Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7512
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቀልድ እና ቁምነገር፥ ሕልም እና ቅዠት ቁጥር 3

Post by Naga Tuma » 13 May 2026, 15:59

ይህን ሕልም ያየሁኝ ካልዘነጋሁ እ አ አ ኤፕሪል 3፣ 2026፣ ዓም ነበር። የያዝኩኝ ማስታወሻ ኣሁን አጠገቤ ዬለም።

ይህ ሕልም ከኣሁን በፊት ካየሁት ሕልም ጋር ተመሳሳይነት ኣለዉ።

ድሮ የማዉቀዉ የጎሳ ዝምድና ያለን ሰዉን መላጣ ሆኖ በሕልሜ ኣያሁኝ።

ለዓመታት ኣይቼዉ ስለማላዉቅ ዕድሜዉ ገፍቶ መላጣ መሆኑን ኣልገመትኩም። ከዓመታት በፊት ያየሁት ግዜ እራሱ ላይ ሙሉ ጸጉር ነበረዉ።

በእዉን ተመልጦ ይሁን ኣላዉቅም።

በሕልሜ እየተጓዝኩ መንገድ ላይ ተገናኘን። ተቀምጦ ስለነበረ አጠገቡ ደርሼ ሰላም ብዬ ተቀመጥኩኝ።

ሰላም እንደማለት እኔን መቆጣት ጀመረ። ገርሞኝ መልስ መመለስ ጀመርኩኝ።

ጭራሽ ብሶበት ከተቀመጠበት ተነስቶ በኣካፋ አፈር ዝቆ ኣናቴ ላይ መነስነስ ጀመረ።

ተቆጥቼዉ ተናገርኩት።

የተናገርኩትን ሰምቶ ኣካፋዉን ኣስቀምጦ ከአጠገቤ ወደ ኋላዉ ዞሮ መሄድ ጀመረ።

ከተናገርኩት ዉስጥ ምኑ ገብቶት ኣፍሮ ይሁን ሌላ ወደ ኋላዉ መዞሩ ገርሞኝ ከዛ በኋላ ነቃሁ።

ይህን ሕልም ለየት የምያደርገዉ ከሕልሙ በኋላ የተከሰተዉ የግንኙነት መስመር ነዉ።