Page 1 of 1

ብርንዶ የሚጎረሰው በአንቀፎ ነው!

Posted: 08 May 2026, 22:29
by Horus
የቃል ትርጉም፤
ብርንዶ = ቀይ (ጥሬ) ክትፎ
አንቀፎ = የቀንድ ማንኪያ

ቅብ ያውነቦ ባናተ = በአናቱ ላይ ዉፋ (ጥሬ) ቅቤ ተቀምጦበት በሻሽ ይታሰራል ። እነዚህ ጋብቻ ለመጠየቅ (ለመለመን) ለሚላኩት ሽማግሎች የሚደረግ ከፍተኛ ተቀባይነትና አክብሮት ነው ። ቅቤና ወተት በምርቃት ውስጥ ከፍተኛ ምልክትነት ያላቸው ነገሮች ናቸው ። ለምሳሌ ሆነ ተብሎ የሚደረግ እርቅና ምርቃት ሲደረግ በሲኒ ወይም ኩባያ ውስጥ ጥሬ ቅቤና ወተት ተደባልቆ ልክ እንደ ተባረከ ዉሃ መርቃት ከተደረገበት በኋላ ታዳሚው ሁሉ ግምባሩን በዚህ ቅቤና ወተት ያስነካል ። መስቀል እንደ መሳለም ፣ ጠበል እንደ መረጨት ማለት ነው ።

https://www.youtube.com/shorts/-JRjNLI9CrI