Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7622
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ግምታዊ መለኮታዊ ፍጻሜ፥ ገነት ማለት እና ገሃነም ማለት

Post by Naga Tuma » 20 May 2026, 19:46

መለኮታዊ አሰራር መኖሩ ለዛላለሙ ላይሻር በዐለም ሁሉ ከታወቀ ምድር ለህያዉ ፈጣሪ ኣክባሪ ዐለም ሁሉ ገነት ሆነች ማለት ይሆን?

ዐለም ዉስጥ ህያዉ ፈጣሪን የሚፈታተን ከተገኘ ወይም ከተገኘች ምድር ገሃነሙ ወይም ገሃነሟ ሆነች ማለት ይሆን?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7622
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ፍጻሜ፥ ገነት ማለት እና ገሃነም ማለት

Post by Naga Tuma » 22 May 2026, 19:46

ዘግናኝ የሆነ የሰዉ ልጆች እልቂት ዉስጥ የእግዜር ቁጣ ይኖርበት ይሆን ብሎ መጠየቅ ሃጥዓት መናገር ሊሆን ይችላል።

ምናልባት እግዜር እየመራ የምያመለክትን ለምን ይሆን ብሎ ኣለመጠየቅም ሃጥዓት ሊሆን ይችላል።

እኔ ስለ መለኮታዊ አሰራር ኣጥንቼ ለመተንተን ብቃት ኣለኝ ማለት በፍጹም ኣልችልም።

ለዚህ ሀላፊነት ያለባቸዉ የሃይማኖት መሪዎች ናቸዉ።

ይህ አስተያየት ወደ ሁለተኛዉ ዐለም ጦርነት ግዜ ይመልሰናል።

ሁለት ዘግናኝ እልቂቶችን ያስታዉሰናል።

ኣንዱ እልቂት የቆመዉ በዋነኛነት በእግዜር ስር በምትል ሃገር ነዉ።

ሌላዉ እልቂት የወረደዉ እግዜር ዬለም ብለዉ በምያምኑ የዐለም ክፍል ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

እስከዚህ ዘመን በቁምነገር ያልተስተዋለዉ የእስራኤል ፕሮፌት ተብሎ ይታወቅ የነበረዉ ሙሴ፣ እግዜር ተገልጦለት ነበር የተባለዉ፣ የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ የሃይማኖት መሪ የነበረ መሆኑ በዛ የዐለም ጦርነት ግዜ መታወቁ ነዉ።

የሁለተኛ ዐለም ጦርነት ግዜ በእግዜር ስር እያለች ዘግናኝ እልቂት በዋነኛነት ያቆመች እና ሌላ ዘግናኝ እልቂት ያወረደች ሃገር አላህ ኣክበር ባዮች ተነሱባት።

የእኔ ጥያቄ የሃይማኖት መሪዎች መለኮታዊ ምልክት እነዚህ ሁሉ ዉስጥ መኖር ይችላል ብለዉ ያምኑ ይሆን ወይ ነዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7622
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ፍጻሜ፥ ገነት ማለት እና ገሃነም ማለት

Post by Naga Tuma » 23 May 2026, 17:18

ሂዱ ንገሩ ለዐለም፣ ለዘለዓለም።

ተዓምራትን የምያሳይ እግዜር ቢኖር ነዉ ያለዉ ምርቃት ያለዉ መሆኑን።

እግዜር ዬለም ያለዉ እርግማን ያለዉ መሆኑን።

Post Reply