Page 1 of 1

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 03 Jun 2026, 07:45
by MINILIK SALSAWI
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።››
(መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪)

በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።
የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው።

የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።

በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።

በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 03 Jun 2026, 16:08
by Naga Tuma
MINILIK SALSAWI wrote:
03 Jun 2026, 07:45
ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
አሐዱ አምላክ
አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።
ብፁዕነትዎ፥

ይህን አስተያየት የምጽፍ ኣንድ ግለሰብ ነኝ።

ስለ መለኮታዊ ነገር ከእርስዎ በላይ ኣዋቂ ነኝ ብዬ እርስዎን ልምከር ማለት ይከብደኛል።

ተዓምራትን እየቆጠርኩኝ ለእርስዎም እንዲገለጡ ኣለማካፈል ሃጥዓት ይሆንብኛል የሚል ግምት ኣለኝ።

እርስዎም ተግተዉ ካላጠኑት ታሪክ ይሆንብዎታል።

ይህን ኣሳዛኝ መልዕክትዎን ሳላይ በፊት ዛሬ ጠዋት በሁለት ትዉልዶች ዘመን ስለ ታዩት ሕልሞች ከዘመዴ ጋር በስልክ ተወያየን።

የመጀመርያዉ ሕልም የታየዉ ኣፄ ሀይለ ሥላሴ ሕይወታቸዉ ያለፈ ግዜ ነዉ።

መምህሬ የነበሩ የፈረስ ዕቃ የተበጀለት ፈረስ ላይ ሆነዉ ቤተክርስትያን ሲሄዱ ሕልም ኣዩ።

ሕልሙን የሰማ የቅርብ ጓደኛ ፌዝ ኣድርጎት ልታርፍ ነዉ ወይ ኣለ ተብሎ ይተረክ ነበር።

ሕልሙን ያዩት ቀናት ሳይቆዩ ኣፄ ሀይለ ሥላሴ ያረፉ ቀን ኣረፉ ኣሉ። ይህ ታሪክ ያለ ስለሆነ ማጣራት ይቻላል።

ሌላ ሕልም እኔ ግንቦት ቀን 11፣ 2026፣ ዓም ንጋት ላይ ያየሁኝ ነዉ።

የእኔ ዘመድ ያማረባት ልብስ ለብሳ ከሌሎች ሰዎች ጋር ቀብር ስትሄድ ኣየሁኝ።

በወቅቱ ሕልሙ የምያሳዝን ኣልመሠለኝም።

ትላንትና ዘመድ ጥየቃ ስልክ ደዉዬ በሕልም ያየሁዋት ዘመዴ ኣርፋለች የሚል መርዶ ሰማሁኝ።

በጣም ኣዘንኩኝ።

ምናልባት እግዝኣብሔር በተዓምራዊ መንገድ መርቶኝ አሓዱ ኣምላክ ብሎ በምድር ላይ ለመጀመርያ ግዜ የሰዉ ልጆችን መንገዱን ያሳየዉ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ የነበረ መሆኑን የደረስኩበት ከሃያ ዓመታት በፊት ነዉ።

ዋቀ ቶክቸ ኤንደ ሞኖቴይዝም የሚል ረጅም የመወያየ ርዕስ ጀምሬ ነበር።

አሓዱ ኣምላክ፣ ዋቀ ቶክቸ፣ እና ሞኖቴይዝም ኣንድ ጽንሰሀሳብ ኣላቸዉ።

እኔ ከሃያ ዓመታት በፊት የደረስኩበትን የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንም ከሃምሳ ዓመታት በፊት ደርሶበት የነበረ መሆኑን ከበርካታ ዓመታት በፊት ሰማሁኝ።

ሎሬቱ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ለካ ኣንተ ነህ! ያለዉን መጥቀስ ብቻ በቂ ነዉ።

ያ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ከስደት በፊት ስሙ አክናተን ይባል ነበር።

ትርጉሙ አሙን ረክቷል ማለት ነዉ ይባላል። አሓዱ ኣምላክ የሚል መለኮታዊ መንገድ ያሳየዉ አሙንን ወይም እግዝኣብሔርን ኣርክቷል ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ንግስት ሕዝብ ቀስቅሳበት ለስደት ተዳረገ ይባላል።

ከስደት በኋላ የእስራኤል ነብይ ወይም ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ነዉ።

የጥንት አክሱማዊያን በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተረገማችሁ ናችሁ የተባሉ ግዜ ግራ ተጋብተዉ ለሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ ያዘገመ የማንነት ትግል ዉስጥ ገቡ የተባለ ታሪክም ተጽፏል።

ፕሮፌት ሙሴ እስራኤሎችን እኔ የመረጥኳችሁ ኣላቸዉ እንጂ የእስራኤል ሕዝብ እግዝኣብሔር የመረጠን ነን ኣላሉም የሚል ታሪክን በሁለተኛዉ የዐለም ጦርነት ዋዜማ ለዐለም የጻፈዉ መሠረቱ ኣይሁዳዊ የሆነ ሰዉ ነዉ።

