አንድ መፍታት ያለብን ችግር አጋጠመን እንበል። ይህን ችግር ለመፍታት የምንጓዘው ትክክለኛ መንገድ ፣ የምንጠቀመው ትክክለኛ ዘዴ ፣ የምንፈጽመው ትክክለኛ ተግባር፣ የምናስበው ትክክለኛ ሃስብ የሚጠይቀው ጥረት ፣ የሚፈጀው ጉልበት ፣ ሃብትና ግዜ አለ ።
በተመሳሳይ ይህን ችግር ለመፍታት የምንጓዘው የተሳሳተ መንገድ ፣ የምንጠቀመው የተሳሳተ ዘዴ ፣ የምንፈጽመው የተሳሳተ ተግባር፣ የምናስበው የተሳሳተ ሃስብ የሚጠይቀው የተሳሳተ ጥረት ፣ የሚፈጀው የተሳሳተ ጉልበት ፣ ሃብትና ግዜ አለ ።
ሁለቱን መንገዶች ለመጓዝ የምንከፍለው ዋጋ እኩል ነው ። ነገር ግን አንዱ መንገድ ወደ ትክክለኛው መፍትሄ ሲያደርሰን ሁለተኛው ግን ወደ ውድቀት ነው የሚያደርሰን።
የነዚህ ሁለት የተፈጥሮ ሕጎችን ልዩነት የማያውቅ አላዋቂ ፣ ሞኝ ፣ ጂል፣ ደደብ ፣ ግብዝ ይባላል። የሰው ልጅ ሁሉ ብቃት ችግር እንዳለው ማወቁ ብቻ አይደለም።
ችግሩ ምን እንደ ሆነ ሳያውቅና ችግሩ ምን እንደ ሆነ አውቆም የተሳሳተ መፍትሄ ለመስጠት እድሜውን ሚፈጀው ፣ ሕይወቱን ሚሰዋው የተፈጥሮ ሕግ ያልገባው ግብዝ ነው ።
በኢቮሉሽን ሂደት ውስጥ ለውጥ የሚያስወግዳቸውና የሚጠፉት፣ ወደ ፊት ከሚጓዘው የፍጥረት ጅረትና ፍሰት የሚቀነሱት እነዚህ ፍጡራን ናቸው ።
መጀመሪያ ችግርህ ምን እንደ ሆነ በትክክል እወቅ!
ሁለተኛ በትክክለኛ መፍትሄ ላይ ብቻ ሕይወትን አባክን! የተፈጥሮ ሕግ ስለሆነ!
Re: የሚሰራ ነገርም ፣ የማይሰራ ነገርም የሚፈጁት ግዜና ጉልበት እኩል ነው! ግብዝ ሁለቱን መለየት አይችልም!
ጭካ ከሌለ አንዲት ብቸኛ ዛፍ ኢኮሎጂያዊ ፋይሳ የላትም ። ማህበረሰብ ከሌለ አንድ ብቸኛ ሰው ማህበራዊ ፋይዳ የለም ። እንዲያም ያ ሰው ካልቸር መፍጠር ስለማይችል ቋንቋም ሆነ ማንነትም አይኖረውም ። በጥረትም ሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ምንም ነገር ተፈጥሮአዊ አገልግሎት ወይም እቅዳዊ አላማ ከሌለው የዚያ ነገር ሕልውና ከተፈጥሮና ማህበራዊ ሕግ ውጭ ነው። ያለው ሚናም አረም ወይም ነቀርሳዊ ሕዋስ ነው። እስቲ ኡህን ቅኔ ፍቱት?