Page 1 of 1

The European Center for Law and Justice has appealed to UNODC regarding the escalating killings in Ethiopia.

Posted: 18 Jun 2026, 09:00
by MINILIK SALSAWI
የአውሮጳ የሕግና የፍትህ ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ እየተባባሰ ነው ያለውን ግድያ አስመልክቶ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዘር ፍጅት መከላከል ቢሮ ጥሪ አቀረበ። ማዕከሉ በቅርቡ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በትንሹ 37 ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መገደላቸውን አብያተ ክርስቲያንም መቃጠላቸውን አመልክቷል። ማዕከሉ ትናንት ባወጣው ማሳሰቢያው ኢትዮጵያ ውስጥ አጠቃላይ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት በአንድ ወገን ክርስቲያኖች ሟች ወገኖቻቸውን ይቀብሩ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎችም ከመኖሪያ ቀያቸው ይሳደዱ ይፈናቀሉ እንደነበር ገልጿል።

ግድያው «ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ክርስቲያኖች ላይ በተደጋጋሚ ከተፈጸመው ጥቃቶች በቅርቡ የተፈጸመ መሆኑን» በማመልከትም ድርጊቱ «በመላው ኢትዮጵያ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ነው» ያለውን «ግፍና ጭካኔ የጨመረ ስጋት ነው» ብሏል። የሁኔታውን መባባስ ምክንያት በማድረግም የአማራ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች እያጋጠሟቸው ያሉ አደጋዎችን በተመለከተ የአውሮጳ የሕግና የፍትህ ማዕከል አስቸኳይ አቤቱታውን ለተመድ የዘር ፍጅት መከላከል ቢሮ አቅርቧል።

ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫ በሚካሄድበት ዕለት በሸርካ ወረዳ ሁለት ዘመዳማቾች በጌዶ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መቀበራቸውን የግለሰቦቹን ስም በመጥቀስ ገልጿል። በዋዜማው ታጣቂዎች ወደ ቤታቸው መጥተው ንብረቶቻቸውንና ከብቶቻቸውን ሰርቀዋል፤ የሰዎቹም አስከሬን ከቤታቸውን ዐሥር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሚታና ጋዶ በተባለ ስፍራ መገኘቱንም አመልክቷል። ግንቦት 22 እና 23 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ውስጥ ተዘዋውረው የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሲቪሎችን በቤታቸው፤ በመንገድ ላይ እና ሲሸሹ መግደላቸውን፤ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የቆየውን የቅዱስ ገብርኤልን ቤተክርስቲያን ማቃጠላቸውን፤ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን ዘርፈው ማቃጠላቸውን ዘርዝሯል።

የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ቤተሰቦችን በመለየትም ቤቶቻቸውን በእሳት ማቃጠላቸውን ንብረቶችንም መዝረፋቸውንም ገልጿል። የአውሮጳ የሕግና የፍትህ ማዕከል መግለጫ በተለያዩ ጊዜያት ጥቃት የተፈጸመባቸው ቦታቸው በዝርዝር በመጥቀስ የተፈጸሙ ድርጊቶችን ማስረጃ በማጣቀስ አቅርቧል። የአውሮጳ የሕግና የፍትህ ማዕከል፦ «በሲቪል ክርስቲያኖች እና አማራዎች ላይ ተከታታይነት ያለው» ሲል የገለጠው «ጥቃት» በተመድ የዘር ፍጅት መከላከል ድንጋጌ እና በሮም ደንቦች (የዓለም አቀፍ የጦር ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት) አኳያ ብርቱ የሕግ ጥያቄዎችን ያስነሳል ብሏል።

Re: The European Center for Law and Justice has appealed to UNODC regarding the escalating killings in Ethiopia.

Posted: 18 Jun 2026, 09:49
by MINILIK SALSAWI


The European Center for Law and Justice has appealed to UNODC regarding the escalating killings in Ethiopia.

Posted: 19 Jun 2026, 08:58
by MINILIK SALSAWI