ይህ ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታቦት የሚሸከመዉ እና የሚጠብቀዉ የእስራኤል ፕሮፎት የተባለዉ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይን ዐስርቱ ትዕዛዛት ነዉ ማለት ነዉ።

ይህ ማለት የጥንታዊ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሁለት ጎኖች ኣሉት ማለት ይሆናል።

ኣንዱ ጎኑ የቅድመ ስደት አሓዱ ኣምላክ ነብይ ሲሆን ሌላዉ ጎኑ ተሰቅሎ ኣዳኝ የተባለዉ ይሆናል ማለት ነዉ።

ካልተሳሳትኩኝ ወስብሓት ለእግዝኣብሔር ማለት ስለ ኣረፉት ለእግዝኣብሔር ማለት ነዉ።

ስህተት ካልሆነ ይህ አስተሳሰብ ከክርስትና በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበረ ለመሆኑ ደበሳ ጉዮ የተባለ የቦረና ሰዉን ኣንድ ግዜ ጠይቄዉ ተመሳሳይ መሆናቸዉን ኣስተዉያለሁ።

የኣርባ ቀን ተዝካር በኦርቶዶክስ በኩል እና የቦረና ሰዉ ህይወቱ ያለፈ ሰዉ የእግዝኣብሔርን ፍርድ የምያገኘዉ በኣርባኛዉ ቀን ነዉ ማለት ተመሳሳይ ናቸዉ።

የእኔ የኢትዮጵያ ህዳሴ ጥሪ ይህን ሁሉ ያስተዋለ ነዉ።

በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ ቡድሃዎች እግዝኣብሔር ዬለም ብላችሁ እየሱስ በሉ ማለት የአደባባይ ምስጥር ሆኗል።

እኔ ይህንን የስምንተኛዉ ሺህ ዘመን ዳያብሎሳዊ ንግስና ብየዋለሁ።

ተዓምራትን እየቆጠርኩኝ ወይም እያስቆጠረኝ ስለሆነ ነዉ።

ተዓምራትን የምያስቆጥር እግዝኣብሔር ህያዉ ሆኖ የእስራኤል ኣዳኝ ለተባለዉ ሳይሆን ለአሓዱ ኣምላክ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ምልክቶችን የምያሳይ ከሆነ የሰዉ ልጅ ሆነ እግዝኣብሔር ዬለም ያለ ዳያብሎስ የእግዝኣብሔርን ተዓምራት መፈታተን ይችላል?

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 03 Jun 2026, 18:29
by Naga Tuma
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቃሉ፣ ለካ ኣንተ ነህ! ያለዉ ከስደት በፊት የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ታላቅ ፈረዖ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙጫ/ሙጬ/ሙሴ መሆኑን ተነባቢ የአስር ምስጥር ካለዉ መገመት ይቻላል።

አደጌን ቃሉ ጄቹ ህን ቤክኔ
አደጌን ቃሉ ቤካ ህን ሴኔ
አደጌን ቤካ ህን ቤክኔ
አደጌን ቤኩምሰ ህን ቤክኔ
አደጌን መዳን ጉረ ህንሴኔ
ጄቴ በር አደዊን ደቺ ሴኔ

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 03 Jun 2026, 18:48
by Naga Tuma
የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ዘላለማዊ ቃላት

የማይነጋ ሕልም ሳልም
የማይድን በሽታ ሳክም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የሰዉ ሕይወት ስከረክም
እኔ ለእኔ ኖሬ ኣላዉቅም

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 03 Jun 2026, 22:48
by Naga Tuma

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 04 Jun 2026, 21:18
by Naga Tuma
እላይ የጠቀስኩኝን ሕልም ያየሁኝ የሚከተለዉ ርዕስ ስር የጻፍኩትን ሕልም ያየሁኝ ሳምንት ነዉ።

ቀልድ እና ቁምነገር፥ ሕልም እና ቅዠት ቁጥር 4

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 04 Jun 2026, 21:59
by Naga Tuma
እኔ ተዓምራትን የምቆጥር እነዚህን ሁለቱ ተከታታይ ሕልሞችን ያሰላሰልኩኝ ስለ መለኮታዊ አሰራር መሆናቸዉን ነዉ።

ኣንዱ ሕልም ዉስጥ ሰምቼ የማላዉቀዉን ዘፈን መስማቴን እና ሌላዉ ሕልም ዉስጥ ረጅሞ ዘመዴ ተሞናሙና ቀብር ስትሄድ ማየቴን ያሰላሰልኩኝ መለኮታዊ አሰራር በጥንት ኢትዮጵያ ፈረዖዎች በኩል እንደ ምልክት መገለጡን ነዉ።

ዘበት ዕዉነትን ማሸነፍ ኣይችልም።

ንግስት ሳባ እና ንጉስ ሰለሞን የኖሩበት ዘመናት የተራራቁ ስለሆነ የቀዳማዊ ምንልክ መወለድ ዘበት ነዉ ከተባለ የኣፄ ሀይለ ሥላሴ ነገድ ቆጥሮ መንገስም ዘበት ነዉ ማለት ይሆናል።

የአሓዱ ኣምላክ ቀዳማዊ አባት ታላቅ ፈረዖ የነበረ መሆኑ ዕዉነት ነዉ ተብሏል።

እነዚህ ታሪኮችን መካድ የማይቻል ከሆነ፣ እግዜር ተዓምራትን እያስቆጠረ የምያሳይ ከሆነ ማን ሊፈታተነዉ ይችላል?

