ግምታዊ መለኮታዊ ክስተት ለዐለም
Posted: 11 Jun 2026, 01:18
እዚህ መድረክ ላይ ስለ ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በርካታ ርዕሶችን የጻፍኩኝ ብሆንም ስለ ግምታዊ መለኮታዊ ክስተት ይህ ርዕስ የመጀመርያዬ ነዉ።
ክስተት ያልኩኝ የተከሰተ ነገር ስለሆነ ነዉ።
መለኮታዊ ያልሉኝ ከመለኮታዊ አሰራር ዉጪ ይህን ክስተት ማብራራት የሚችል ሌላ መንገድ መኖሩን በፍጹም ስለማላዉቅ ነዉ።
ግምታዊ ያልኩኝ ያየሁትን የማዉቀዉ እኔ ብቻ ነኝ ብዬ ስለማምን ነዉ።
ሜይ 18፣ 2026፣ ለሊት ኣንድ የአጎቴ ልጅ ያማረባት ልብስ ለብሳ ከሌሎች ሴቶች ጋር ቀብር ስትሄድ ሕልም ኣየሁኝ።
ረጅም እንደነበረች ኣዉቃለሁ። ያየሁኝ ሕልም ዉስጥም ከሁሉም ረዘም ብላ ጎን ለጎን ተርታ ገብተዉ እሷ መሃላቸዉ ሆና ነዉ።
ራቅ ያለ ባላገር ትኖር ስለነበረ ከሃገር ሳልወጣ በፊት ጀምሮ ተገናኝተን ሆነ ተነጋግረን ኣናዉቅም።
እኔ ሕልሙን በክፋት ሳላየዉ ማስታወሻ ይዤ ዝም ኣልኩኝ።
ጁን 2፣ 2026፣ ለሌላ ጉዳይ ዘመድ ጋ ደዉዬ ሰለወንድሟ ሠላምታ ስጠይቅ በሕልም ያየኋት የአጎቴ ልጅ ኣርፋ ሀዘን ላይ ናቸዉ የሚል መርዶ ሰማሁኝ።
በሕልም ኣይቻት ነበረ ብዬ በጣም ኣዘንኩኝ።
በጣም የሚገርመዉ እሷ ኣረፈች የተባለ ቀን እና እኔ ሕልም ያየሁኝ ቀን መቀራረባቸዉ ነዉ።
ስለዚህ እኔ ይህን ክስተት ከመለኮታዊ አሰራር ዉጪ ልያብራራዉ የሚችል ሊኖር ይችላል ማለት በጣም ይከብደኛል።
ይህ ክስተት የተገለጠዉ እዚህ መድረክ ላይ ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉ ሰዎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ እግዝኣብሔር ዬለም ሲሉ እኔ ተዓምራትን የምያስቆጥር ሌላ ምንድነዉ እያልኩ ለብቻዬ ስከራከር ከሰነበትኩ በኋላ ነዉ።
ለብቻዬ ስከራከር ድሉዥናል ተብያለሁ።
ይህ ክስተት ከተገለጠ በኋላም ከመለኮታዊ አሰራር ዉጪ ማብራራት የሚችሉበትን መንገድ ይኖራቸዉ ይሆን?
ሕልሙን ከኣንተ ሌላ ማን ኣየ ሊሉ ይችሉ ይሆናል። ሰዉ ሕልምን ለማየት ተዘጋጅቶበት በቪድዮ ሆነ በሌላ ቀርጾት ለማስረጃ ማቅረብ የሚችል ኣይመስለኝም።
ማስረጃዉ ምልክቶችን የምያሳይ ኣንዴ ብቻ ኣሳይቶ የምያቆም ኣይመስለኝም።
ምልክቶችን የምያሳይ መኖሩ እንደዚህ ዐይነት ክስተቶች ማስረጃዎች ሲሆኑ እግዝኣብሔር ዬለም ያለን በቁሙ እና ለዘላለሙ መቅበሩ ይሆናል ብዬ ኣምናለሁ።
እግዝኣብሔር መኖሩ በዐለም ላይ ከነገሰ ዐለም ሁሉ ኣማኝ ሆነ ማለት ይሆናል።
ስለዚህ እኔ ሕልሙን ለመፍታት የሞከርኩኝ ከሁሉም ረዘም ብላ ያማረባት ልብስ ለብሳ ቀብር ስትሄድ ያየሁኝ የአጎቴ ልጅ እግዝኣብሔር ዬለም ያለን ለመቅበር እግዝኣብሔር ለእኔ ልኳት መኖሩን የገለጠ መሆኑን ነዉ።