Page 1 of 1

Anti orthodox chrisitian ethiopian bipolar pm tried to kill former tigray governr,orthodox priest,pretend it was robbery

Posted: 23 Jun 2026, 16:31
by JudgementDay1234
#NewsAlert ‼️ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አምባሳደር ፀጋይ በርሀ ከዝርፊያ እና የአካል ጥቃት ማምለጣቸው ተሰማ።

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በኢህአዴግ ዘመን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት አምባሳደር ፀጋይ በርሀ፣ በመቐለ ከተማ በታጠቁ አጃቢዎቻቸው ድጋፍ ካጋጠማቸው የዝርፊያ እና የአካል ጥቃት ለጥቂት ማምለጣቸው ተነግሯል።

አምባሳደር ፀጋይ በርሀ በመቐለ ከተማ ለተለመደው የጤና እንቅስቃሴ (ስፖርት) በወጡበት ወቅት፣ ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ሁለት ዘራፊዎች የሞባይል ስልካቸውን ለመቀማት ሙከራ አድርገዋል።

በወቅቱ ስልኩን ላለማስነጠቅ በአምባሳደሩ እና በሁለቱ ዘራፊዎች መካከል ጠንካራ አካላዊ ትንቅንቅ የተፈጠረ ሲሆን፣ በቅርብ ርቀት ሁኔታውን ይከታተሉ የነበሩ አጃቢዎቻቸው ሽጉጥ በመተኮስ ዘራፊዎቹ ለቀዋቸው እንዲጠፉ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ላይ ምንም ዓይነት የአካል ጉዳት ሳይደርስ እንዲሁም ንብረታቸው ሳይቀማ በሰላም መተርፋቸው ተረጋግጧል።

አምባሳደር ፀጋይ ከቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገብሩ አስራት በመቀጠል የትግራይ ክልልን ለረጅም ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩ ሲሆን፣ በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ እና በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ መአረግ አምባሳደር በመሆን ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊ ነበሩ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከትግራይ ጦርነት ማብቃት በኋላ በክልሉ እያገገመ ካለው ማህበራዊ ህይወት ጎን ለጎን፣ በመቐለ ከተማ የፀጥታ መጓደል በስፋት ይስተዋላል።

በተለይም በጠራራ ፀሐይ ጭምር በማጅራት መቺዎች የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና የቅምያ ወንጀሎች በነዋሪው ላይ ስጋት እየፈጠሩ ናቸው።

የመቐለ ከተማ አስተዳደር ወይም ፖሊስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰጡት ይፋዊ መረጃ ወይም መግለጫ የለም።