የብልጣብልጦች ቢዝነስ በቤተ ክርስቲያን
Posted: 27 May 2026, 00:14
የብልጣብልጦች ቢዝነስ በቤተ ክርስቲያን
1) ጵጵስና ፦በወር ከ50ሺ እስከ 70ሺ ብር ደምወዝ ያስገኛል።በዚህ ላይ ከቦታ ቦታ በተንቀሳቀሱ ቁጥር አበል ይከፈላል።ከሙዳየ ምጽዋት አለ።የሀብታም ማዕድ በመባረክ የሚገኝ ብር አለ። አሜሪካና አውሮፓ ሲኬድ የሚቀፈል የዶላር አለ። ታቦት በመነገድ የሚመጣ ብር አለ።ለኪስ ተብሎ በዓመት እስከ 300ሺ ብር ይሰጣል።
2) የከተሜ ምንኩስና፦የመነኩሴ መናሪያ ገዳም ነው ከተማ ለከተማ የሚዞሩት ምንኩስናን ለጽድቅ ሳይሆን ለእንጀራ መብያነት ይጠቀሙበታል።ሰብስቦ ወደ ገዳም መሸኘት ያስፈልጋል።
3) አስተዳዳሪነት፦አንድ ሰው እንደምንም ብሎ ወደ አስተዳደርነት ከመጣ ከአንድና ከሁለት ዓመት በኋላ ዘመናዊ መኪና ይገዛል ቪላም ይገነባል ዘመዶቹን በሙሉ በ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰበስባል።ዋሸሁ እንዴ?
4) በአንድ አጥቢያ ብዙ ታቦታትን መደራረብ ፦ በአንድ አጥቢያ ብዙ ታቦታትን በማብዛት በነዚህ ታቦታት ወራዊና ዓመታዊ በዓላት ሚነግሱበት ዕለት ይኽን አመካኝቶ የሕዝቡን ኪስ ማጠብ ከዚያን ለግል ዓላማ ማዋል።
5) የሕንጻ ግንባታ፦ የተሠራ ቤተ ክርስቲያን እያለ ሌላ ቤተ ክርስቲያን መጀመር ከዚያን ቶሎ ተሠርቶ እንዳያጠናቀቅ ማዘግየት።ሕንጻው ቶሎ የሚጠናቀቅ ከሆነ የሕዝቡን ኪስ ለማጠብ አይመቻቸውም። ስለዚህ ያላቸው አማራጭ ሕንጻው ቶሎ እንዳይልቅ ማጓተት ነው።በደብራችሁ ይኽ የለም?
6) ጉባኤያትን ማብዛት፦ የጉባኤ ትልቁ ዓላማ ወንጌልን ማስተማር ቢሆንም ቅሉ ትንሽ ቆሎ ይዘው ወደ አሻሮ ጠጋ እንዲሉ አበው በወንጌሉ አመካኝቶ" ካባ ለባሽ ፕሮፌሽናል ለማኞችን" ተከራይቶ በማምጣት ሕዝቡን በሆሆህታ ሞቅ ሞቅ እያደረጉት እያካዋከቡት የቅዱሳንን ስም እየጠሩ እስቲ በእገሌ አማላጅነት የምታምኑ እጃችሁን ከፍ አድርጉት ከፍ ከፍ ይህ እጃችሁ እንዲባርክ አጨብጭቡበት
ከዚያን ወደ ኪሳችሁና ቦርሳችሁ ክተቱት
በሉ በኪሳችሁና በቦርሳችሁ ያለውን አውጥታችሁ ስጡ።ስጡ! ዛሬ ቤታችሁ ሁሉ ሙሉ ሆኖ ይቆያችኋል።እንዲህና እንዲያ እያሉ ኑሮ ከብዶት መሄጃ ያጣውን ምስኪኑን ሕዝብ ያጥቡታል።
7) ሰባኪነት፦ ይኽም ወፍራም ብሮችን ያስገኛል።አንድ ሰባኪ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ጎንደር ወይም ሐዋሳ ለመሄድ ከ100ሺ እስከ 200ሺ ልጠይቅ ይችላል።ይኽ ካስተሟላለት አይንቀሳቀሳት።
ዘማሪነት፦ ይልቁኑ የእመቤታችን ስም ጥሩ የእንጀራ መብያ ሆኗል።ተራራውን ወጣሁ፣ቁልቁለቱን ወረድሁ፣ወንዙን ተሻግርሁ፣ጫካውን አለፍሁ፣ጓደዬን ሞላ ወዘተ...የሚሉ ለዘፈን የቀረቡ መዝሙሮችን ዩቲዩብ ላይ ትለቃለህ 200ሺ ተመልካች ታገኛለህ ።የተዋጣለት የመዝሙር ነጋዴ ትሆናለህ።
9) አጥማቂነት፦አጥማቂነት ክህነት ያላቸው ሰዎች ሁሉ የሚከውኑት አገልግሎት እንጂ ለጥቂቶች ብቻ የሚሰጥ ጸጋ አይደለም።ብዙዎች ግን የማጥመቅ ጸጋ ተሰጥቶናል እያሉ ምስኪኑን ሕዝብ ይነዱታል ኪሱንም ያጥቡታል።እነዚህ ሰዎች ሕዝቡን በመዝረፍ በኢኮኖሚ የበለጸጉ ናቸው በአሜሪካ ሳይቀር ሰፊ መሬቶችን ገዝተው የግል ቤተ ክርስቲያን እስከጳጳሳትን ሳይቀር
10)የከተሜ ንስሐ አባት መሆን፦ ከንስሐ ሌጆቻቸው ገንዘብ መሰብሰብ ከዚያን ከጥቂት ዓመታት በኋላ ባለቤት ባለ መኪና መሆን። ንስሐን በብር መግዛት ይሉሃል ይኽ ነው።እውነተኛ ካህናት እናንተን አይመለከትም።
11) ደብተራነት(መርጌትነት)፦ ደብተራነት የእውቀት ማደርያ መሆን ነው።ግብዞች ግን በዚህ ስም ተጠቅመው መስተፋቅር እንሠራለን፣ ገንዘብ እንድታገኙ እናደርጋለን ወዘተ... እያሉ ሚሊየኖችን ያታልላሉ ።አሁን አሁንማ ተራ ሰዎች ሳይቀሩ በቴሌግራም መርጌታ እገሌ እያሉ በማጭበርበር ላይ ይገኛሉ።
12)የሚዲያ ልመና፦ በቲክቶክና በዩቲዩብ ፕላትፎርሞች ቤተ ክርስቲያን እንረዳለን፣ቤተ ክርስቲያን እናሠራለን በማለት የሕዝቡን ኪስ ማጠብ
13) የቲክቶክ ሰባኪ፦በዓረብ ሀገራት ያሉ ምስኪን እህቶቻችንን ለማለብ።እውነተኛ መምህሮችንና ወንድሞችን አያካትትም።
14)ባዛር፦በበረከት ስም የሕዝቡን ኪስ ማጠብ
15) ጉዞ ማዘጋጀት
16) ማኅበራትን መፈልፈል
17) ጸበል፦ጸበልን ለፈዋሽነት መጠቀሙ ቀርቶ የሕዝብ መሰብሰቢያና የገንዘብ ማግኛ ሆኗል
( ከ ”ትህትና የክርስቶስ እስረኛ“ የተወሰደ )