ካልቸር ሃሳብ አይደለም ፤ የፖለቲካ ምርጫ ግን ካልቸር ነው! የአበሻ ችግር ደሞ ይህ ነው!
Posted: 02 Jun 2026, 10:56
እኔ ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም።
ትላንት የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ምርጫ አድርጓል ። የፖለቲካ ምርጫ የአንድ ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ካልቸር ነው ። እሱም የፖለቲካ ውሳኔ መወሰኛ ዘዴ ወይም ስልት ማለት ነው።
ሶስት ሺ ዘመን እድሜ ያላት ኢትዮጵያ ሰባት ግዜ ብቻ ብሄራዊ የፖለቲካ ምርጫ ማድረጓ ኢትዮጵያ የምርጫ ካልቸር እንደ ሌላት መቶ በመቶ የሚያረጋግጥ መረጃ ሃቅ ነው።
ዘመናዊ ፖለቲካ እንደ ዛፍና አበባ በራሱ ተፈጥሮ የሚያድግ ነገር አይደለም ።
የፖለቲካ ስርዓት ሆን ተብሎ በእቅድ ፣ በኢንቴንሽ ፣ ታስቦበት የሚፈጠር ማህበራዊ ስራ ነው ። የፖለቲካ ስርዓት መሰረቱ የፖለቲካ ሃሳብ ፣ የፖለቲካ ፍልስፍናና የፖለቲካ ቲኦሪ ቢሆንም ሃሳብ በራሱ ካልቸር አይሆንም።
የፖለቲካ ካልቸር የሚፈጠረው፣ የሚያድገው በስራ ነው ፤ በፕራክቲስ ነው፤ በሙከራ ፣ በጥረት ፣ ነው ፤ በተሞክሮ ነው።
ኢትዮጵያ እውነቱን እንናገር ከተባለ ፣ ብሄራዊ የፖለቲካ ፍልስፍና የላትም፤ ብሄራዊ የፖለቲካ ቲኦሪ የላትም ፤ ብሄራዊ የፖለቲካ ካልቸር የላትም ።
ለምሳሌ ትላንት የሆነውን እንመልከት ...
ምርጫ ካልቸር ነው ብያለሁ ፣ ካልቸር ደሞ የሚሰራው በስራ ፣ በተግባር ነው ብያለሁ ። ትላንት የሆነው ያ ነው። አንድ ትንሽዬ የምርጫ ካልቸር የመፍጠር ትንሽዬ ሙከራ ።
በሌላ በኩል ሰላማዊ ተፎካካሪዎችና የአመጽ ተፎካካሪዎችን ተመልከቱ ...
ሰላማዊ ተፎካካሪው አንድ ብሄራዊ ፓርቲ ማደራጀት ስላልቻለ በምርጫው ውስጥ ነበረ ማለት ስህተት ነው ። የምርጫ ካልቸር ለመፍጠር ጥረት አደረገ ማለት ፍጹም ስህተት ነው ። ካልቸር በወረቀት ላይ ሃሳብን ጽፎ መበተን አይደለም ። ካልቸር ስራ ነው ። ካልቸር ተግባር ነው።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ መደብ በኢትዮጵያ ገና አልተወለደም ። ይህም የሆነው ብሄራዊ የፖለቲካ ፍልስፍናና ቲኦሪ ያረቀቀ ብሄራዊ ተፎካካሪ ፓርቲ ስለሌለ ነው ።
በአመጽ ተፎካካሪው በመሰረቱ ኢትዮጵያ ለሶስት ሺ ዘመን ያገዛዝ ስርዓት ያከናወነችበት ቅድመ ፊውዳልና የፊውዳሊዝም ፖለቲካ ካልቸር ነው ። በትግሬ ፣ አማራና ኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ ገንኖ ያለው የአመጽ ተፎካካሪነት ካልቸር አልነቀል ያለው የፊውዳልና ቅድመ ፊውዳል ካልቸር ነው ። ይህ ደሞ እነዚህን ማህበረሰቦች በኋላ ቀርነት እስር ቤት ከርችሞ ያሰረ ታሪካዊ ችግር ነው ።
በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሪያሊቲ ይህ ነው።
ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍልስፍና የላትም ፤ የፖለቲካ ቲኦሪ የላትም ፣ የዘመናዊ ፖለቲካ ካልቸር የላትም ።
ብልጽግና ምንም አይነት ተፎካካሪ የሌለው፣ ያልነበረው ስለዚህ ነው ።