ታሪካዊ ሐቆች
1) እ ኢ አ በ1888 ዓም ገደማ መንግስቱ ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ዉስጥ ያቋቋመዉ ኣዲስ ኮሌጅ ዉስጥ ስለ ኣንዱ የእንግሊዝ ሳይንቲስት ኒዉተን ቀመር ወይም ሎዉ ተማርኩኝ።
2) ኮርሱን ያስተማረዉ በወቅቱ ሌክቸረር የነበረ ዶክተር ስለሺ በቀለ ነዉ።
3) አሜሪካ የትምህርት ዕድል ኣግኝቼ ተምሬ ስራ ኣግኝቼ በጥቂት ወራት ዉስጥ ኢትዮጵያ የተማርኩኝ የስራ አሰራር ይኖራል ብዬ ስለገመትኩ እንድያሳየኝ ኣንድ የስራ ባለሙያ ጠየኩኝ።
4) የጠየኩት የስራ ባለሙያ ስለምን እንደጠየኩት ያላጤነ መሆኑን እና የጠበኩት አሰራር ኣለመኖሩን በኣጭር ግዜ ዉስጥ ግልጽ ሆነልኝ።
5) ለግዜዉ ተሰናብቼዉ የስራዉ አሰራር ባለመኖሩ እጅግ ተገርሜ ራመድ ራመድ እያልኩኝ ለብቻዬ ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮብሌም ኣልኩኝ።
6) የስራዉ አሰራር ኣለመኖሩ ብቻ ሳይሆን አሰራሩ ሳይኖራቸዉ ስራዉን እንዴት መስራት እንደቻሉ በጣም ደነቀኝ።
7) ይኖራል ብዬ የጠበኩኝን አሰራር ሰርቼ ለማሳየት ትልቅ ዕድል ነዉ ብዬ ተያያዝኩት።

አሰራሩን ኣብረን እንስራ እያልኩ ስወተዉትም ብዙ ግዜ ኣለፈ።
9) ሰርቼ ለማሳየት እድል ኣገኘሁ ያልኩኝን ስራ ሙጭጭ ብዬ ቁልጭ ኣድርጌ ኣሳይቼ እ ኢ አ በ2004 ዓም ኣንድ የኣሜሪካ የሙያ ጆርናል ዉስጥ ለማሳተም በቅቻለሁ። ይህን ሳይንሳዊ ስራ ስሰራ ተዋከብኩ ብል እንጂ ተደገፍኩ ማለት የምችል ኣይመስለኝም። አለቃ የነበረዉ እንደ ቡድሃዎች እግዝኣብሔር ዬለም ብሎ የምያምን መሆኑን ሆነ ኣለመሆኑን ኣላዉቅም።
10) እ ኢ አ 1996 ዓም ገደማ ተዓምራዊ የሆነ በሚመስል መንገድ ዶክተር ስለሺ በቀለ እኔ የምኖርበት ከተማ ጓደኛዉን ሊጠይቅ መጥቶ እግረመንገዱን ተገናኘን።
11) እኔ መምጣቱን ኣዉቄ እንገናኝ ብዬ ጠይቄ ሳይሆን እሱ በከተማዉ መኖሬን ሰምቶ እንድንገናኝ ጠይቆ ተገናኘን።
12) ከጓደኛዉ ጋር ለእራት ጋብዘናቸዉ መልካም ግዜ ኣብረን ያሳለፍን ይመስለኛል።
13) ግብዣዉ ላይ ዉይይት ተነስቶ ሁለቱ ጓደኞች ስለ ኣንድ ርዕስ ኣንድ ደቂቃ ላልሞላ ግዜ ተነጋገሩ። ኣንዱ ኢትዮጵያ ዉስጥ በዛን ወቅት ከነበሩት መሪዎች ዉስጥ ኣዕምሮ ያለዉ ኤከሌ ብቻ ነዉ ሲል ሌላዉ ኤከሌ እና ኤከሌ ናቸዉ ኣለ። እኔ ስለ ርዕሱ ኣንድም ነገር መናገሬን ኣላስታዉስም።
14) በዉጪ ሃገር ስለ ኢትዮጵያ የፖለትካ ዉይይት ሳነብ እና ኣልፎ ኣልፎ አስተያየት ስሰጥ ኖሬ እ ኢ አ 1996 ዓም መጀመርያ አከባቢ ያለኝን አስተያየት ላጋራ እና ወደ ኣካዳሚ ላተኩር ብዬ ባለ አረት ክፍሎች ትንታኔ ጻፍኩኝ።
15) ከዛ ትንታኔ በኋላ የኦሮምያ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እንዲዛወር መወሳኑን ዜና ሰማሁኝ።
