ሕልም እና ቅዠት፥ ይህኛዉ ቁምነገር ይሆን?
Posted: 27 May 2026, 16:27
ይህን ሕልም ያየሁኝ ግንቦት ቀን 16፣ 2018፣ ዓም ወደ ግንቦት ቀን 17 ሲነጋ አከባቢ ነዉ።
ከብዙ ዓመታት በፊት በመኪና አደጋ ህይወቷ ማለፉን መርዶ የሰማሁኝ ዘመድ በረት ያለዉ ቤት ዉስጥ ሆና ከርቀት ኣየኋት።
ከዛም ሰዉ ከቤቱ ይዟት ወደ በረቱ ወጥታ ስትቀመጥ ኣየኋት።
የተቀመጠችበት ቦታ ትንሽ ርቀት ላይ እናቷ ተቀምጠዉ ኣየሁኝ።
ህይወቷ ያለፈዉ ተቀምጣ ብዙ ሳትቆይ ከበረቱ ኣንድ ጥግ ወጣቶች ሁካታ ጀምረዉ ወደ እሷ ሲንቀሳቀሱ ኣየሁኝ።
እሷ ሁካታዉን ሰምታ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ ነበረችበት ቤት መራመድ ስትጀምር ኣየሁኝ።
ሰግቼ እያየሁኝ ሁካታዉ ዉስጥ ከፍ ያለ ድምጽ ሰማሁኝ። ከዛም ጀርባዋን መመታቷን እና የተመታችበት ቦታ መድማቷን ኣየሁኝ።
ደንግጬ ትተርፍ ይሆን እያልኩ እያየኋት ተንገደግዳ በፊት ለፊቷ ስትወቅ ኣየሁኝ።
ደንግጬ ከእንቅልፌ ነቃሁ።
የህይወቷን ማለፍ መርዶ የሰማሁኝን ግዜ ኣልረሳም።
እዚህ አሜሪካ ዉስጥ ጉዳይ ገጥሞኝ ታዝቤ ወደ ቤቴ ተመልሼ በጥቂት ቀናት ዉስጥ የሰማሁኝ መርዶ ስለነበረ ነዉ።
በህልሜ አጠገባቸዉ ተቀምጠዉ ያየሁኝ እናቷ በልጅነቴ ነጭ ሽንኩርት እንደማልወድ ሰምተዉ ቃሉ ተኡፊ ብለዉ የቀለዱብኝ ነበሩ።
እኔ በዛ ዕድሜ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ስለማላዉቅ ኣዲስ ነገር ሆኖብኝ ኣለፍኩኝ።
ይህ ሕልም ቀልቤን የሳበበት ምክንያት ህይወቷ በመኪና አደጋ በድንገት ያለፈዉ እንደተባለዉ የመኪና አደጋ ነበረ ወይስ ተንኮል ነበረበት ለማለት ነዉ።
ንፁሃንን ተንኮል ፈጸሙ ማለት ሃጥዓት ነዉ። ሕልሙ ቅዠት ነዉ ማለት ነዉ።
ምናልባት ተንኮል የነበረበት ከሆነ ሕልሙ ቅዠት ላይሆን ይችላል ማለት ነዉ።
በእኔ አስተሳሰብ ይህ ቅዠት ይሁን ሕልም በቀላሉ ማጣራት የሚቻል ይመስለኛል። የመኪና አደጋዉ ታሪክ ያለዉ ስለሆነ መርምሮ ማጣራት ከባድ ኣይመስለኝም።
ቁልፉ ጥያቄ ምናልባት፣ ምናልባት ተንኮል የነበረበት ከሆነ በሕልም የምያሳይ ምንድነዉ የሚለዉን ጥያቄ ያስከትላል።
አባቷ አያነ ኣክባሪ ስለነበሩ አያነ አባ ይሆን?
በምን ዐይኖቹ የምያይ እግዜር ኣለ ተብሎ በኢትዮጵያዊ የተተረተበት እግዜር እንደዚህ የምያሳይ ይሆን?