Page 1 of 1
ጳጳሱ የወርቅ ጽላት ሰረቁ
Posted: 15 May 2026, 23:40
by MINILIK SALSAWI

የቤተክህነት ቁማር ....

ዕድሜ የሰጠው ፣ በጆሮው እና በዐይኑ ብዙ ነገር ይሰማል ያያል በተለይ የቤተክህነቱን ሤራ ፣

የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከመጀመሩ እና ከተጠናቀቀ በኃላ ፣ የሕንፃ ምረቃ ፣ የልማት ሥራ ጉብኝት አብዛኛው ጊዜ ለተርዮ አልያም ፣ የተሰራውን ስህተት ለመሸፈኛ የሚፈጸሙ ተግባራቶች ናቸው ፦

በዚህ ዘመን ጳጳስ የክህደት ትምህርት አስተማረ ፣ ጳጳሱ ዘረፉ ፣ ጳጳሱ ሠረቁ ፣ ጳጳሱ አጭበረበሩ ፦ ይህንን መስማት እንዴት ያማል ፣ ይህንን እውነት ለመዳኘት የሚቀመጡት እነሱ ናቸው አንዱ አንዱን አሳልፎ አይሰጥም ምክንያቱም አብዛኞቹ ነገ የእኔም እጣ ይህ ነው ብለው ስለሚያስቡ ትክክለኛ ብይን እና ፍርድ ከመስጠት ይልቅ አደባብሰው ተሸፋፍነው ያልፋሉ ።

ሰሞኑን የተሰማው እና የታየው እጅግ ይገርማል ጳጳሱ የወርቅ ጽላት ሰረቁ በሚል ጉምጉምታ የፈጠረው የሲኖዶሱ ስብሰባ ጳጳሱን ከቦታ በማንሳት የተዳፈነው ስብሰባ ማለቁን ተከትሉ ለዚህ ማርከሻ ጳጳሳቱ ተሰብስበው ሕንፃ መረቁ በሚል ሚዲያው እና የሁለቱ ጳጳሳት ምንደኞች እና ቡቹሎች እንዲህ በማለት ይዝጀምራሉ "በሁለቱ ጳጳሳት ተጀምሮ በሁለቱ ጳጳሳት አለቃ "፣

ገንዘቡን ከኪሳቸው አውጥተው ሰርተው እንደጨረሱ ፣ ይህ ህንፃ 10 ዓመት ፈጀ ተባለ ሲጀመር በነሱ የሥልጣን ዘመን ተጀመረ ከተባለ ፣ ዛሬ ለፓለቲካ ፍጆታ በድጋሚ እንዲመረጡ ከመደረጉ በፊት ለስድት ዓመታት አራት ጳጳስት ተቋሙን መርተውታል ፣ ሁለቱ በጠቅላ ዋና ሥራ አስኪያጅነት አቡነ ያሬድ እና አቡነ አብርሃም ሁለት ጳጳሳት ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊነት በድምሩ ለስድት ዓመታት አገልግለዋል ።

ታዲያ በእምነ በርድ ድንጋይ ከተፃፈው ጹሑፍ ጀምሮ ስማቸው እንደ ግል ንብረት ጎልቶ የሚታየው የሁለቱ ጳጳሳት ነው ? ይህ ምን ያሳያል ? እረ ሰው ይታዘበናል በሉ ፣ ለቤተክርስቲያን ክብር ሳይሆን ለክብራችሁ የምትጨነቁ እንደሆናችሁ ሁሉም ያውቃል ፣ ፈረጅያ ጎታቾቹ ግን ነገሩን ቀዝቀዝ አድርጉት፣

ይህ በመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት በብዙ ቢሊዮን ብር እየተሰራ ያለው የሕንፃ ፕሮጀክት እንዴት ለቅዱስ ሲኖዶስ በሪፖርት መልክ አልቀረበም ፣ ለምንስ አልቀረበም ብሎ የሚጠይቅ ማን ነው? ፣ ይህ ከፍተኛ ቢሊዮን የወጣበትን ገንዘብ የሚቆጣጠረው ማን ነው ? ዝርዝሩ ይቀርባል ....