16) ዉሳኔዉ እተዋለሁ ወደኣልኩኝ መልሶኝ ተቃዉሞ ለማስተባበር ጣርኩኝ።
17) የሃገር ዉስጥ ተቃዉሞን ለማስተባበር መረራ ጉድና ቀዳሚ ሚና የነበረዉ መሆኑን ዜና ባነብም የዉጪ ሃገሩን ተቃዉሞ ለማስተባበር የእነማን ጉልህ ሚና እንደሚበልጥ ኣላዉቅም።
18) እ ኢ አ 1997 ዓም ገደማ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተነሳ ፎቶ ሴረ ቱማ ገዳ ተብሎ ሎስ ኣንጀለስ ከተማ የተደረገ የማህበረሰብ ስብሰባ ዉስጥ በኣጋጣሚ ኣየሁኝ። ፎቶዉን ገና እንደኣየሁኝ ደንቆኝ ከዚህ ፎቶ በላይ ስለ ስልጣኔ አጀማመር የምያሳይ ምን ኣለ ዐይነት ጥያቄ መጠየቄንም ኣልረሳም።
19) ፎቶዉ ከኢትዮጵያ የተላከለት ሰዉ ኣንድ ግዜ እኔ የምኖርበት አከባቢ ለጉብኝት መጥቶ ተገናኝተን እኔ መኪና እየነዳሁኝ ዙርያዉን ኣይቶ ብይ ኩን ብየ ዋቅን ለፈ ቱቄ ፈካተ ያለዉን ብዙ ግዜ ኣስታዉሳለሁ። ዙርያ ክቡን ስያዩት ሰማይ ምድርን የሚገናኝ ስለሚመስል ነዉ።
20) እዚህ መድረክ ላይ ሰዎች መለኮትን ፍሩ ብዬ ኣንድ ርዕስ ጀምሬ ነበር።
21) ኣንድ ርዕስ ስር የሆረስን ኣንድ አስተያየት ኣንብቤ ኣማኝ ከሆንክ ብዬ መልስ ሰጠሁት።
22) ሆረስ መልስ ሲመልስ ዶክተር ስለሺ በቀለ እግዝኣብሔር ሲል የምያሳይ ቪድዮ ለጠፈ።
23) እኔ ኣማኝ ከሆንክ ማለቴን እና መልሱ ዉስጥ ዶክተር ስለሺ በቀለ እግዝኣብሔር ሲል መሰማቱን በደንብ ልብ ይበሉ።
24) እኔ ቪድዮዉ መኖሩን ሳላዉቅ በፊት ነዉ ኣማኝ ከሆንክ ያልኩኝ። ቪድዮዉን ሳይ በቅጽበት ያስታወስኩኝ ተዓምራዊ በሚመስል ሁኔታ ከዶክተር ስለሺ በቀለ ጋር እግረመንገዱን መገናኘታችን ነዉ።
25) ጻድቆች ኣይቀጣጠሩም የሚባል የሰማሁ ቢሆንም እዚህ የጠቀስኩኝን አስተያየት ልዉዉጥ ሳስታዉስ ኦምኒፕረዘንት ስለ ተባለዉ ጽንሰሀሳብ ያስታዉሰኛል።
ይህን ሁሉ ታሪካዊ ሐቆች እዚህ የምጽፍበት ምክንያት ኣንድ ብቻ ነዉ። ይህን ታሪካዊ ሐቆች ማንበብ የሚችል ኢትዮጵያ ሆነ ኤርትራ ዉስጥ ምሁር ሆነ መንፈሳዊ መሪ ኣለ ወይ ለማለት ነዉ።
ልብ ከተባለ የደርግ ዘመን የተቀሰመ ዕዉቀት እስከዚህ ዘመን ተዓምራትን የምያስቆጥር እግዝኣብሔር ኣለ እና እግዝኣብሔር ዬለም ክርክርን ያካትታል።
የደርግ ሃጥዓት ኣምባገነንነቱ ነበረ። ኢትዮጵያ ትቅደም ማለቱ ጽድቅ ነበረ።
ከኢትዮጵያ ነፃ ኣዉጪዎች ነን ባሉ ተዋከበ።
የደርግ ዘመን የተቀሰመ ዕዉቀት ሃገር ዉጪ ተዋክቧል ማለት ይቻላል።
የዚህ ዘመን ሌላ ማዋከብ ተዓምራትን የሚያሳይ እግዝኣብሔር ኣለ የሚልዉ እግዝኣብሔር ዬለም በሚሉ ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉ መሆኑ ነዉ።
በተያያዥ ገዳ የሚሉ እና ገዳም የሚሉ የጥንት ኢትዮጵያ ማህበረሰቦች መተባበር ሳይሆን ለየጎራ መሆን ያሳዝናል።