬም አሰብኩ


Post Reply