Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 19514
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

ጽምዶ ፅምዶ አትበለኝ ዞር በል ከፊቴ!

Post by Axumezana » 16 May 2026, 17:56

ሲፈታ ወደ እርሱ ሲታሰር ወደ እኔ
አመንዝራው ሻእብያ አበዛህ ኩነኔ፥
ፅምዶ ፅምዶ አትበለኝ ዞር በል፥ ከፊቴ
እርሱን ርሳውና መልስ የወሰድከው ንብረቴ
እህቴን ደፍረህ፥ ወንድሜን ገድለህ
ለፍርድ ትቀርባለህ እኔም አለቅህ
ኤርትራ መንግስት አልባ ስትተራመስ
ያኔ እመጣሎሁ ንብረቴን፥ ላስመልስ
ከአሰብ እስከ አዶሊስ ይገባኛል ውርስ


[/quote]
[/quote]
[/quote]


Horus
Senior Member+
Posts: 43456
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጽምዶ ፅምዶ አትበለኝ ዞር በል ከፊቴ!

Post by Horus » 16 May 2026, 18:51

አክሱም
የምር የምር ግን መለስ የተባለ ባንድ ኢትዮጵያን ባይወድ አይገርመንም! ትግራይን በዚህ ልክ መጥላቱን ግን ፍጹም የማይገባን ነገር ነው! ለአንድ ሰኮንድ ብቻ ይችሂን አስብ! መለስ አሰብን ለትግሬ እንኳን ብሎ ለሻቢያ ባይሰጥ ዛሬ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አቅጣጫ ወደ ምስራቅና ጂቡቲ/ሱማሌ መሆኑ ቀርቶ ወደ ትግሬ/አፋርና ወሎ ይሆን ነበር ። ይህ ሁሉ መንገድ ፣ ባቡር ፣ ፋብሪካና ብልጽኛ ሁሉ መስመሩ አሰብ እንጂ ሱማሌ አይሆንም ነበር። ይቺን የሕጻን ሎጂክ የማያስቡ ወያኔዎች ናቸው ትግሬን ለድፍን 60 አመት መከራዋን የሚያበሏት! ማሳዘን አይደለም ያሳፍራል!

Axumezana
Senior Member
Posts: 19514
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ጽምዶ ፅምዶ አትበለኝ ዞር በል ከፊቴ!

Post by Axumezana » 16 May 2026, 21:01

Horus ባልከው እስማማሎሁ ፥ መለስ በእጁ የነበረውን ማለትም የኤርትራን ነፃነት እውቅና ለመስጠት አሰብ ፥የኢትዮጵያ እንዲሆን ማድረግ ነበረበት። የኤርትራ እሳቤ ኢኮኖሚዋ፥በኢትዮጵያ ጥሬ እቃ፥ በኢትዮጵያ ገበያና የወደብ አገልግሎት ላይ ይመሰረታል ተብሎ ታስቦ ስለነበር፥ ኢሳያስ በቀላሉ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ትኩረታችን መሆን ያለበት ኢሳያስ የሚሸኝበት ጊዜ ስለደረሰና ኤርትራ ለተወሰነ ጊዜ መንግስት አልባ ስለምትሆን አንድነታችንን አጠናክረን ግብ ማድረግ ነው።
ኢሳያስ አፈወርቂ እንድ ሐሙስ የቀረው
ጦርነት አያስፈልግ መላ በልብ ነው
ብዙ ሳናውራ ባህር ላይ ጉብ ነው
ግብፅ፥ አረብ ሲያለቃቅስ ማህረብ ማቀበል ነው

Post Reply