Page 1 of 1

ቀልድ እና ቁምነገር፥ ሕልም እና ቅዠት ቁጥር 5

Posted: 25 Jun 2026, 18:59
by Naga Tuma
ዛሬ ወደ ንጋት ላይ ሁለት የታወቁ የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣናትን በሕልም ኣየዃቸዉ።

ኣንዱ እራሱ የሰዉ እና የአምበሳ መካከል የሆነ ፍጡር ሆኖ በጀርባዉ ተኝቶ ኣየሁኝ።

መጀመርያ ላይ ማንነቱን ዲስጋይዝ ያደረገ እና ይህ ሰዉ ማነዉ ጫወታ ወይም ጌም መስሎ ታየኝ።

ሌላ የቀድሞ ባለስልጣን አጠገቡ ደርሶ በኣንድ እጁ ግንባሩን ነካ አድርጎ ይህ ኤከሌ ነዉ ብሎ ኣለፍ ኣለ።

በጀርባዉ ተኝቶ የነበረዉ ማንነቱ ግልጽ ሆኖ ከተኛበት ተነሳ።

ከዛም ኣመም ኣደረገዉ እና ተንገዳግዶ እኔ የሆነ ግድግዳ አጠገብ ቆሜ የነበረበት መጣ።

እጆቼ ተዘርግተዉ በጀርባዉ እኔን ተደገፈኝ። ኣቅፌዉ ፌይንት የምያደርግ እየመሰለኝ ሰጋሁ።

ፌይንት ማድረጉ በመሃል ወንድሜን ኣስባለኝ።

ከቆይታ በኋላ ተሻለዉ እና የዳነ መስሎ ከእቅፌ ወጥቶ በጀርባዉ ተኝቶ ወደነበረበት ሄደ።

በመዳኑ ደስ ብሎኝ ፈገግ ብዬ ኣየሁት። ሕልሜ እዛ ላይ ኣበቃ።

ቅዠት ማንም ይቃዣል። ሕልምንም ማንም ያያል።

ኣሁን ጥያቄ የሆነብኝ እንደዚህ ዐይነት ሕልም ሆነ ቅዠት የምታይበት ቀን ቀጠሮ ኣለዉ ወይ ነዉ።