Page 1 of 1

አበርገሌ ወረዳ በአዴን Aka በ ኣገው ታጣቂ ቡድን ቁጥጥር ስር መዋሉ.(((HAHAHA))).!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 04 Jun 2026, 13:49
by tarik
አበርገሌ ወረዳ በአዴን ታጣቂ ቡድን ቁጥጥር ስር መዋሉ
ኢሳያስ ገላው
ከ 39 ደቂቃዎች በፊትከ 39 ደቂቃዎች በፊት
በአማራ ክልል ዋግ ህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሚገኘውን የአበርገሌ ወረዳን በሚያዝያ ወር የተቆጣጠረው እራሱን የአገው ዲሞክራሲ ሕብረት (አዴን/አገው ሸንጎ) ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፣ ባሳለፍነው ግንቦት 19 ቀን ሁለተኛውን የጻግብጂ ወረዳን በኃይል መቆጣጠሩንና በዚህም ሳቢያ የወረዳዉ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/5ErMJ
ሰቆጣ ከተማ
ሰቆጣ ከተማ ፎቶ ከማኅደርምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW
አበርገሌ ወረዳ በአዴን ታጣቂ ቡድን ቁጥጥር ስር መዋሉ

03:49




በሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. እራሱን የአገው ዴሞክራሲ ሕብረት አሊያም ያገው ሸንጎ ብሎ የሚጠራው የታጣቂ ቡድን በአማራ ክልል የዋግ ህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አንድ ወረዳ የሆነውን አበርገሌን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ባሳለፍነው ግንቦት 19ም ሁለተኛውን የጻግብጂ ወረዳን በኃይል መቆጣጠሩን እና በርካቶች መፈናቀላቸውን የወረዳው ነዋሪዎች ተናገሩ።

ከወረዳው 06 ቀበሌ የተፈናቀሉት አቶ ይግዛው ይስማው እንደሚናገሩት፣ በግንቦት 19ኙ ጥቃት በርካቶች አካባቢያቸውን ለቀው መውጣታቸውን እና በበረሃም ያለመጠለያ ቀናትን እያሳለፉ መሆኑን ይናገራሉ።

«እንግዲህ ስንወጣ አንድ ዕቃ ይዞ የመጣ ሰው የለም። ሁሉም ባዶውን ነው የወጣው፤ የወጣንብረት የለም፣ መኪና አይቀር ሁሉ አመራር አይቀር ተትቶ ነው የመጣው። እስካሁን ድረስ እኛም ያለነው ወደ ቆላ አካባቢ ላይ በረሃ ላይ ነው ያለነው። የሚበላ የለም የሚጠጣ የለም፣ ሕዝብም ቢሆን ተነግሮ የማያልቅ ነገር ላይ ነው ያለነው። ንብረት ብዙ ምንም የወጣ ንብረት የለም፤ ሁሉ ማኅበረሰቡ ሳይቀር፣ ታጣቂው ሳይቀር፣ አመራሩ ሳይቀር የወረዳ ንብረት፣ የመንግሥት ንብረት፣ የወጣ ንብረት አንድም የለም።"

የጻግብጂ ወረዳ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎም በርካቶች ወደ ዞኑ ዋና ከተማ ሰቆጣ ቢያመሩም፣ ምንም ዓይነት ሰብአዊ ድጋፍ ባለፉት ስድስት ቀናት አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

«እኔ ገብቻለሁ ከከተማ ላይ፤ ሕዝቡ ግን ጫካ ላይ ያለውም አለ፣ ከከተማ የገባውም አለ። ብትንትን ብሎ ነው ያለው። ሕጻን የያዘው በቃ ስቃይ ላይ ነው ያለው። ሴትም አለ ወንድም ብዙ ነው፤ ወንድም አለ ሴትም አለ። ሕዝብ … የቀረ ሕዝብ ሁሉ የለም እዛ።»

በተለይም የፖለቲካ ልዩነት የነበራቸው የጻግብጂ ወረዳ ነዋሪዎች እና የመንግሥት ሠራተኞች አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸው ነው የተገለጸው።

በግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. አበርገሌ ወረዳን የተቆጣጠረውን ታጣቂ ቡድን በመፍራትም ወደ ሰቆጣ ከተማ ከተፈናቀሉ ከአንድ ወር በላይ ያስቆጠሩ በርካታ ነዋሪዎችም እስካሁን ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው ይገልጻሉ።

«እኛ አማራጭ ስላጣን ነው እንጂ፣ መሄጃ አጥተን ነው እንጂ። እዚህ ልጆችን ይዘን ዝም ብለን አፈር ላይ በቃ ቆሻሻ ላይ ነው ያለነው፤ እኛም መሄጃ አጣን በቃ። በምናገኘው ሁሉ ነው የምናድረው በቃ።»

በግጭቱ ምክንያት ከኮረም፣ ዋፍላ፣ አበርገሌ፣ ዛታ፣ አላማጣ አሁን ደግሞ ከጻግብጂ ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን የምታስተናግደው ሰቆጣ ከተማም የተዘጋጀ መጠለያ ባይኖርም በየዕለቱ ግን አዳዲስ ተፈናቃዮችን እየተቀበለች ትገኛለች።

በጉዳዩ ዙሪያ ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉን የጠየቅናቸው የዋግ ህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአደጋስጋት እና ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ምህረት መላኩ «ጊዜ የለኝም» በማለት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በአዴን አሊያም በአገው ሸንጎ ታጣቂዎች የተያዙ ሁለት ወረዳዎችን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡን የዋግ ህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ወደሆኑት አቶ ሹመት ጥላሁን ስልክ ብንደውልም፣ የጽሑፍ መልዕክት ብንልክም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ኢሳያስ ገላው

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