የአብይ አህመድ ተቋም ውሸት እና የቤተክነቱ ተቃውሞ
Posted: 10 Jun 2026, 01:36
" ... ከተገደሉት ውስጥ የእስልምና እምነት ተከታይ ይገኝበታል። ነገር ግን ኮሚሽኑ 3 ሰዎች ብቻ እንደተገደሉ አድርጎ ያቀርበው ሪፖርት ከእውነት የራቀ ነው " - የአሰኮ ወረዳ ቤተክህነት
በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ግንቦት 23 እና 24 ቀን 2018 ዓ/ም በታጣቂዎች የተፈጸመውን ጥቃት መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያሳወቀውን የሟቾች ቁጥር ወረዳ ቤተክህነቱ ተቃወመው።
በወረዳው ግድያ መፈጸሙ የሚታወቅ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ " በምሥራቅ አርሲ 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምዕመናን መፈናቀላቸውንና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን " በወቅቱ አሳውቀዋል።
ነዋሪዎች የሟቾቹን ብዛት ከ13 በላይ ያደረሱት ሲሆን፣ ሌሎች የጠፉ እንዳሉ መግለጻቸው ይታወሳል።
የአሰኮ ወረዳ ቤተክህነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ 13 ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጦ ሌሎች የጠፉ እንዳሉ ተናግሯል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ይህንኑ ጥቃት አስመልክቶ ትናንት ባወጣው ሪፖርት፣ ሟቾቹ " ሁለት የክርስትና እምነት ተከታዮች " እና " አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ "፣ በአጠቃላይ "ሦስት" መሆናቸውን ገልጿል። ከተቃጠለው የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ባለፈ የሼክ ሙስተፋ መስጅድ አጥር ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክቷል።
የኢሰመኮ ሪፖርት ከወጣ በኋላ ስለግድያው ገለጻ የሰጡን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ በዞኑ ሀገረ ስብከት የአሰኮ ወረዳ ቤተክህነት አመራር፣ " ቦታው (ግድያ የተፈጸመበት) ላይም ሄደናል፤ የተገደሉት 13 ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
ከተገደሉት 13 ሰዎች መካከል አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ይገኝበታል ብለዋል።
" 282 ቤቶች፣ አንድ ቤተክርስቲያን ተቃጥለዋል" ያሉት እኚሁ አካል፣ ሰሞኑን በተሰራው ሪፖርት መሰረት ደግሞ ተፈናቃዮች ከ2,500 በላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። " የወደመው ንብረት ግን ቁጥርም ልክም የለውም " ነው ያሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአሰኮውን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት የተገደሉት "ሦስት" ሰዎች ናቸው ብሏል፣ እናንተ ደግሞ "13" ናቸው ብላችኋል፤ ይህ አይጣረስም ? ሲል የወረዳ ቤተክህነት አመራሩን ጠይቋቸዋል።
እሳቸውም፣ ወረዳ ቤተክህነታቸው ለኮሚሽኑ የገለጸው፣ "13" ሰዎች እንደተገደሉ፣ ከ2,500 በላይ እንደተፈናቀሉ መሆኑን ጠቅሰው፣ " ስንት ልጆች እንዳላቸው፣ ስንት ቤተሰብ እንደተገደለባቸው ከተፈናቃዮች በትክክል ዳታ ሰርተን እንጂ ተባለ በሚል አይደለም " ብለዋል።
እኝሁ አካል የኢሰመኮን ሪፖርት " ከእውነት የራቀ፤ ስህተት ነው። አግባብም ትክክልም አይደለም። በቦታው ላይ የመንግስት አካላትም መጥተው አይተዋል " ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
በተያያዘ በሰሞኑ ጥቃት አሰኮ ወረዳ የተገደሉት ሰዎች ብዛት በማህበራዊ ሚዲያዎች " ከ30 በላይ " ተደርጎ ሲገለጽ ተስተውሏል፤ እውነቱ የትኛው ነው ? ስንል የጠየቅናቸው የቤተክህነቱ አካል፣ " እሱ ስህተት ነው " ብለዋል።
" እኔ እውነት ነው የምናገረው። እነርሱ የዘገቡት በአርሲ ሲባል በሺርካም በሌሎችም ቦታዎች የተገደሉትን ጨምር ካልሆነ በስተቀር እንጅ እኛ ጋር በትክክል በእለቱ የተገደሉት ሰዎች 13 ናቸው " ሲሉ ገልጸው " ዘጠኙ በእለቱ የተገኙ ናቸው። ሌላ አንድ ቄስም ተገኝተዋል። አስክሬናቸው በ5ኛው፣ በ6ኛው ቀን የተገኘ፤ ገና ደግሞ ያልተገኙ ይሙቱ ይኑሩ ያልታቁም አሉ " ብለዋል።
" በተጨባጭ የተቀበሩት 13 ናቸው። አሰኮ ቅድስት ማርያም፣ እሬቻ ቅዱስ ሚካኤል፣ ካሪ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ነው የተቀበሩት " ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላኛው የወረዳ ቤተክህነቱ አካልም፣ " ከ30 በላይ " ተብሎ የተጠቀሰው ከዚህ በፊት በዞኑ የተገደሉትን ተጨምሮ ተጠቅሶ ካልሆነ በስተቀር አሁን ስለ ወረዳው እየተሰራጨ ያለው ስህተት እንደሆነ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል፣ "ከጥቃቱ" ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ የወረዳ አካላት እንዳሉ ተነግሯል፤ እውነት ነው ? ስንል የጠየቅናቸው የመጀመሪያውን ገለጻ የሰጡን የወረዳ ቤተህነቱ አካል፣ " በድርጊቱ ይሳተፉ አይሳተፉ ባላውቅም ግን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አባቡ አብደላ በቁጥጥር ስር ውለዋል " ብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የስልክና የፅሑፍ ምላሽ ባለመስጠታቸው፣ የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀትጉሃን ከፍያለው ሽንቁጤ፣ " አሁን ስብሰባ ላይ ነኝ " በማለታቸው ሀሳባቸው ለጊዜው አልተካተተም።