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 04 Jun 2026, 22:21
by Naga Tuma

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 05 Jun 2026, 00:55
by MINILIK SALSAWI
የአርሲ ኦርቶዶክሳውያንን የጅምላ ፍጅት ለምን ማስቆም አቃተን?
======
** "እኛስ ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?" (1ኛ ቆሮንቶስ 15÷30)
** የምዕመናንን መብት ማስጠበቅ የሚለው በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ለምን የለም? |
** ቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባዔ ለምን አይጠራም?
=====
መከራ ሲበዛ፣ ኃዘን አንገትን ሲሰብር፣ ተመሳሳይና ተደጋጋሚ መከራ በተመሳሳይ መንገድ ወገናችንን ሲፈጅ ግና መፍትሔ ማበጀት ሲያቅተን ቃላት ራሳቸው ትርጉም ያጣሉ። አርሲን በተመለከተ ለብዙ ዘመን ጮኸናል፣ አልቅሰናል። ግን ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም።

ጠላቶቻችን መላገጫ፣ መሳቂያ መሳለቂያ አድርገውናል። አዕምሮ እንደሌላቸው ድኩማን፣ አቅም እንደሌላቸው ምንዱባን፣ ሀገር እንደሌላቸው መጻተኞች ቆጥረውናል። እኛም በርግጥ ከመናገርና ከመጮህ የዘለለ በአንድነት ትርጉም ያለው ሥራ ለመሥራት እንደማንችል አስመስክረናል:: የጠላቶቻችን መላገጫ መሆናችን አላንገበገበንም።

እነሆ አሁንም አርሲ በክርስቲያን ደም እየጨቀየ ነው። ከቅ/ ፓትርያርኩ ጀምሮ ሁሉም የኀዘን መግለጫ አውጥቷል። ግን መግለጫዎቹ የክርስቲያኑን የጅምላ ፍጅት አላስቆሙም፣ አያስቆሙምም። ምን ይሻላል ጎበዝ? ከዚህ በፊት ያልሞከርነው፣ ነገር ግን የግድ ልንፈጽመው የሚገባ ርምጃ ምንድነው?

https://www.youtube.com/live/X49SplSo6F ... HhwQImabWW

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 05 Jun 2026, 05:17
by Naga Tuma
እኔ ድሮ የማዉቀዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሃይማኖት መሪዎችን መሪህ ይሰማል።

የአርሲ የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና፣ እና የባህላዊ ሃይማኖት መሪዎች የማይተዋወቁ ናቸዉ?

የሚተዋወቁ ከሆነ ተሰብስበዉ ለሕዝቡ ሰላም ማስፈን እንዴት ተሳነን ማለት ኣይችሉም?

ጋዜጠኞችን ኣሳትፈዉ መወያየት ኣይችሉም?

ይህ ኣንድ ሀሳብ ነዉ።

የጥንታዊ ኢትዮጵያ ህዳሴ ብሎም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ መሠረቱ ኣንድ የሆነ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ፈረዖ የነበረ ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ ወይም ነብዩ ሙሳ የተባለ ነዉ ማለት ምንድነዉ የሚሉ ልሂቃን የሕዝቡን ህሊና ማንቃት ኣይችሉም?

ለመሆኑ ሃገራዊ የምክክር ኮምሽን የተባለዉ እንደዚህ ዐይነት እልቂት እንዲቆም ማድረግ የማይችል ነዉ?

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 05 Jun 2026, 05:27
by Naga Tuma
የዘመዴን ያማረባት ልብስ ለብሳ ዘለግ ብላ ቀብር ስትሄድ ሕልም ኣይቼ ማረፍዋን መርዶ መስማቴን ሳሰላስል እግዜር ዬለም ያለዉን ዳያብሎስ ልትቀብር የሄደች ይመስለኛል።

ምክንያቱም እንደዚህ ዐይነት ተዓምራዊ ሕልም የምያሳይ እግዜር ካልሆነ ሌላ ምንድነዉ?

እንደዚህ ዐይነት ተዓምራዊ ሕልም የምያሳይ እግዜር ነዉ ከተባለ መኖሩን ኣስመሰከረ ማለት ይሆናል። ኣይዴለም?

Re: ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት

Posted: 06 Jun 2026, 01:05
by Naga Tuma
የሚከተለዉን ርዕስ የጀመርኩኝ ያለምክንያት ኣልነበረም።

የጥንት ኢትዮጵያ ፈረዖዎች ተዓምራዊ አነሳስ በዚህ ዘመን

ጥንታዊ ኢትዮጵያ የስደት ንስሃ እንጂ የስቅለት ንስሃ ኣልነበራትም።